መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም
በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የረጅም ዘመን ሐዋርያዊ ጉዞ ላይ በጎ ተፅዕኖ ካላቸው የአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አባቶች መካከል አንዱ ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም ነው፡፡ ይህ አባት ምንም እንኳን በቋንቋ ውሱንነትና በቦታ ርቀት በርካቶች ሥራዎቹና ጽሑፎቹ የታወቁለት ባይሆንም ሕይወቱን በብሕትውና የመራ የትርጓሜ መጻሕፍትን፣ የቅኔ፣ የግጥምና የወግ ጽሑፍ በማዘጋጀት የኖረ ባለ በጎ ገድል አባት ነው፡፡
‹‹እግዚአብሔር በልባቸው የዋሃን ለሆኑ ቅርብ ነው፥ በመንፈስ ትሑታን የሆኑትንም ያድናቸዋል›› (መዝ.፴፫፥፲፰)
ሰዎች የዋህነት ወይንም ትሕትና ሲጎላቸው ከፍቅር ይልቅ መጥፎነት ያስባሉ፡፡ በቤተሰባዊም ሆነ በማኅበራዊ ግንኙነታቸው መከባበር እንዳይኖር፣ መናናቅ እንዲፈጠርና ክፋት እንዲስፋፋ ይጥራሉ፡፡ በዚህም ፍቅርና ሰላም አጥተው ዘወትር በስጋትና በጥላቻ ስሜት ይኖራሉ ማለት ነው፡፡
የጅማ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች እስር እየተፈጸመባቸው እንደሆነ ታወቀ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጅማ ሀገረ ስብከት የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የተላለፍወን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሽፋን በማድረግ አግባብ ያልሆነ እስርና እንግልት በምእመናንና በአባቶች ላይ እየተፈጸመ መሆኑን በማኅበረ ቅዱሳን የጅማ ማእከል አስታወቀ፡፡
የቤተ ክርስቲያንን ቅርስ ዘርፈው እጅ ከፍንጅ የተያዙ ተጠርጣሪዎች ከእስር ተፈቱ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሜታ ሮቢ ወረዳ ቤተ ክህነት ሥር የሚገኘውን የሙጤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንን ቅርስ ዘርፈው እጅ ከፍንጅ የተያዙ አራት ግለሰቦች በፍርድ ቤት ትእዛዝ ከእስር መፈታታቸውን የወዳ ቤተ ክህነቱ ሥራ አስኪያጅ መሪጌታ ክፍሌ ቱቦ አስታወቁ፡፡
‹‹በበለስ ዛፍ ሥር አየሁህ›› (ዮሐ.፩፥፶፩)
እግዚአብሔር ሁላችንንም ከበለስ በታች ያውቀናል፡፡ እግዚአብሔር ዝም የሚለው ስለማያውቀን አይደለም፡፡ ናትናኤልን እያወቀው ተንኮል የሌለበት የእስራኤል ሰው እንደሆነ ተናገረ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ በገሊላ ባሕር እንዳስተማረው ትምህርት ሊሰሙ፣ ሊማሩ፣ ሊለወጡ ባለመቻላቸውም ‹‹ኮራዚ ወዮልሽ! ቤተ ሳይዳ ወዮልሽ! በእናንተ የተደረገው ተአምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርጎ ቢሆን ቀድሞ ማቅ ለብሰው አመድም ነስንሰው በተቀመጡ ንስሓም በገቡ ነበር፡፡ ነገር ግን ጢሮስና ሲዶና ከእናንተ ይልቅ በፍርድ ቀን ይቅርታን ያገኛሉ፡፡ አንቺም ቅፍርናሆም እስከ ሰማይ ድረስ ከፍ ከፍ ብትዪ እስከ ሲኦል ትወርጃለሽ›› ብሎ ጌታችን ተናገሯል፡፡ (ሉቃ.፲፥፲፫-፲፭)
‹‹የይቅርታ ልብ ይኑረን››
የሰው ልጅ ወደ አምላኩ እግዚአብሔር ይመለስ ዘንድ የይቅርታ ልብ ሊኖረው ይገባል፡፡ አዳም ይቅርታ ባይጠይቅ እና ከእግዚአብሔር ይቅርታን ባያገኝ ኖሮ የዘለዓለም ቅጣት ይፈረድበት ነበር፡፡ ሆኖም ከሚኖርባት ገነት ወደ መሬት በመምጣት ቅጣት ተቀብሏል፡፡ አዳም ዕንባ ሲያልቅበት ደም፣ ደም ሲያልቅበት እዥ እያነባ ‹‹በድያለሁ ይቅር በለኝ›› ብሎ ፈጣሪን ይቅርታ በመጠየቁ ድኅነትን አግኝቷል፡፡ ይቅርታ ሰውን እንደገና ወደጥንት ክብሩ የመለሰ ትልቅ ጸጋ ነው፡፡ ያለ ይቅርታ ዓለም ለኃጢአት ስርየትም ሆነ ቸርነት የበቃ አይሆንም፡፡
ሰማዕታተ ጽድቅ ዘኢትዮጵያ!
‹‹እንደተማራችሁት በሃይማኖት ጽኑ›› (ቆላ. ፪፥፯)
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆቿ ሃይማኖታቸውን እንዲያጸኑ ታስተምራለችና ስለሃይማኖታችን ልንኖር ይገባል፤ ሃይማኖት የእግዚአብሔርን ህልውና ማወቅ ለእርሱ መታመን ነውና ምእመናን ሁሉ በሃይማኖት መጽናት አለብን፡፡ ይህም በሕይወታችን የሚመጣብንን መከራ እና ፈተና ሁሉ በትዕግሥት እንድናልፍ ይረዳናል። ቅዱስ ጳውሎስ አስቀድሞ ለቆላስይስ ምእመናን ማስተማሩን በማስታወስ እኛ ክርስቲያኖች በቅድሚያ የተማርነውን ትምህርት አጽንተን በሃይማኖት እንድንቆይ ነግሮናልና።
‹‹የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ ትወደኛለህን?›› (ዮሐ. ፳፩፥፲፭)
የዮና ልጅ ስምዖን በቤተ ሳይዳ ዓሣ አጥማጅ የነበረ ሰው ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተጠመቀበት ዕለት ማግሥት ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ አድርጎ መረጠው፤ ስሙም ጴጥሮስ ተባለ፡፡ ወንጌልን ይሰብክ እና ምእመናንም ይፈውስ ዘንድ ሥልጣንና ኃይልን የተሰጠው ቅዱስም ሆነ፡፡ የአስቆርቱ ይሁዳ ጌታን ለአይሁድ አሳልፎ እስኪሰጠው ድረስም ከእርሱ ጋር ኖሯል፡፡ ፍጹም ሃይማኖት፣ ለጌታውም ቅንዓት እና ፍቅርም ነበረው፡፡ (ስንክሳር ሐምሌ ፭)
‹‹የጌታ ፈቃድ ይሁን ብለን ዝም አልን›› (ሐዋ.፳፩፥፲፬)