መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
ማኅበረ ቅዱሳን ሐዋርያዊ አገልግሎት በአርሲ ሀገረ ስብከት አካሔደ
ታኅሣሥ 20/2004 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ሐዋርየዊ
አገልግሎት በአርሲ ሀገረ ስብከት ከኅዳር 29/2004 ዓ.ም እስከ ታኅሣሥ 10/2004 ዓ.ም ለ11 ተከታታይ ቀናት በተለየዩ ወረዳዎች አካሔደ፡፡ 27 አባላት የተሳተፉበት ሐዋርያዊ አገልግሎት በተመረጡ 6 ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ ቤተ ክርስቲያናት እንዲሁም በአሰላ ከተማ በተሳካ ሁኔታ የተከናወነ ሲሆን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያፈራቻቸው የማኅበረ ቅዱሳን ሰባኪያነ ወንጌል አማካይነት በአውደ ምሕረት ላይ ለምእመናን ሰፋ ያለ የወንጌል ትምህርት ተሰጥቷል፡፡ በማኅበሩ መዝሙር ክፍል አባላት አማካይነት ከአባቶች እግር ስር ቁጭ ብለው የተማሩትን የቤተ ክርስቲያኗን ሥርዓትና ትውፊት የጠበቀ ያሬዳዊ ዝማሬ አቅርበዋል፡፡
በዓለ ክብሩ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል
ታኅሣሥ 18/2004 ዓ.ም
ነቢዩ ዳንኤል “ዐይኖቼንም አነሣሁ” አለና አስከትሎ “እነሆም በፍታ የለበሰውን ጥሩም የአፌዝን ወርቅ በወገቡ ላይ የታጠቀውን ሰው አየሁ፡፡ አካሉም እንደ ቢረሌ ይመስል ነበር፤ ፊቱም እንደ መብረቅ አምሳያ ነበረ፤ ዐይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፣ የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበረ፡፡… ይህንም ታላቅ ራእይ አየሁ፤ ኀይልም አልቀረልኝም፤ ክብሬም ወደ ውርደት ተለወጠብኝ ኀይልም አጣሁ፡፡ የቃሉንም ድምፅ ሰማሁ፤ የቃሉን ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ደንግጬ በምደር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ” አለ፡፡(ዳን.10፡5-9)
ሕንፃ ሰብእ ወይስ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ይቀድማል?
ታኅሣሥ 16/2004 ዓ.ም
ትርጉም፡- በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
“የጌታን ቤት በወርቅ ወይም በብር ባለማስጌጣቸው ከጌታ ዘንድ በሰዎች ላይ የሚመጣ አንዳች ቅጣት የለም”
የሰማዩ ቤተ መንግሥት (ለህጻናት)
15/04/2004 ዓ.ም
በእኅተ ፍሬስብሐት
በህንድ ሀገር ታከሻሊላ በተባለ ከተማ ጎንዶፓረስ የተባለ ንጉሥ ነበር፡፡ ይህ ንጉሥ በኢየሩሳሌም ስለ ነበረው የንጉሥ ሰሎሞን ቤተ መንግሥት ዝና እየሰማ እርሱም በሀገሩ ማሠራት ይፈልግ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ነጋዴዎች በየሀገሩ ሲጓዙ የታወቀ ግንበኛ እንዲያመጡለት አዘዛቸው፡፡
ይህንን መልእክት ከሰሙት ነጋዴዎች መካከል አንዱ ፋርስ ወደሚባለው ሀገር ተጓዘ ከዚያም ያ ነጋዴ አንዱ ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስን አገኘው፡፡ ነጋዴው ቶማስ ከኢየሩሳሌም እንደመጣ ሲሰማ የግንበኝነት ሙያ ይችል እንደሆነ ጠየቀው፤ ሐዋርያው ቶማስ ወደ ህንድ ሄዶ ማስተማር ይፈልግ ነበር፡፡ ስለዚህም ይህንን ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም ለመሔድ “በኢየሩሳሌም ሳለሁ ህንፃ በመገንባት እኖር ነበር፡፡” አለው፡፡
የምእመናን መሰባሰብ፤ የቅዳሴ ቀዳሚ ምስጢር
ታኅሣሥ 13/2004 ዓ.ም
ቅዳሴ የአንዲቷ ሰማያዊት ቤተ ክርስቲያን እውነተኛ ገጽ እንደሆነ ሁሉ የምእመናን መሰባሰብ ደግሞ የቅዳሴ የመጀመሪያ መሠረት ነው፡፡
በመሰባሰብ የፈጸመው የቅዳሴ ሥርዓታችን አስቀድሞም በቅዱሳን መላእክት ዓለም የነበረና በምድር ባለች መቅደሱም በምእመናን መሰባሰብ የሚፈጸም ነው፡፡ “እኔ በመካከላቸው እሆናለሁ” ብሎ ደስ የሚያሰኝ ዘላለማዊ ቃል ኪዳን የገባልን ጌታችን፣ “ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት” በማለት መሰባሰባችን ጸጋና ረድኤቱን እንድናገኝ ምክንያት መሆኑን ነግሮናል /ማቴ.18፥20/ በዚህ ርዕስም የጌታን ቃል በታላቅ ትጋት በፈጸመች ሰማያዊ ሥርዓቷን ከቅዱሳን መላእክት ዓለም ያገኘች፣ የምስጋና ሥርዓቷም በትውፊት ደርሶ ለቤተ ክርስቲየን መሠረት በሆነው በጠንታዊት /በሐዋርያት ዘመን/ ቤተ ክርስቲያን ለምእመናን መሰባሰብ ይሰጥ የነበረውን ትኩረትና ምስጢራዊ እይታ እንመለከታለን፡፡
ልዩ ዐውደ ጥናት
ለአንተ እንዲደረግልህ የምትፈልገውን ለሌላውም አድርግ
ደጉ ሰው (ለሕፃናት)
ታኅሣሥ 6/2004 ዓ.ም በእኅተ ፍሬስብሐት በአንድ ወቅት አንድ ሰው ከሚኖርበት ከተማ ተነሥቶ ለንግድ ወደ ሌላ ሀገር ጉዞ ጀመረ በጉዞው ወቅትም ሌቦች ከሚኖርበት ዋሻ አጠገብ ደረሰ፡፡ ሌቦቹም ሰውየውን ባዩት ጊዜ ከዋሻው ወጥተው ደበደቡት፡፡ የያዘውን ገንዘብ በሙሉ ቀሙት፡፡ ልብሱንም ገፈው በዚያው ጥለውት ሄዱ፡፡ የተጎዳው ሰው መንቀሳቀስ ስላቃተው በዚያ ቆየ፡፡ እየመሸ ሲሄድ አንድ ሰው በዚያ ሲያልፍ አየ፡፡ መንገደኛውን […]
በአታ ለማርያም
ታኅሣሥ 3/2004 ዓ.ም
ለደቡብ ትግራይ ማይጨው እና ደቡብ ምሥራቅ ትግራይ አህጉረ ስብከት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ካህናት ሥልጠና በመሰጠት ላይ ነው፡፡
ታኅሣሥ 5/2004 ዓ.ም
ሥልጠናው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በደቡብ ትግራይ ማይጨውና ደቡብ ምሥራቅ ትግራይ አህጉረ ስብከት እንዲሁም በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን በዋናው ማእከል ምክክር የተዘጋጀው ነው፡፡
ከታኅሣሥ 2 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ በደቡብ ትግራይ ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስና አዳራሽ በማይጨው ከተማ ከ 11 ወረዳዎች ለተወጣጡ 150 ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና ካህናት ሥልጠና እየተሰጠ መሆኑን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ አስታወቁ፡፡ ከታኅሣሥ 2 እስከ 6 ቀን 2004 ዓ.ም በሚቆየው በዚህ ሥልጠና የተገኙት የወረዳ ቤተ ክህነት ሊቃነ ካህናት፣ የአብነት መምህራን፣ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች መሆናቸውን ብፁዕነታቸው ገልጠዋል፡፡
የሎጥ ዘመን በዚች ቅድስት ሀገርና ሕዝብ ላይ አይደገምም!!!
ዘመኑ የሎጥ ዘመን ሆኖአል፡፡ በዚያ ዘመን የተነሡ የሰዶምና የገሞራ ሕዝቦች እግዚአብሔርን እያወቁ “እናይ ዘንድ ሥራውን ያፋጥን፤ እናውቃትም ዘንድ የእስራኤል ቅዱስ ምክር ይምጣ”(ኢሳ.5፡19)በማለት እግዚአብሔርን በመገዳደር ወንዱ ከወንዱ ጋር ሴቷም ከሴቷ ጋር በመዳራታቸው ምክንያት እግዚአብሔር ተቆጥቶ ከሰማይ እሳትና ዲንን በማውረድ ፈጽሞ ያጠፋቸው ሕዝቦች ናቸው፡፡(ዘፍ.18፡16-32፤19)እነርሱን ያጠፉአቸው ዘንድ የተላኩም መላእክት የእግዚአብሔር ቁጣ በእነዚህ ላይ ምን ያህል እንደነደደ ሲገልጡ “እኛ ይህቺን ስፍራ እናጠፋታለንና ጩኸታቸውም (ተግዳሮታቸውም) በእግዚአብሔር ፊት ትልቅ ሆኖአልና፤ እናጠፋት ዘንድ እግዚአብሔር ልኮናል”(ዘፍ.19፡13) ብለዋል፡፡ በዚህ ዘመንም እንደ ምዕራባውያኑ የእግዚአብሔርን ሕልውና ሽምጥጥ አድርገው የካዱ ወገኖች በሀገራችን ውስጥ ተነሥተዋል፡፡ እነዚህ ወገኖች ይህን ጸያፍ የሆነ ድርጊታቸውን ይፈጽሙ ዘንድ በገንዘብ ፍቅር በሰከሩ ግብረ ገብ በሌላቸው ባለ ሀብቶች የሚደገፉ ናቸው ፡፡ ነገር ግን ማንም እንዳይስት ይጠንቀቅ፡፡ እነዚህ ወገኖች ለገንዘብ በማጎብደድ በዚህ ደሃ የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በቡሃ ላይ ቆረቆር እንዲሉ ባሕሉና ሃይማኖቱ ፈጽሞ የማይፈቅደውን ከተፈጥሮ ሥርዐት የወጣውን ግብረ ሰዶማዊነትን ለገዛ ጥቅማቸው ሲሉ እንዲስፋፋ እየደከሙ ይገኛሉ፡፡