መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
የእምነት አርበኞች!
ሕዝቡን እያሳተ ከገደል ቢመራ
ትእዛዙ ሲፈጸም ለሥጋው የፈራ
የእምነት አርበኖች ሠለስቱ ሕፃናት
ከፊቱ በመቆም መሰከሩ ለእምነት
በእሳት ሲያስፈራ በሚከስመው ነዶ
ጣኦትን ሊያስመልክ ፈጣሪን አስክዶ
ከላይ ከሰማያት መልአክን አውርዶ
እሳቱ ሲበርድ ሰይጣን በዚህ ሲያፍር
ጽናት ተጋድሏቸው ገሀድ ሲመሰክር
የሰው ተፈጥሮና ሥርዓተ ጾታ
የሰው ዘርና መሠረት የሆኑት አዳምና ሔዋን ስያሜያቸው በጾታ ተለይቶ በማይታይበት ሁኔታ (በጋራ ስያሜአቸው) ‹‹ሰው›› የሚሰኙ ሲሆን ‹‹አዳም›› በመባል የሚታወቀው ቀዳሚ ፍጥረትም ከወንድ ጾታ በተጨማሪ የሰው ዘር ሁሉ ምንጭና መጠረያ ሆኖም አገልግሏል፡፡
በአጠቃላይ ‹‹ተባዕታይ/ዊ/››- “ወንዳዊ፣ ወንድ፣ ወንዳማ፣ ወንዳ ወንድ፣ ብርቱም” ማለት ሲሆን ‹‹አንስታይ/ዊ/››- “ሴታም፣ ሴትማ፣ ሴት፣ ባለ ሴትም” የሚለውን ያመለክታል፡፡ አንስትና ብእሲት ለሰው ብቻ ይነገራል፡፡ (ዘፍ.፩፥፳፯)
ጾታቸውና ግብራቸው በአንድነት ሲገለጽ ደግሞ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ስያሜዎች የሚከተሉትን ትርጉሞች ይይዛሉ፡-
አዳም ማለት “የሚያምር፣ ደስ የሚያሰኝ ሰው፣ ደግ፣ መልከ መልካም፣ የመጀመሪያ ሰው፣ የሰው ሁሉ አባት” የሚል ትርጒም ተሰጥቶታል፡፡
ሔዋን ማለት “ሕይወት” ማለት ነው፡፡ “ሔዋን” ብሎ የሰየማትም አዳም ሲሆን ስያሜው ‹‹የሕያዋን ሁሉ እናት /እመ ሕያዋን/›› መሆኗን ያመለክታል፡፡ (ዘፍ.፪፥፬-፳፬) ከዚህም ሌላ ረዳት ትባላለች፡፡
ለቤተ ክርስቲያን የሚበጅ ብቁ ዜጋ ለማፍራት በልዩ ትኩረትና በንቃት መሥራት እንደሚገባ ተገለጸ!
የማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል ለትውልድ ማእከል ግንባታ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ በታኅሣሥ ወር ፳፻፲፯ ዓ.ም. ባካሄደው ልዩ መርሐ ግብር ላይ በመሪጌታ ባሕረ ጥበብ ሙጬ “የሉላዊነት ተጽዕኖ በኦርቶዶክስ ላይ” በሚል ርእስ የቀረበው ጥናታዊ ጽሑፍ ለቤተ ክርስቲያን የሚበጅ ብቁ ዜጋ ለማፍራት በልዩ ትኩረትና በንቃት መሥራት እንደሚገባ የሚያመለክት እንደሆነ ተገልጿል፡፡
የቱን ታስታውሳላችሁ?
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁልን? ትምህርት እንዴት ነው? እየበረታችሁ ነውን? የምትማሩትን ትምህርት እያጠናችሁ እንደሆነ ተስፋችን ነው፤ በርቱ! ልጆች ለዛሬ ይዘንላችሁ የቀረንበው ባለፉት በተከታታይ ሳምንታት ስንማማረው ከነበረው የአማላጅነት ትምህርት ካነበበችሁት (ከተማራችሁት) መካከል “የቱን ታስታውሳላችሁ” በሚል ርእስ ጥያቄዎችን ነው፡፡ በጥንቃቄ አንብባችሁ መልሶቻችሁን በድረ ገጽ አድራሻችን “website.amharic@eotcmk.org” እና “https://t.me/Hiwot122716” ትልኩልናላችሁ!
የሰው ተፈጥሮና ሥርዓተ ጾታ
የሰው ልጅ ተፈጥሮአዊ ባሕርይ በስሙ ተገልጧል፡፡ የተለየ የሚያደርገውም በአምሳለ እግዚአብሔር የተፈጠረ መሆኑ ነው፤ ነገር ግን አሁን ባለው ዓለም ውስጥ ክብሩን ለማዋረድ የሚሞክር ነገረ ህልውናም ፍጹም በተሳሳተ እይታ የሚተነትን የሐሰት “ሳይንስ” ይስተዋላል፡፡ መላእክት ዕውቀት አላቸው፤ ነገር ግን በኃይለ ዘር አይራቡም:: ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ እንስሳት ዕውቀት የላቸውም፤ በኃይለ ዘር ግን ይራባሉ፤ ሰው ግን እንደ መላእክት ዕውቀት እንደ እንስሳት ደግሞ በኃይለ ዘር ስለሚራባ ከሁለቱም የተለየ ያደርገዋል፤ ዳግመኛም መላእክት ሕያዋን ናቸው፤ እንስሳት ደግሞ መዋትያን ናቸው፤ የሰው ልጅ ግን ሕያውም መዋቲም በመሆኑ የተለየ ነው፤ እግዚአብሔር እንዲህ ውብና ቅዱስ አድርጎ የፈጠረው ስላለው ክብር ባለ መረዳትና ባለ ማወቁ ወደ ኃጢአት ሲወድቅ ይስተዋላል፡፡
ማኅበራዊ ሕይወታችን!
ሕይወታችንን ስናስብ የሌሎችን በሕይወት መቆየት እንጠባበቃለን። በጋራ ዓለም ላይ አብሮ የጋራ ዓለምን ማቅናት ላይ እንድንመረኮዝ እንገደዳለን። በሕገ ተፈጥሮ ውስጥ ለራሱ የተፈጠረ ፍጥረት የለም። ከእሑድ እስከ ዓርብ ያሉ ፍጥረታት እርስ በራሳቸው ተመጋጋቢ ቢሆኑም ሁሉም ግን ስለ አዳም ተፈጥረዋል። አንዳንዶቹ ለምግበ ሥጋ ምግበ ነፍስ፣ አንዳንዶቹ ለአንክሮ ለተዘክሮ፣ አንዳንዶቹ ለመድኃኒትነት፣ አንዳንዶቹ ለምስጋና፣ አንዳንዶቹ አዳም መሥዋዕት አድርጎ ሊያቀርባቸው፣ ሌሎቹ ደግሞ ለሌላ ለተለያየ ነገር ተፈጥረዋል። እነዚህ ሁሉ ለራሳቸው ሲባል አልተፈጠሩም።
ምድር እስከ መቼ ታለቅሳለች?
እውነት ነው! ደም በከንቱ ፈስሶ አይቀርም፡፡ የንጹሐን ደም ዋጋ ያስከፍላል፤ ልጅን የልጅ ልጅን ያጠፋል፤ ከርስት ከጉልት ይነቅላል፤ እሳትና ዲን ያዘንማል፤ ምድርንም ያቃጥላል፡፡ እነዚህ ሁሉ ዛሬ እንደዘበት የሚገደሉ ነፍሳት ሁሉ ክሳቸው አይቋረጥም፤ ቃላቸውም እስከ ሰማየ ሰማያት ያስተጋባል፤ የገዳዮች ልጆች ከዚህ ምድር እስኪጠፉ፣ የልጅ ልጆቻቸውም ከሰው ልጅ ተለይቶ እስኪጠፋ ትውልዳቸውም እስኪደመሰስ ነፍሳት ይካሰሳሉ፤ የነፍሳት ጌታም እውነተኛ ዳኛ ነውና፤ ፍትሕ ርትዕ አያጎድልምና፤ ፍርዱን በምድርና በውስጧ ባለን በሁላችን ላይ ያመጣል፡፡ ሰማያትን ይለጉማል፤ ምድርን ያናውጣታል፤ ጠለ ምሕረትን እክለ በረከትን እንዳታስገኝ ፣ የመዓት ነፋሳት እንዲነፍሱና መቅሠፍት እንዲሆኑ፣ ዝናማት በረዶ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡ ልንመለስ አልወደድንምና፡፡
አገልግሎቴን አከብራለሁ!
በእያንዳንዳችን ሕይወት ውስጥ “አገልግሎት” የሚለው ቃል በተለያየ መልኩ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ሰው በግሉ፣ ከቤተ ሰቡ እንዲሁም ከማኅበረሰቡ ጋር ከሚያከናውናቸው ተግባራት ውስጥ “አገልግሎቴ” ብሎ የሚያስባቸው ምግባሮች ሊኖሩት ይችላሉ፡፡ ለዚህም ዕውቀት ይኑረው አይኑረው ለማወቅ ቢያዳግትም ከቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ግን አገልግሎትን ማወቅ፣ መረዳትና መተግበር እንዲችል ግንዛቤ መፍጠር ተገቢ ነው፡፡
የጽድቅ ብርሃን
በብርሃናት ልብስ ተሸልሞ…
በብዙ ሀብታት ያጌጠ
ሥጋን ከነምኞቱ ሰቅሎ…
ለምትበልጠው ጸጋ ያለመታከት የሮጠ
ይህ ነው ዜና ማርቆስ ትውልድ የሚያወሳው
የጽድቅ ብርሃን… ጧፍ ሆኖ የሚያበራው!
ወርኃ ታኅሣሥ
ሰፊ አስተምህሮ እና ምሥጢር ካላቸው ወራት አንዱ የታኅሣሥ ወር ነው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ በባሕረ ሐሳብ ቀመር ቀኑ ዘጠኝ ሌሊቱ ዐሥራ አምስት ይሆናል፤ ከዚህ በኋላ ቀኑ እየጨመረ ሌሊቱ እያነስ ይሄዳል