ተዝካረ ዕረፍቱ ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
/in ምንባባት, ዝክረ ቅዱሳን /by Mahibere Kidusanተአምራቱና ትሩፋቱ እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነ ቅዱስ አባት ተጋዳይ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የዕረፍቱ ቀን መታሰቢያ መጋቢት ፭ ነው፡፡ ይህም ቅዱስ አባት በተወለደበት ቀን ድንቅ የሆነ ሥራን ሠራ፤ ተነሥቶ ከእናቱ እቅፍ ወርዶ ከጨለማ ወደ ብርሃን ላወጣኸኝ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ሰግዷልና ምስጋና አቅርቧልና፡፡
ምኵራብ
/in አጽዋማት, ወቅታዊ ትምህርት /by Mahibere Kidusan‹‹ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን እወዳለሁ፤ የሰንበት ጌታዋ የምሕረት አባቷም እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም የሰንበት ጌታዋ ነው፡፡ ያባቴን ቤት የንግድ ቦታ አታድርጉት››
ዝርዝር ርባታ
/in ግእዝ ይማሩ /by Mahibere Kidusanውድ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? የእግዚአብሔር አምላካችን ስም የተመሰገነ ይሁን! ባለፈው የትምህርታችን ክፍለ ጊዜ የ ‹‹ሀ፣ አ፣ ወ እና የ›› የሚያመጡት የርባታ ለውጥ በግሥ ርባታ አስተምረናችሁ ነበር፡፡ በዚህ ሳምንት ደግሞ ለሰጠናችሁ መልመጃ ምላሽና ስለ ዝርዝር ርባታ እንመለከታለን፤ በጥሞና ተከታተሉን!
ቅድስት
/in አጽዋማት, ወቅታዊ ትምህርት /by Mahibere Kidusanቅድስት ማለት ‹የተለየች፣ የነጻች፣ የከበረች› ማለት ነው፡፡ ይኸውም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጾም የጀመረባት፣ ልዩ፣ የተቀደሰች፣ የከበረች፣ ንጹሕ፣ ክቡር በሚሆን በጌታችን የተጾመች መሆኗን ያመላክታል፡፡ ይህች ጾም በማቴዎስ ወንጌል የተገለጠች ስትሆን፣ አምላካችን በገዳመ ቆሮንቶስ ዐርባ መዓልትና ዐርባ ሌሊት በጾመበት ጊዜያት ሦስቱን አርእስተ ኃጣውእ ድል አድርጓል፡፡ (ማቴ.፬፥፪)
‹‹ዐርባ ቀንና ዐርባ ሌሊትም ጾመ›› (ማቴ.፬፥፪)
/in ለሕፃናት /by Mahibere Kidusanውድ የእግዚአብሔር ልጆች! ለከበረው ጤንነታችሁ እንዴት አላችሁ? የመንፈቀ ዓመቱ ትምህርት ተጠናቆ ፈተና ተፈትናችሁ ጥሩ ውጤት እንዳመጣችሁ ተስፋችን ነው፤ በርቱ!
ልጆች! ለዛሬ የምንማረው ስለ ዐቢይ ጾም ነው፤ ዐቢይ ማለት ታላቅ ማለት ነው፤ አባቶቻችን በሠሩልን ሥርዓት መሠረት ከሰባት ዓመት በላይ የሆኑ ክርስቲያኖች ሁሉ እንዲጾማቸው የታወጁ ሰባት አጽዋማት አሉ፤ ከእነዚህ መካከል ደግሞ አንዱ ዐቢይ ጾም ነው::
ፈቃደ እግዚአብሔር
/in ስብከት /by Mahibere Kidusanበሰዎች ሕይወት ውስጥ የእግዚአብሔር ክቡር ፍቃድ አለ፤ እነዚህም ሁለት ፍቃዳት ናቸው፡፡ አንደኛው ግልጽ ፈቃድ ሲባል ሁለተኛው ደግሞ ስውር ፈቃድ ይባላል፡፡ ግልጽ ፍቃዳት የሚባሉት በመጽሐፍ ተጽፈው የምናነባቸው ናቸው፤ በሕግ መልክ በብሉይ እና በሐዲስ ኪዳን የተቀመጡልን ትእዛዛቱ እንድንሰማቸው፣ እንድንማራቸው፣ እንድንኖራቸው የተሰጡትን ነው፡፡ መጽናናትን፣መረጋጋትን ገንዘብ የምንዳርባቸው፣ ተግሣጽንና ምክርን የምንሸምትባቸው ገባያችን ናቸው፡፡
ዘወረደ
/in አጽዋማት, ወቅታዊ ትምህርት /by Mahibere Kidusanከሰማይ ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም ካለው ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ቃል በመነሣት ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በዚህ ዕለት ምስባክ ‹‹አዳምን ለማዳን ከሰማይ የወረደውን አይሁድ ሰቀሉት፤ የሰማይን ሥልጣን ያለው የሁሉ ጌታ እንደሆነም ምንም አላወቁም›› ብሎ ተናግሮ ነበር፡፡ ይህም ድርሰት በቤተ ክርስቲያናችን የጾም መጀመሪያ የሆነው ዕለተ ሰንበት ዋዜማ፣ መግቢያ (መሐትው) ሆኖ ከዋዜማ በፊት ምንጊዜም በየዓመቱ ይቆማል፤ ይዘመራል፤ ይመሰገናል ማለት ነው፡፡
ዐቢይ ጾም
/in አጽዋማት, ክርስቲያናዊ ሕይወትና ሥነ ምግባር, ወቅታዊ ትምህርት /by Mahibere Kidusan‹ዐቢይ›› የተባለው የዓለማት ፈጣሪ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአርአያነት ጾሞ የመሠረተው ጾም ስለሆነ ነው፡፡ በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ካሉት ሰባት የአዋጅ አጽዋማት ረጅሙ (፶፭ ቀን ያለው) ስለሆነ ደግሞ ‹‹ሁዳዴ›› ይባላል፡፡ ኢትዮጵያዊው የዜማና የቅዱሳት መጻሕፍት ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በዐቢይ ጾም ውስጥ የሚገኙትን ስምንት ሣምንታት ለትምህርት፣ ለአዘክሮና ለምስጋና በሚመች መልኩ ልዩ ስያሜዎች ሰጥቷቸዋል፡፡ ስለሆነም በእያንዳንዱ ሳምንት (ሰንበት) የሚነበቡ፣ የሚተረጎሙ፣ የሚዘከሩ፣ የሚዘመሩ ልዩ ልዩ መጽሐፍ ቅዱሣዊ ኩነቶችና አስተምህሮዎች አሉ፡፡
‹‹ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው›› (ማቴ.፬፥፩)
/in አጽዋማት, ወቅታዊ ትምህርት /by Mahibere Kidusanበወንጌል ቅዱስ ማቴዎስ ስለ ጌታችን መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስ ዐቢይ ጾም ሲጽፍ ‹‹ከዚያ ወዲያ›› በማለት ከጀምረ በኋላ እርሱ ለሰዎች ድኅነት ሲል ለዐርባ ቀንና ሌሊት ያለ መብልና መጠጥ በጾም በምድረ በዳ እንደቆየ ይገልጽልናል፡፡
መጽሔተ ተልእኮ ዘማኅበረ ቅዱሳን
/in ምንባባት /by Mahibere Kidusanመጽሔተ ተልእኮ ዘማኅበረ ቅዱሳን መጽሔት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን በሕዝብ ግንኙነትና ትብብር አገልግሎት ማስተባበሪያ የሚዘጋጅ ነው፡፡ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መጽሔቱን ያንብቡ!