መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
መልካም አስተዳደር እና ቤተ ክርስቲያን
ውድ የዚህ ጽሑፍ አንባብያን! እንዴት ሰነበታችሁ? እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃድ ‹‹መልካም አስተዳደር እና ቤተ ክርስቲያን›› በሚል ርእስ ተከታታይ ጽሑፍ እናደርሳችኋለንና ተከታተሉን፡፡
የምእመናን ድርሻ በቤተ ክርስቲያን
ሰው ሲቀደስም ሲረክስም የሚኖረው በፈቃደ ሥጋ እና ፈቃደ ነፍስ መካከል ባለው የአሸናፊነትና ተሸናፊነት ትግል ነው፡፡የተቀደሰ ጾምን በተቀደሰ ሥርዓት ጹመን በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ እናገኝ ዘንድ በሥርዓቱ፣ በትሕትና፣ በንስሓና በተሰበረ ልቡና ሆነን ልንጾም ይገባል።
በጸሎትህ ጠብቅ!
ከቅዱሳን አበው የሆነ ውልደትህ
የጸሎታቸው መልስ ለእናት ለአባትህ
ክብርህ እጅግ በዛ ተወደደ ሥራህ
ፍጥረት ያስደሰተ የውልደትህ ዜና
ገና ሕፃን ሳለህ የጀመርክ ምሥጋና፡፡
ጽድቅን ተጎናጽፈህ ወንጌል ተጫምተሃል
በጉብዝናህ ወራት መስቀሉን ሽተሃል፡፡
እንደ ጠዋት ጤዛ በምትረግፈው ዓለም
ልብህ ሳይሸነፍ ለምቾት ሳትደክም
ከትዳርህ ይልቅ ምንኩስናን መርጠህ
ከጫጉላ ቤት ወጥተህ በረኃ ተገኘህ፡፡
‹‹ትነብር ውስተ ቤተ መቅደስ፤ በቤተ መቅደስ ውስጥ ትኖር ነበር›› ቅዱስ ያሬድ
ዓለም ሁሉ ተሰብስቦ ቢመዘን አንድ የራሷን ፀጉር የማያህል ደግ ፍጥረት፣ ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች፣ ንጽሕናዋንም ይሁን ቅድስናዋን ፍጥረት በአንደበቱ ተናግሮም ሆነ ጽፎ የማይጨርሰው፣ የአምላክ ማደሪያ፣ እመ አምላክ፣ እመ ብዙኃን፣ ሰዓሊተ ምሕረት፣ አቁራሪተ መዓት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት የከበረ በዓል ነው፡
በወቅታዊ ጉዳዮች ከቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
ቤተ ክርስቲያን ልዩ ልዩ ጸዋትወ መከራን፣ ሞትንና ስደትን፣ የመቀበል ታሪኳ ዛሬ የተጀመረ ባይሆንም በአሁኑ ጊዜ የሰው ልጅ ይሀረንና መሰል መተኪያ የሌለው ሕይወት የሚያጠፋና ሥጋት ላይ የሚጥሉ ተፈጥሮአዊ፣ ሰብአዊ ክብሩን የሚያራክስ ተግባራት እንዳይደገሙ ለማድረግ በሚጥርበት ዓለም ችግሩ በተለይም በሀገራችን እየተባባሰ መቀጠሉ እጅግ ያሳስበናል፡፡
ነቢዩ ኤልያስ
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች ! እንዴት አላችሁ? ባለፈው ትምህርታችን ስለ ቅዱሳን ነቢያት፣ እነርሱ ስለ ጾሙትና የነቢያት ጾም ተብሎ ስለሚጠራው ጾም በጥቂቱ ተመልክተናል፤ለዛሬ የምንነግራችሁ ደግሞ ስለ ከቅዱሳን ነቢያት አንዱ ስለሆነው ስለ ነቢዩ ኤልያስ ነው፡፡
ፍቅር ግን እርሱ ነው!
ፍቅር ግን ምንድነው? ብዬ ስጠይቀው
ሁሉም ሊያብራራልኝ ሊገልጸው አቃተው!
ፍቅር ግን እርሱ ነው
ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወሰብእ የሆነው
ራሱን በመስቀል ለእኛ ሲል የሰዋው!
‹‹የእግዚአብሔር ሰው›› (፩ኛሳሙ.፱፥፮)
መልእክተኛውም ሚክያስን ‹‹እነሆ ነቢያት ሁሉ በአንድ አፍ ሆነው ለንጉሡ መልካሙን ይናገራሉ፤ ቃልህም እንደ ቃላቸው እንዲሆን መልካም እንድትናገር እለምንሃለሁ›› ይለዋል፡፡ (፩ኛ ነገ.፳፪፥፲፫) ነቢዩ ግን ‹‹ሕያው እግዚአብሔርን! እግዚአብሔር የሚነግረኝን እርሱን እናገራለሁ›› አለው፡፡
በአርሲ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች በኦርቶዶክሳውያን ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በማስመልከት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የተሰጠ መግለጫ
በአርሲ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች በኦርቶዶክሳውያን ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት በጥብቅ እናወግዛለን፤ የጸጥታ ተቋማትም ጥቃቱን እንዲከላለሉ እንጠይቃለን።
‹‹ለብ ያልህ አትሁን!››
የሁላችንም ሕይወት ትኩስ፣ ለብ ያለና በራድ ተብለው በሚገለጹ ሦስት ሁነቶች ውስጥ የሚገኝ ነው። ቅዱስ ዮሐንስ እነዚህን ሦስቱን የገለጸው ‹‹በራድ ወይም ትኩስ እንዳይደለህ ሥራህን አውቃለሁ፤ በራድ ወይም ትኩስ ብትሆንስ፣ መልካም ነበር፤ እንዲሁ ለብ ስላልህ፥ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው›› በማለት ነበር፡፡ (ራእ.፫፥፲፭-፲፮)