መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
መጽሔተ ተልዕኮ- ሚያዝያ 2005
ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ
ወርቅ ሠሪው ጴጥሮስ(ለሕፃናት)
በእመቤት ፈለገ
ልጆች እንደምን ሰነበታችሁ? ዛሬ ይዘንላችሁ የቀረብነው የአንድ ጌጣጌጥ የሚሠራ ሰው ታሪክ ነው ተከታተሉ፡፡
ከብዙ ዓመታት በፊት ስሙ ጴጥሮስ የተባለ በጣም ጥሩ ክርስቲያን ነበር፡፡ የተለያዩ ጌጣጌጦች ማለትም ቀለበት፣ የአንገት ሃብል ይሠራ ነበር፡፡
“በእንተ ጦማረ ሐሰት”
ግንቦት 13፣ 2003 ዓ.ም
ሕገ ቤተ ክርስቲያን ስለ ቅዱስ ሲኖዶስና ስለ ቅዱስ ፓትርያርክ ምን ይላል?
ግንቦት 11፣2003ዓ.ም
ቅዱስ ሲኖዶስ በ1991 ዓ.ም ባወጣው ሕገ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስለ ቅዱስ ሲኖዶስና ስለ ቅዱስ ፓትርያርክ የሚናገሩ ምዕራፎች እና አንቀጾችን አቅርበናል፡፡
ምዕራፍ ሁለት
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ
1. በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ የመንበረ ሐዋርያት ወራሽ ስለሆነ በቤተ ክርስቲያኒቱ የመጨረሻው ከፍተኛ ሥልጣን ባለቤት ነው፡፡
2. ከማንኛውም የቤተ ክርስቲያኒቱ የሥልጣን መዋቅር ሁሉ የበላይ አካል ቅዱስ ሲኖዶስ ስለሆነ ሕጐችን፣ ልዩ ልዩ ደንቦችንና መመሪያዎችን የማውጣትና የዳኝነት ሥልጣን አለው፡፡
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ዛሬ ተጀመረ፡፡
ግንቦት 10፣ 2003ዓ.ም
ቅዱስ ሲኖዶስ ጠንካራ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል
ግንቦት 10/2003 ዓ.ም.
«እርሳቸው የያዙት መንገድ ሙሉ በሙሉ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ማዳከም ነው፡፡ » ማኅበረ ቅዱሳን
ማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ፕሮግራም ቢሮ ያከናውናቸውን ተግባራት አስታወቀ።
ሥራዎቹንም የሚያሳይ ዓውደ ጥናት በኢትዮጵያ የስብሰባ ማእከል እንደሚካሔድ ተገልጧል
ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም (ክፍል ሦስት)
ዲ/ን ዮሐንስ ልሳነወርቅ
ግንቦት 4፣ 2003ዓ.ም
ከክፍል ሁለት የቀጠለ
5.የሥጋ(ሰውነት) ክብር (The value of the Body)
ቅዱስ ኤፍሬም የሥጋን ክብር ለመንቀፍ ከሚሹ ከተወሰኑ የቀድሞ የክርስትና ልማዶች መገለጫ ከሆኑት ከፕላቶናዊ ወይም ከምንታዌ ዝንባሌዎች ፣ በእጅጉ የራቀ ነው። ለቀና አመለካከቱ መነሻው ነጥብ ሥጋ ከእግዚአብሔር ፍጥረታት መካከል ስለሆነ ሊጠላ አይገባዉም የሚል እውነታ ነው፤ በየትኛዉም መንገድ ክፉ ተደርጎ ከሚታሰበው አስተሳሰብ የራቀ ይሁን። ግና በተጨማሪ ቅዱስ ኤፍሬም ሦስት ጠቃሚ ግንዛቤዎች አሉት።
የሆሣዕና ምንባብ17(ዮሐ.5÷11-31)
እርሱም መልሶ÷ “ያዳነኝ እርሱ፡- አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለኝ” አላቸው፡፡ አይሁድም÷ “አልጋህን ተሸክመህ ሂድ ያለህ ሰውዬው ማነው?” ብለው ጠየቁት፡፡ ያ የተፈወሰው ግን ያዳነው ማን እንደ ሆነ አላወቀም፤ ጌታችን ኢየሱስ በዚያ ቦታ በነበሩት ብዙ ሰዎች መካከል ተሰውሮ ነበርና፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ያን የዳነውን ሰው በቤተ መቅደስ አገኘውና÷ “እነሆ÷ ድነሃል፤ ግን ከዚህ የባሰ እንዳያገኝህ ደግመኛ እንዳትበድል ተጠንቀቅ” […]