መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
አገልግሎቴን አከብራለሁ!
በእያንዳንዳችን ሕይወት ውስጥ “አገልግሎት” የሚለው ቃል በተለያየ መልኩ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ሰው በግሉ፣ ከቤተ ሰቡ እንዲሁም ከማኅበረሰቡ ጋር ከሚያከናውናቸው ተግባራት ውስጥ “አገልግሎቴ” ብሎ የሚያስባቸው ምግባሮች ሊኖሩት ይችላሉ፡፡ ለዚህም ዕውቀት ይኑረው አይኑረው ለማወቅ ቢያዳግትም ከቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ግን አገልግሎትን ማወቅ፣ መረዳትና መተግበር እንዲችል ግንዛቤ መፍጠር ተገቢ ነው፡፡
የጽድቅ ብርሃን
በብርሃናት ልብስ ተሸልሞ…
በብዙ ሀብታት ያጌጠ
ሥጋን ከነምኞቱ ሰቅሎ…
ለምትበልጠው ጸጋ ያለመታከት የሮጠ
ይህ ነው ዜና ማርቆስ ትውልድ የሚያወሳው
የጽድቅ ብርሃን… ጧፍ ሆኖ የሚያበራው!
ወርኃ ታኅሣሥ
ሰፊ አስተምህሮ እና ምሥጢር ካላቸው ወራት አንዱ የታኅሣሥ ወር ነው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ በባሕረ ሐሳብ ቀመር ቀኑ ዘጠኝ ሌሊቱ ዐሥራ አምስት ይሆናል፤ ከዚህ በኋላ ቀኑ እየጨመረ ሌሊቱ እያነስ ይሄዳል
የቅዱሳን አማላጅነት
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁልን? እንኳን ለጾመ ነቢያት (ለገና ጾም) አደረሳችሁ! ጾመ ነቢያት አባቶቻችን ነቢያት አምላካችን ተወልዶ ያድነን ዘንድ የጾሙት ጾም ነው፤ እኛ ደግሞ ከሰማያት ወርዶ፣ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ አድኖናል ስንል ውለታውንና ፍቅሩን እያሰብን እንጾማለን!
በዘመናዊ ትምህርታችሁ የዓመቱን አንድ አራተኛ (ሩቡን የትምህርት ዘመን) ጨረሳችሁ አይደል! መቼም ከነበራችሁ ዕውቀት እንደጨመራችሁ ተስፋ እናደርጋለን! በርትታችሁ ተማሩ እሺ! መልካም!
ባለፈው ተከታታይ ትምህርታችን ስለ አማላጅነት ምንነት፣ ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና ስለ ቅዱሳን መላእክት አማላጅነት በተወሰነ መልኩ ተምረን ነበር፤ ዛሬ ደግሞ ስለ ቅዱሳን አባቶቻችንና እናቶቻችንን አማላጅነት እንማራለን! ተከታተሉን!
ምድር እስከ መቼ ታለቅሳለች?
ምድር ዛሬ እያለቀሰች ነው፡፡ ግን እስከ መቼ ታለቅሳለች? ሰዎችስ ከክፋታቸው የሚመለሱት መቼ ነው? የምድረ በዳው ሣርስ እስከ መቼ ደርቆ ይቀጥላል? አዕዋፋትና እንስሳትስ እስከ መቼ ያልቃሉ? እግዚአብሔርስ ምድርን እስከ መቼ ነው የሚቆጣት? ቅዱሳንስ ስለ ደማቸው እስከ መቼ ምድርን ይካሰሷታል? ነቢዩ ኤርምያስ የሚጠይቀውን ጥያቄ አሁንም እኛ እንጠይቃለን፡፡
‹‹ሽማግሌዎች ከአደባባይ፥ ጎልማሳዎች ከበገናቸው ተሻሩ›› (ሰቆ.ኤር.፭፥፲፬)
በኤርምያስ ዘመን የሆነው እንዲህ ነበር፡፡ ልክ እንደ ዛሬው ክፉዎች ሠልጥነው ነበር፤ ከመከራቸው የተነሣ ልጆች፣ ድሃ አደጎችና አባት እናት የሌላቸው ሕፃናት ብዙዎች ነበሩ፤ እናቶች እንደ መበለቶች ሆነው ነበር፡፡ ውኃቸውን በብር እንጨቶቻቸውን፣ በዋጋ ገዝተው የተጠቀሙበት ጊዜ ነበር፡፡
ጽዮን ሆይ ክበቢኝ!
የገባልሽ ኪዳን የሰጠሽ መሐላ
ከንቱ ነበረ ወይ የጨረቃ ጥላ?
በአጋንንት ፍላጻ ነፍሴ ብትወጋ
ምልጃሽ ነው ተስፋዬ ከጥላሽ ልጠጋ፡፡
ጽዮን ሆይ ክበቢኝ ለውዳሴሽ ልትጋ
የኃጢአት ጎዳናዬ መንገዴ ይዘጋ!
ብፁዕ አቡነ አብርሃም እየተዳከመ የመጣው የብራና መጽሐፍ ዝግጅት ዳግም ማንሠራራቱን ገለጹ
ሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ ድርጅት በኅዳር ፲፭፤ ፳፻፲፯ ዓ.ም. በጠቅላይ ቤተ ክህነት በአካሄደው የምስጋና መርሐ ግብር ላይ የተገኙት የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳርና ሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ባስተላለፉት መልእክት የብራና መጽሐፍት ዝግጅት ረጅም ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ እየተዳከመ የመጣ ቢሆንም ዛሬ ላይ በዚህ መልክ እያደገ መምጣቱ የሚያስደስት መሆኑን አክለው ገልጸዋል፡፡
‹‹ፈኑ እዴከ እምአርያም፤ ወአድኅነኒ፤ እጅህን ከአርያም ላክ፤ አድነኝም›› (መዝ. ፻፵፫፥፯)
ይህ ሱባኤ፣ ዘመነ ነቢያት፣ ወርኃ ጾመ ነቢያት ከመቼውም በላይ አስጨናቂዎቻችን፣ በሥጋ በነፍስ የሚዋጉን፣ አጋንንት ውሉደ አጋንንት፣ ረቂቃኑ አጋንንት፣ ልቡሰ ሥጋ አጋንንት፣ ሁሉ እንደ ጤዛ ረግፈው፣ እንደ ትቢያ ተበትነው፣ ከሕዝበ ክርስቲያንና ከቤተ ክርስቲያን ይርቁ ዘንድ፣ የክርስቶስም መንጋ በሰላም በበረቱ ያድር ዘንድ፣ ‹‹እጅህን ከአርያም ላክ፤ አድነንም›› የምንልበት ጊዜ ነው፡፡
የቅዱሳን መላእክት አማላጅነት
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! ለከበረው ጤንነታችሁ እንዴት አላችሁልን?! በፈቃደ እግዚአብሔር አዲሱን ዓመት ከተቀበልን ሁለት ወራትን አሳልፈን ሦስተኛውን ጀምረናል! ለዚህ ያደረሰን አምላክ ይመስገን! ለመሆኑ ትናንት ከነበረው ማንነታችሁ ላይ ምን ለውጥ አመጣችሁ? በዘመናዊ ትምህርትስ ምን ያህል ዕውቀትን ሸመታችሁ? በመንፈሳዊ ሕይወታችሁስ በሥነ ምግባር ምን ያህል ለውጥ አመጠችሁ? በርትታችሁ መማር ይገባል፤
….ባለፈው ተከታታይ ትምህርታችን ስለ አማላጅነት ትርጉም እንዲሁም ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ተምረን ነበር፡፡ በዚህ የትምህርት ክፍለ ጊዜያችን ደግሞ ስለ ቅዱሳን መላእክት አማላጅነት እንማራለን! መልካም!