መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
የማይስማሙትን እንዲስማሙ አድርጎ ፈጠራቸው
ሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መልአክ
እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥረው ከሰባት እርስ በርሳቸው ከማይስማሙ ነገሮች ፈጥሮታል:: አራቱ ባሕርያት እግዚአብሔር በጥበቡ ካላስማማቸው በቀር መቼም የማይስማሙ ባላንጣዎች ናቸው፡፡ ምን አልባት ተስማምተው ከተገኙም በጽርሐ አርያም ባለው የእግዚአብሔር ማደሪያ ብቻ ሊሆን ይችላል፡፡ በዚያ ግን ባለጠጋው እግዚአብሔር የውኃ ጣራ፤ የእሳት ግድግዳ ያለው አዳራሽ ሠርቷል፤ ዓለም ከተፈጠረ እስከ ዛሬ ተስማምተው ይኖራሉ እንጂ አንዱ ባንዱ ላይ በክፋት ተነሳስቶ ውኃው እሳቱን አሙቆት፤ እሳቱም ውኃውን አጥፍቶት አያውቅም፡፡ ይህ ትዕግስታቸው በፍጥረት ሁሉ አንደበት ሠሪያቸውን እንዲመሰገን አድርጎታል::
በታች ባለው ምድራዊ ዓለምም ያለው ብቸኛው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሰው ልጅ ነውና እነዚህ እርስ በእርስ የማይስማሙ መስተጻርራን ነገሮች ተስማምተው የሚኖሩበት ዓለም ሆኗል፡፡ እሳት ከውኃ፤ ነፋስ ከመሬት ጋር የሚያጣብቃቸውን የፍቅር ሰንሰለት የሰው አዕምሮ ተመራምሮ ሊደርስበት የማይችል ታላቅ ምሥጢር ነው፡፡ ግን እንዴት ይሆናል? ነፋስ መሬትን ሳይጠርገው፤ መሬትም ነፋስን ገድቦ ይዞ መላወሻ መንቀሳቀሻ ሳያሳጣው፤ ተስማምተው እንዲኖሩ ያደረገ እግዚአብሔር ታላቅ ነው፡፡ ውኃና እሳት ተቻችለው አንድ ቤት ውስጥ መኖር ችለዋል፤ የጥንት ጠላትነታቸውን በጥበበ እግዚአብሔር አስታራቂነት እርግፍ አድርገው ትተው ከሞት በቀር ማንም ላይለያቸው በቃል ኪዳን ተሳስረዋል፡፡
“አትሮንስ” የመጻሕፍት ውይይት መርሐ ግብር ሊጀመር ነው
ጥቅምት 26 ቀን 2006 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ማኅበረ ቅዱሳን የቅዱሳት መጻሕፍት የንባብ ባሕልን ለማዳበር በየደረጃው ከሚሠራቸው ተግባራት በተጨማሪ “አትሮንስ” የተሰኘ በመጻሕፍት ላይ የሚደረግ የውይይት መርሐ ግብር ኅዳር 1 ቀን 2006 ዓ. ም. በማኅበሩ ኤዲቶሪያል ቦርድ አስተባባሪነት ይጀመራል፡፡
ንባብ ዕውቀትን ለማዳበር፤ አስተሳሰብን ለማስፋት፤ ሚዛናዊ ብያኔን ለመሥጠት፤ የአባቶችን ሕይወትና ትምህርት ለማወቅ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን የሚገልጸው የኤዲቶሪያል ቦርድ ክፍል፤ መንፈሳዊ መጻሕፍትን ማንበብ ዘላለማዊ ሕይወት ማግኛ መንገድን የሚጠርግና ጠቀሜታው የላቀ መሆኑን በመገንዘብ ተግባራዊ እንደሚደረግ አስታውቋል፡፡
ትኩረት ለፊደላት
ጥቅምት 25 ቀን 2006 ዓ.ም.
በዳዊት ደስታ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለሀገራችን በርካታ ነገሮችን አበርክታለች፡፡ ከዚህም ካበረከተቻቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ ኢትዮጵያ የራሷ ፊደል እንዲኖራት በማድረግ ነው፡፡ የቅርሳቅርስ ጥናት ሊቃውንትና ታሪክ ጸሐፊዎች እንደሚያረጋግጡት የአጻጻፍ ስልት በኢትዮጵያ የተጀመረው ከጌታ ልደት በፊት እንደነበር ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አጭር የታሪክ የሃይማኖትና የሥርዐት መጽሐፍ ይገልጻል፡፡ /ገጽ. 9-11/
በአክሱም ዘመነ መንግሥት የሳባውያንና የአግዓዝያን ፊደላት በኅብረት ይሠራባቸው ነበር፡፡ በአክሱም ዘመነ መንግሥት ግን የግእዝ ፊደልና የግእዝ ቋንቋ እያደገ ስለመጣ በክርስቲያን ነገሥታት በአክሱም ዘመነ መንግሥት በሐውልቶችና በሌላም መዛግብት የተጻፉ ጽሑፎች በግእዝ ፊደልና በግእዝ ቋንቋ ተጽፈው እናገኛለን፡፡ የጽሑፍ መሠረት የሆነው ፊደልና የጽሑፍ ስልት በደንብ የታወቀው የክርስትና ሃይማኖት ማለት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት በኢትዮጵያ መስፋፋት በጀመረበት ወቅት መሆኑ ግልጽ ነው፡፡
ማእከሉ Tewahedo/ተዋሕዶ /የተሰኘ የስልክ አፕ አዘጋጀ
ጥቅምት 22 ቀን 2006 ዓ.ም. በዳዊት ደስታ የማኅበረ ቅዱሳን የሰሜን አሜሪካ ማእከል የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ዘመኑን የዋጀ እንዲሆን Tewahedo /ተዋሕዶ የተሰኘ የስልክ አፕ/ በአይቲ ክፍል አዘጋጀ፡፡ በማእከሉ የተዘጋጀው አፕ የኢትዮጵያና የጎርጎሮሳዊያንን የዘመን አቆጣጠር አጣምሮ የያዘ ነው፡፡ የፈለጉትን ዓመት የበዓላት እና አጽዋማት ቀናት በቀላሉ ማየት ያስችላል፡፡ የየቀናቱን የቅዳሴ ምንባብ በመጽሐፈ ግጻዌ መሠረት ያሳያል፡፡ […]
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ አጠናቀቀ፡፡
ጉባኤው ከጥቅምት 11 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ላለፉት 10 ቀናት ተወያይቶ ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች አስመልክቶ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በተገኙበት በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡ የመግለጫውን ሙሉ ቃል እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡
የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር እንደሚካሔድ ተገለጸ
ጥቅምት 19 ቀን 2006 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ማኅበረ ቅዱሳን ሐዊረ ሕይወት /የሕይወት ጉዞ/ የተሠኘውንና ምእመናንን በማሳተፍ በተመረጡ ቅዱሳት መካናት የሚያካሒደውን መርሐ ግብር ታኅሣሥ 6 ቀን 2006 ዓ.ም. በደብረ ዘይት ደብረ መድኀኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን እንዳዘጋጀ የመርሐ ግብሩ አስተባባሪ ኮሚቴ ገለጸ፡፡
አቶ ግርማ ተሾመ የማኅበረ ቅዱሳን ምክትል ዋና ጸሐፊና የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዝግጅቱን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ በመርሐ ግብሩ ላይ ከ5000 በላይ ምእመናን ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅና የቲኬት ሽያጩንም በማሰራጨት ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ ምእመናን ቲኬቱን በማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል ጽ/ቤት፤ በማኅበሩ የንዋያተ ቅዱሳት ማከፋፈያና መሸጫ ሱቆች እንደሚያገኙ የተናገሩት አቶ ግርማ የቲኬት ሽያጩም ኅዳር 25 ቀን 2006 ዓ.ም. እንደሚጠናቀቅ አሳውቀዋል፡፡
ቅዱስ ሲኖዶስ ችግሮችን በውይይት መፍታት እንዳለበት ተገለጸ
ጥቅምት 12 ቀን 2006 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ቅዱስ ሲኖዶስ ችግሮችን በውይይትና በውይይት ብቻ በጋራ የመፍታት ባሕልን መደገፍና ማጎልበት እንደሚገባው ተገለጸ፡፡
በዛሬው ዕለት ጥቅምት 12 ቀን 2006 ዓ.ም. ጠዋት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ከመጀመሩ በፊት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በአሁኑ ጊዜ በጥልቀት፣ በማስተዋልና የሓላፊነት መንፈስ በተላበሰ ወኔ፣ አጥብቆ ሊወያይባቸውና ሊወስንባቸው፤ ከውሳኔ በኋላም ለተግባራዊነታቸው ሊረባረብባቸው የሚገቡ በርከት ያሉ ጉዳዮች እንዳሉ አመልክተዋል፡፡
የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ መክፈቻ በምሕላ ጸሎት ተጀመረ
ጥቅምት 11 ቀን 2006 ዓ.ም. በእንዳለ ደምስስ የጥቅምት 2006 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዛሬው እለት ጥቅምት 11 ቀን 2006 ዓ.ም. ከቀኑ ዐሥር ሰዓት ጀምሮ ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በምሕላ ጸሎት ተጀመረ፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ከጥቅምት 12 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ በሚያካሒደው […]
ለቅዱሳን ፓትርያርኮችና ለብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት መታሰቢያ ጸሎተ ፍትሐት ተደረገ
ጥቅምት 8 ቀን 2006 ዓ.ም. በእንዳለ ደምስስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ሲመሩ ለነበሩና ከዚህ ዓለም በሞት ለተለዩ ቅዱሳን ፓትርያርኮችና ሊቃነ ጳጳሳት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጥቅምት 10 ቀን 2006 ዓ.ም. የመታሰቢያ ጸሎተ ፍትሐትና ቅዳሴ ተካሔደ፡፡ በጸሎተ ፍትሐትና ቅደሴ ሥነ ሥርዓት ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም […]
መንፈሳዊ ኮሌጆች ወጥ የሆነ ሥርዓተ ትምህርት ሊኖራቸው እንደሚገባ ተጠቆመ
ጥቅምት 11 ቀን 2006 ዓ.ም.
በይብረሁ ይጥና
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥር የሚገኙት መንፈሳዊ ኮሌጆች አንድ ወጥ የሆነ ሥርዓተ ትምህርትና የትምህርት ጥራት ሊኖራቸው እንደሚገባ ተገለጠ፡፡
ከጥቅምት 4-11 ቀን 2006 ዓ.ም. በተካሄደው የ32ኛ መንፈሳዊ የሰበካ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ ላይ በተሳታፊዎች ተደጋግሞ እንደተነሣው የአቋም መግለጫው እንደሚያመለክተው የቅድስት ሥላሴ፣ የሰዋሰወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስና የቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጆች በርካታ ደቀ መዛሙርትን ድኅረ ምረቃ፣ በዲግሪ፣ ዲፕሎማና ሠርተፍኬት በማስተማር እንደሚያስመርቁ ተገልጿል፡፡