ማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ፕሮግራም ቢሮ ያከናውናቸውን ተግባራት አስታወቀ።

በይብረሁ ይጥና

ሥራዎቹንም የሚያሳይ ዓውደ ጥናት በኢትዮጵያ የስብሰባ ማእከል እንደሚካሔድ ተገልጧል

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ  መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን በትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ዋና ክፍል የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ፕሮግራም ማስተባበሪያ ቢሮ እስካሁን ያከናወናቸውንና በቀጣይ ሊሠራ ያቀዳቸውን ተግባራት አስታወቀ፡፡
 
የፕሮግራሙ ማስተባበሪያ ቢሮ ሓላፊ አቶ ዳንኤል ተስፋዬ እንዳስታ ወቁት በ2001 እና 2002 ዓ.ም ፕሮግራሙን ለምእመናን የማስተዋወቅና የመቅረጽ ሥራ ተሠርቶ በተወሰነ ደረጃ ወደ ትግበራ ተገብቷል፡፡

በ2003 ዓ.ም በጠቅላይ ቤተክህነት ለትምህርትና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ክፍል የተነደፈውን ፕሮግራም እንዲያውቀው ተደርጓል፡፡ መምሪያውም ለፕሮግራሙ ማስፈጸሚያ የሚሆን አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ቃል ተገብቷል፡፡

እንደዚሁም ከጠቅላይ ቤተክህነት ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ መምሪያ ጋር በመሆን ፕሮግራሙ ተግባራዊ ከሚደረግባቸው ሃያ ሀገረ ስብከቶች ለተውጣጡ ሥራ አስኪያጆችና ሰባክያነ ወንጌል በጠቅላይ ቤተክህነት አዳራሽ ፕሮግራሙን የማስተዋወቅ ሥራ ከተሠራ በኋላ ለተግባራዊነቱ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ደብዳቤ ተበትኗል ሲሉ አመልክተዋል፡፡

ፕሮግራሙ በዋናነት የሚያተኩረው ስብከተ ወንጌልን ለምእመናን ማዳረስ ሲሆን የንድፈ አሳቡ መነሻ ደግሞ በተለይ በጠረፋማና ገጠራማ አካባቢ ለሚገኙ ምእመናን ጉባኤ ማካሔድና ሰባኬ ወንጌል ከመመደብ ጀምሮ ለአካባቢው ካህናትና የሰንበት ትምህርት ቤት አመራር አባላትም የአቅም ግንባታ ሥልጠና መስጠት ነው፡፡

ፕሮግራሙ በመላው ሀገሪቱ ከሚገኙ ዐርባ አምስት ሀገረ ስብከቶች መካከል ችግሩ ይበልጥ ይከፋል ተብሎ በታመ ነባቸው ሃያ ሀገረ ስብከቶች መሆኑን አቶ ዳንኤል  ጠቁመው፣ በኦሮሚያና ደቡብ ክልል በሚገኙ ጠረፋማና ገጠር አካባቢዎች ልዩ ትኩረት ይደረጋል ብለዋል፡፡

የፕሮግራሙ ማስተባበሪያ ቢሮው በ2003 ዓ.ም እሠራቸዋለሁ ብሎ ካቀዳቸው ዕቅዶች መካከል፤ ዐሥር ሐዋርያዊ ጉዞ በማድረግ፣ ሃያ የሕዝብ ጉባኤያትን ማካሔድ፣ በተለያዩ ቋንቋዎች ዐሥራ ሁለት የስብከame=”Medium List 2 Accent 5″/> » አለው፡፡

ሊቀ ነቢያት ሙሴ ከእስራኤል ሽማገሌዎች ጋር በኮሬብ በነበረው ዐለት ያደረገው ስብሰባ በሐዲስ ዘመን ከተሰበሰቡት ሲኖዶሶች /ጉባኤዎች/ ጋር ይመሳሰላል፡፡

ሙሴ በሌላ ጊዜ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ከእስራኤል ሽማግሌዎችና ከካህናቱ ጋር ወደ ደብረ ሲና ለመውጣት ያደረገው ስብሰባ ከሲኖዶስ ጋር የሚመሳሰል ነው፤/ዘፀ.19፡1-25/፡፡ በተለይም የእግዚአብሔርን ክብር ያዩ ዘንድ ሙሴና የእስራኤል ሽማግሌዎች፣ ከካህናቱ ጋር ወደ ደብረ ሲና ወጥተው በሩቅ ቆመው ለእግዚአብሔር ክብር ስግደት በማቅረብ የተሰበሰቡት ስብሰባ ሲኖዶስን የሚመስል ነው እንላለን፡፡ /ዘፀ.24111/፡፡

በሌላ በኩል የእስራኤል ልጆች ወደ ምድረ ከነዓን ለመግባት በሲና ምድረ በዳ በሚጓዙበት ወቅት የሚበላ ዳቦና የሚጠጣ ውኃ ሲያጡ ወደ ሙሴ ይጮኹ ነበር፡፡ ሙሴም የሕዝቡን ችግር ለእግዚአብሔር እያሰማ ሕዝቡ ማግኘት የፈለጉትን ያሰጣቸው ነበር፡፡ በዚሁ መሠረት አንድ ቀን የእስራኤል ልጆች እጅግ ጎምጅተው «የምንበላው ሥጋ ማን ይሰጠና? በግብፅ ሳለን ያለዋጋ ዓሣውንም፣ ዱባውንም፣ በጢሁንም፣ ነጭ ሽንኩርቱንም፣ ቀይ ሽንኩርቱንም እንደ ልብ እንበላ ነበር፡፡ አሁን ግን ሰውነታችን ደረቀች፣ ዐይናችንም ከዚህ መና በቀር የሚያየው የለም» ብለው አጉረመረሙ፡፡


በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር ሙሴን ጠርቶ ከሕዝቡ ሰባ ሽማግሌዎችን የሕዝቡ አለቆችና ሸማግሌዎች ይሆኑ ዘንድ መርጦ ወደ መገናኛው ድንኳን እንዲያቀርባቸው አዘዘው፡፡ ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘው ሰባዎቹን ሰዎች ከሕዝቡ መርጦ ወደ ማደሪያው ድንኳን አቀረባቸው፡፡ እግዚአብሔርም ለሙሴ ከሰጠው መንፈስ ወስዶ በእነርሱ አሳደረባቸው፡፡ መንፈስም
/መንፈስ ቅዱስ/ በሰባው ሰዎች ላይ ባደረ ጊዜ ትንቢት ተናገሩ፡፡ በዚያው ወቅትም ከሰባው ጋር ተመርጠው ወደ ድንኳኑ ሳይመጡ በሕዝቡ ሰፈር የቀሩ ኤልዳድና ሞዳድ የተባሉ ሰዎች ነበሩ፡፡ መንፈስም ባሉበት ወረደባቸው፡፡ እነርሱም ትንቢትን ተናገሩ፡፡ ከዚያ በኋላ ከእነዚህ ሰባ ሁለት ሽማግሌዎች ጋር ሙሴ የሕዝቡን ችግር እንዲሸከም ታዘዘ፡፡ ከዚያም እግዚአብሔር ከእነዚህ ሰባ ሁለት ሽማግሌዎች /72 ሊቃናት/ ፊት በሙሴ አማካይነት ለእስራኤል ልጆች ሥጋ አዘነበላቸው፤/ዘኁል.11፥115/፡፡

በመሆኑም የእነዚያ ሰባ ሁለት ሽማግሌዎችና የሙሴ በማደሪያው ድንኳን መሰብሰብና የመንፈስ ስጦታን መቀበል በዘመነ ሐዲስ ከተደረጉት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤዎች ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡ ኢያሱም ከሙሴ ዕረፍት በኋላ ሕዝበ እስራኤልን ለመምራት እንዲችል በእግዚአብሔር ትእዛዝ ሙሴ ኢያሱን በማኅበሩ ሁሉ ፊት /በጉባኤ ፊት/ በአንብሮተ እድ እንደሾመው መጽሐፍ ይነግረናል፤ /ዘኁል.27፥1523/፡፡ ስለሆነም የኢያሱ በጉባኤው ፊት መሾም ሰባቱን ዲያቆናት በአንብሮተ እድ ከሾሙት ከሐዋርያት ጉባኤ ጋር የሚመሳሰል ነው፤ /ሐዋ.6፥16/፡፡

እንደዚሁም በመጽሐፈ ነገሥት ካልዕ በምዕራፍ 2፥12 እና በምዕራፍ 4፥30 ላይ እንደተገለጸው፤ ደቂቀ ነቢያት በነቢዩ በኤልሳዕ ፊት ያደረጉት ስብሰባ ከቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡ ስለዚህ በዘመነ ሐዲስ ቅዱሳን ሐዋርያት ካደረጉት የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በፊት በዘመነ ብሉይ በሕዝበ እስራኤል መካከል የተከሰተውን ችግር ለማስወገድና ሕዝበ እስራኤንም በጉባኤ ውሳኔ ለመምራት ቅዱስ ሲኖዶስን የመሰሉ ስብሰባዎች መደረጋቸውን በአጭሩ ለማስረዳት ተሞክሮአል፡፡

ሲኖዶስ ዘቅዱሳን ሐዋርያት

የቤተክርስቲያን ታሪክ እንደሚያስረዳን የክርስቶስን ቤተክርስቲያን በቅዱስ ሲኖዶስ መምራት የጀመሩት ቅዱሳን ሐዋርያት ናቸው፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያት ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን በሥምረት ለመምራት በዘመናቸው የተለያዩ ጉባኤዎችን እንዳደረጉ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፡፡ ይኸውም በአስቆሮታዊው ይሁዳ ምትክ ሌላ ሐዋርያ ለመምረጥ ያደረጉት ስብሰባ ነው፡፡ ይኸውም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞተና ከተቀበረ በኋላ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላ ቅዱስ ሉቃስ እንደመሰከረው ለደቀመዛሙርቱ አርባ ቀን እየተገለጸላቸው፣ ስለእግዚአብሔር መንግሥትም እየነገራቸው /እያስተማራቸው/ በብዙም ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖና ከሙታን ተለይቶ መነሣቱን ለእነርሱ እየታያቸው ቆየ /ሐዋ.1፥1-4/፡፡

ስለ እርሱ የተጻፉትንም መጻሕፍት ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው፡፡ እንዲህም አላቸው፣ «ክርስቶስ መከራ ይቀበላል፣ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ይነሣል፣ በስሙም ንስሐና ኃጢአት ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ ለአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል» ተብሎ እንዲሁ ተጽፎአል፡፡ እናንተም ስለዚህ ምስክሮቼ ናችሁ፡፡ እነሆም «አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፣ እናንተ ግን ከላይ ኃይልን እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ ብሎ አዘዛቸው፡፡ ከዚያም ወደ ቢታንያ ወደ ደብረ ዘይት አወጣቸው፣ እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው፣ ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ፣ ወደ ሰማይም ዐረገ» /ሉቃ.24፥41-53/፡፡ እነርሱም ጌታ ወዳረገበት ወደ ሰማይ ትኩር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ እነሆ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች /ሁለት መላእክት/ በአጠገባቸው ቆሙ፡፡ ደግሞም እንዲህ አሉአቸው «እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ ወደ ሰማይ ትኩር ብላችሁ እየተመለከታችሁ ስለምን ቆማችሁ? እነሆ ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁ እንዲሁ ይመጣል» ሲሉ ነገሩአቸው፡፡ /ሐዋ.1፥6-11/፡፡

ሐዋርያትም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ከደብረ ዘይት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፡፡ ከዚያም ዘወትር እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እያወደሱ /እየባረኩ/ በመቅደስ /በጽርሐ ጽዮን/ ኖሩ /ሉቃ.24፥50/፡፡ በአንድነት ተሰብስበው ሳሉ በአጠቃላይ መቶ ሃያ ሰዎች ያህል ባሉበት ቅዱስ ጴጥሮስ ተነሥቶ በይሁዳ ቦታ ሌላ ሰው መተካት እንዳለበት ንግግር አደረገ፡፡ «ወንድሞች ፥ሆይ፣ ኢየሱስን ለያዙት መሪ ስለሆናቸው ስለ ይሁዳ መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ በዳዊት አፍ የተናገረው ይፈጸም ዘንድ የተገባ ሆነ፤ እርሱም ከእኛ ጋር ተቆጥሮ ነበርና፣ ለዚህም ሐዋርያዊ አገልግሎት ታድሎ ነበርና» ብሎ በመናገር ስለ አስቆሮቱ ሰው ስለ ይሁዳ ዐመፅና አሟሟት ገለጻ አደረገ፡፡ ከዚያም ይሁዳን ስለሚተካው ሰው አስመልክቶ «ከዮሐንስ ጥምቀት ጀምሮ ከእኛ ዘንድ እስካረገበት ቀን ድረስ ጌታ ኢየሱስ በእኛ መካከል በገባበትና በወጣበት ዘመን ሁሉ እኛ ጋር አብረው ከነበሩት ሰዎች፣ ከእነዚህ አንዱ ከእኛ ጋር የትንሣ ኤው ምስክር ይሆን ዘንድ ይገባል» ብሎ ገለጸ፡፡

ወዲያውም በጉባኤው ስምምነት መሠረት የመቶ ሃያው ማኅበር አባላት ከነበሩት መካከል በርያስ የተባለውን ዮሴፍንና ማትያስን፣ሁለቱን በመካከል አቆሙአቸው፡፡ ስለ እነርሱም ሲጸልዩ፤ «የሁሉን ልብ የምታውቅ አንተ ጌታ ሆይ፣ ይሁዳ ወደ ገዛ ራሱ ይሔድ ዘንድ በተዋት በዚህች አገልግሎትና ሐዋርያነት ቦታን እንዲቀበል የመረጥኸውን ከእነዚህ ከሁለቱ አንዱን ሹመው» ብለው ጸለዩ፡፡ ቀጥሎም ዕጣ ተጣጣሉላቸው፤ ዕጣውም ለማትያስ ወደቀ /ወጣ/፡፡ እርሱም ዐሥራ አንዱ ሐዋርያት ጋር ተቆጠረ» /ሐዋ.1፥15-26/፡፡

ማትያስን መርጠው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እንዲሾመው ከጸለዩ በኋላ ቁ ሩ ከሰብዐ ሁለቱ አርድእት ውስጥ የነበረው ረድእ ማትያስ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ተሹሞ ከቀሩት ሐዋርያት ጋር ገብቶ ተቆጠረ፡፡ በዚህ ሁኔታ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው ከአርያም /ከሰማይ/ የሚላክላቸውን ኃይል ማለት ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ደጅ እየጠኑና እየተጠባበቁ በጽርሐ ጽዮን ተሰብስበው እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ሰነበቱ፡፡ በዓለ ሃምሳም የተባለው ቀን በደረሰ ጊዜ ጌታ ባረገ በዐሥረኛው ቀን ሁሉም በአንድነት አብረው እየጸለዩ ሳለ ድንገት እንደሚነጥቅ አውሎ ነፋስ ከሰማይ ወደ እነርሱ ድምፅ መጣ፡፡ ተቀምጠው የነበሩበትንም ሁሉ ሞላው፤ እንደ እሳትም የተከፋፈሉ ልሳኖች /የእሳት ላንቃ/ የመሰሉ ታዩአቸው፤ በእያንዳንዳቸውም ላይ ተቀመጠባቸው፣ መንፈስ ቅዱስም ይናገሩ ዘንድ እንደሰጣቸው በልዩ ልዩ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር፤ /ሐዋ.2፥1-5/፡፡

በዚህ ጊዜ ጌታችን ከትንሣ ኤው በፊት «እኔ በአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ /ጰራቅሊጦስ/ ከአብ የሚወጣ /ዘይሠርጽ/ የጽድቅ /የእውነት/ መንፈስ በመጣ ጊዜ ስለ እኔ ይመሰክራል፣ እናንተም ደግሞ ከመጀመሪያ ጀምሮ ከእኔ ጋር ኖራችኋልና ትመሰክራላችሁ» ብሎ የተናገረው ተስፋ ተፈጸመ፡፡ ደግሞም ወደ ሰማይ በሚያር ግበት ወቅት «እነሆ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፣ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ» ሲል የሰጠው ሰማያዊ ተስፋ ተፈጸመ፤ /ሉቃ.24፥49፤ሐዋ.2፥43/፡፡

ከዚህ በላይ እንዳየነው ከበዓለ ሃምሳ ዋዜማ ጀምሮ በኢየሩሳሌም በጽርሐ ጽዮን የተካሔደው የመጀመሪያው የሐዋርያትና የሰብዓ አርድእት ጉባኤ እጅግ በጣም ታላቅ ጉባኤ ስለነበረ የመጀመሪያው የሐዋርያት ሲኖዶስ ሊባል ይገባዋል፡፡ ምክንያቱም፦

1. ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም የነበረችበት ጉባኤ በመሆኑ፤
2. ቅዱስ ማትያስን የመረጠና የሾመጉባኤ በመሆኑ፤
3. ለሐዋርያትና ከእነሱ ጋር በጸሎት ተሰብስበው ለነበሩት ሁሉ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ የወረደበት ጉባኤ በመሆኑ፤
4. በዚያው ቀን የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ በመውረዱ ምክንያት በሐዋር ያት ስብከት ሦስት ሺሕ የሚያህል ሕዝብ በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ የቤተክርስቲያን አባል የሆነበት ቀን በመሆኑ ጉባኤው የቤተክርስቲያን የመጀመሪያ ሲኖዶስ ተብሎ ሊጠራ ይገባል፡፡ በመሆኑም  ቤተክርስቲያን ታሪክ የቅዱስ ሲኖዶስ ታሪካዊ አመሠራረት ከዚህ ቀዳሚው ጉባኤ መሆኑ የሚያከራክር አይደለም፡፡ በሌላ መንገድም በቤተክርስቲያን ታሪክ እንደተመዘገበው ከሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ በየጊዜው በተለያዩ ቦታና ዘመን የተደረጉ የአህጉረ ስብከት /Regionsl or local/ ሲኖዶሶችና በዓለም አቀፍ ደረጃ የተደረጉ ሲኖዶሶች መሠረታቸው የኢየሩሳሌሙ የመጀመሪያው የሐዋርያት ጉባኤ ነው ቢባል እርግጥ ነው፡፡

ሁለተኛው የሐዋርያት ሲኖዶስ

ሁለተኛው የሐዋርያት ሲኖዶስ ተብሎ ሊጠራ የሚገባው ጉባኤ፤ ራሳቸው ሐዋርያት ተሰብስበው የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን በአንብሮተ እድየሾሙት ዐቢይ ሲኖዶስ ተደርጎ እንደነበረ መጽሐፍ ያረጋግጥልናል፡፡ ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት /ደቀመዛሙርት/ ምእመናንን በሙሉ ጠርተው፤ «እኛ የእግዚአብሔርን ቃል /ወንጌልን/ ትተን ማዕድን እናገለግል ዘንድ የሚገባ ነገር አይደለም፡፡ ወንድሞች ሆይ በመልካም የተመሰከረላቸውን፣ መንፈስ ቅዱስና ጥበብም የሞላባቸውን ሰባት ሰዎች ከእናንተ ምረጡ፣ ለዚህም ጉዳይ እንሾማቸዋለን፣ እኛ ግን ለጸሎትና ቃሉን ለማገልገል እንተጋለን» ብለው ገለጹላቸው፡፡ ይህም ቃል /ንግግር/ ሕዝቡን ሁሉ ደስ አሰኛቸው፡፡ ስለዚህም እምነትና መንፈስ ቅዱስም የመላበትን ሰው እስጢፋኖስን፣ ፊልጶስንም ጵሮኮ ሮስንም፣ ኑቃሮናንም ጰርሜናንም መረጡ፡፡ በሐዋርያትም ፊት አቆሙአቸው ሐዋርያት ከጸለዩ በኋላ እጃቸውን ጫኑባቸው /ሐዋ. 6፥1-7/፡፡

ከላይ እንደተገለጸው ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ከአርድእትና ከምእመናኑ ጋር ተሰብስበው ከተወያዩ በኋላ፤ ሐዋርያት በወሰኑት ውሳኔ ሕዝቡ በሙሉ ተደስተው ሰባቱን የቤተክርስቲያን አገልጋዮች መርጠው ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አቅርበው የሾሙት ጉባኤ በመሆኑም ጉባኤው ከወሰነው ታላቅ ቁም ነገር የተነሣ  «ሲኖዶስ» ተብሎ ሊጠራ ይችላል፡፡ ነገር ግን እንደሚታወቀው በቤተ ክርቲያን ታሪክ መሠረት በተለምዶ የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ጉባኤ ወይም የመጀመሪያው ሲኖዶስ ተብሎ የሚጠራው በኢየሩሳሌም 50/51 ዓ.ም የተደረገው ጉባኤ ነው፡፡

ሦስተኛው የሐዋርያት ሲኖዶስ

ይህ በኢየሩሳሌም የተደረገው ሦስተኛው የሐዋርያት ጉባኤ ቅዱስ ሲኖዶስ ተብሎ ሊጠራ ይገባል፡፡ ነገር ግን በተለምዶ የመጀመሪያው የሐዋርያት ጉባኤ /ሲኖዶስ/ እየተባለ መጠራቱ ሁሉም የሚያውቀው ነው፡፡ ጉባኤው ሊደረግ የተፈለገበት ዋና ምክንያት የሚከተለው ነው፡፡ በሐዋርያት ዘመን በአንጾኪያ ከተማ በነበረችው ቤተክርስቲያን ነቢያትና መምህራን ነበሩ፡፡ እነርሱም በርናባስ፣ ኔጌር የተባለው ስምዖን፣ የቀሬናው ተወላጅ ሉክዮስ፣ የአራተኛው ክፍል ገዥ የነበረው የሄሮድስ ባለሟል ምናሔና ሳውል እነዚህ ሁሉ ጌታን እያመለኩና እየጾሙ ሳለ መንፈስ ቅዱስ፤ «በርናባስንና ሳውልን ለጠ ራኋቸው ሥራ ለዩልኝ፤ ፍልጥዎሙ ሊተ ለበርናባስ ወለሳውል ለገብር ዘፈቀድክዎሙ» አላቸወ፡፡ እነርሱም መንፈስ ቅዱስ እንደነገራቸው አደረጉ፡፡ ከጾሙ ከጸለዩና እጃቸውንም ከጫኑ በኋላ አሰናበቱአቸው   /ሐዋ.13፥1-3/፡፡

ከዚያም ጳውሎስ በርናባስና ማርቆስ ከሌሎቹ ጋር ወደ ቦታው ሁሉ እየዞሩ ወንጌልን ሰበኩ፡፡ በየሰንበቱም በአይሁድ ምኩራብ እየተገኙ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነትና ስለ ትንሣ ኤው ይሰብኩ ነበር፡፡ እንደዚሁም በልስጥራ፣ በደርቤን፣ በጲስድያ፣ በጵንፍልያ፣ በጴርጋሞን፣ በጵርሄንም የእግዚአብሔርን ቃል /ወንጌልን/ እየሰበኩ ሕዝቡን ያጽናኑ ነበር፡፡ አንጾኪያም በደረሱ ጊዜ ቤተክርስቲያንን /ምእመናንን/ ሰብስበው እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ያደረገውን ሁሉ ለአሕዛብም የሃይማኖት ደጅ አንደተከፈተላቸው ተናገሩ፡፡
ነገር ግን በዚያን ጊዜ አንዳንዶች ከይሁዳ ሀገር ወደ አንጾኪያና ወደ ሌሎቹ አውራጃዎች ወረዱና «እንደሙሴ ሥርዓት ካልተገረዛችሁ ትድኑ ዘንድ አትችሉም» እያሉ ወንድሞችን /ምእመናንን/ ያስተምሩ ጀመር፡፡ በዚያን ጊዜ በእነዚያ ሰዎች በጳውሎስና በበርናባስ መካከል ብዙ ጠብናክርክር ተፈጠረ፡፡ ጠቡና ክርክሩ እያየለ በሔደ ጊዜ ጳውሎስ፣ በርናበስና ከእርሱ ጋር የነበሩ የወንጌል አገልጋዮች ተነጋግረው ወደ ሐዋርያት ለመሔድ ወሰኑ፡፡ ወደ ኢየሩሳሌምም በደረሱጊዜ ቤተክርስቲያን /ምእመናን/ ሐዋርያትና ቀሳውስት /Aposstles and the elders/ ተቀበሉአቸው፡፡ እነ ጳውሎስም በዞሩባቸው አህጉረ ስብከት ሁሉ ያደረጉትን /የፈጸሙትን/የወንጌል አገልግሎትና የገጠማቸውን ችግር ሁሉ በዝርዝር ሪፖርት አቀረቡ፡፡ በዚያን ጊዜ በጌታ ካመኑት ከፈሪሳውያን ወገን የሆኑት ሰዎች ተነሥተው «ትገርዙአቸው ዘንድና የሙሴንሕግ እንዲጠብቁ ታዝዙአቸው ዘንድ ይገባል» ብለው ለሐዋርያት ተናገሩ፡፡ እነሆም በዚያን ጊዜ ሐዋርያትናቀሳውስት /Apostles and the elders/ ለመመካከርና ለመወሰን በአንድነት ተሰበሰቡ፡፡ የዚህ ዐቢይ ሲኖዶስ ሰብሳቢ /ሊቀመንበርም/ ቅዱስ ያዕቆብ ኤጲስ ቆጶስ ዘኢየሩሳሌም እንደነበር በቤተክርስቲያን ታሪክ ተገልጿል፡፡ በጉባኤውም በቀረበው ጉዳይ ላይ ቅዱስ ጴጥሮስ የመጀመሪያውን ንግግር አደረገ፡፡ ከቅዱስ ጴጥሮስ ንግግር በኋላም ጳውሎስና በርናባስ ተነሥተው እግዚአብሔር በእጃቸው በአሕዛብ መካከል ያደረገውን ምልክትና ድንቅ ነገር ሁሉ ለሲኖዶሱ ተረኩ፡፡ ከዚያም የጌታ ወንድም እየተባለ የሚጠራው የኢየሩሳሌም ኤጲስ ቆጶስና የጉባኤው ሰብሳቢ ቅዱስ ያዕቆብ ንግግር አደረገ፡፡ ከቅዱስ ያዕቆብ ንግግር በኋላ
ሐዋርያትና ቀሳውስት /Apostles and the elders/ ከቤተክርስቲያኑ /ምእመናኑ/ሁሉ ጋር ከእነርሱ የተመረጡትን ሰዎች ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር ወደ አንጾኪያ ይልኩ ዘንድ ተስማሙ፡፡ ከእነ ጳውሎስ ጋር እንዲሔዱ የተመረጡትም በርስያን የተባለው ይሁዳናሲላስ ነበሩ፡፡ የጉባኤውም አባላት በጉባኤ የተወሰነውን ውሳኔ ጽፈው በተመረጡት ወንድሞች እጅ ላኩ፡፡ መልእክተኞቹም ተሰናብተው ወረዱ፤ ሕዝቡንም ሰብስበው ከሐርያት ጉባኤ የተላከውን ደብዳቤ ሰጡአቸው፡፡ ባነበቡትም ጊዜ ከምክሩ የተነሣ  ደስ አላቸው፡፡ ይሁዳና ሲላስም ደግሞ ነቢያት ነበሩና ወንድሞችን በብዙ ቃል መክረው አጽናኑአቸው፡፡ አያሌ ቀንም ከእነርሱ ጋር ከተቀመጡ በኋላ ከወንድሞቻቸው በሰላም ተሰና ብተው ወደ ሐዋርያት ተመለሱ፡፡ ቤተክርስቲያን ሐዋርያዊትና ሲኖዶሳዊት ለመሆንዋ ተደጋግሞየተነገረ ነው፡፡ በመንፈስ ቅዱስ የተመሩ ቅዱሳን ሐዋርያት ቤተክርስቲያንን በስብከተ ወንጌል ስለአሰባሰቡና ስለአጠናከሩ ቤተክርስቲያን በሲኖዶስ እየተመራች ከዚህ ዘመን በመድረስዋ ሲኖዶሳዊት /ጉባኤያዊት/ እየተባለች ትጠራለች፡፡

ከቅዱሳን ሐዋርያት ቀጥለው የተነሡት አባቶችም ቤተክርስቲያንን በሚመሩበት ወቅት፡-
ሀ. የቤተክርስቲያንን ቅዱሳት መጻሕፍት ከመናፍቃን መጻሕፍት ለመለየትና ቁጥራቸውን
    በቀኖና /በሕግ/ ለመወሰን፤
ለ. ሥርዐተ ቅዳሴንና ሥርዐተ ጸሎትን በቀኖና /በሕግ/ ለመመደብ፤
ሐ. አጽዋማትንና በዓላትንም ለመወሰን የሲኖዶስ ስብሰባ በማድረግ ከላይ የተዘረዘሩትን ሁሉ ወስነዋል፡፡ በሌላ በኩልም ከመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በየጊዜው መናፍቃን /ሐራ ጥቃዎች/ በተነሡ ጊዜ ቅዱሳን የቤተክርስቲያን አባቶች ርትዕት፣ ስብሕት /ኦርቶዶክስ/ ሃይማኖትን ለመጠበቅ ሐራጥቃዎችን በቀኖናዋ ውግዘት ለማስወገድ በሲኖዶስ እየተሰበሰቡ ይወስኑ ነበር፡፡ በዚህ መሠረት ከሦስተኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ጀምሮ በየሀገሩ የአካባቢ ሲኖዶሶች /Regional or Local synods/ ተደርገዋል፡፡ ከተደረጉት ሲኖዶሶችም ለአብነት ጥቂቶቹን ቀጥለን እንመለከታለን

1.    በ257ዓ.ም በካርቴጅ የተደረገው ሲኖዶስ፡- በዚህ የአካባቢ /regional/ ሲኖዶስ ሰማንያ አራት ኤጲስ ቆጶሳት ተሳትፈዋል፡፡ የሲኖዶሱ ሰብሳቢ ቅዱስ ሲፕሪያኖስ ነበር፡፡ በዚህ ጉባኤ ሥርዓተ ጥምቀትንና መናፍቃንን፣ ቅዱሳት መጻሕፍትንና የኤጲስ ቆጶሳትን ሥልጣን የተመለከቱ ቀኖናዎች ተወስነዋል፡፡
2.    268 – 270 ዓ.ም በተከታታይ በአንጾኪያ ሲኖዶስ ተደርጎአል፡፡ በዚህ ሲኖዶስ ዐሥራ አራት ኤጲስ ቆጶሳት ተሰብስበው በምስጢረ ሥጋዌ የኅድረትንና የፅምረትን /ምንታዌ አካላትን/ ትምህርት ማስፋፋት የሞከረውን ኤጲስ ቆጶስ ጳውሎስ ሳምሳጢን መክረው አልመለስ ስላለ አውግዘው ከቤተክርስቲያን ለይተውታል፡፡
3.    በዚሁ ዓይነት በአንካራ በ314 ዓ.ም ፣በጋንግራ 365 ዓ.ም፣ በሳርዲካ በ343ዓ.ም፣ በአንጾኪያ በድጋሚ በ341 ዓ.ም፤ በላኦዶቂያ በ334 እና በ381 ዓ.ም የተጠራው ሲኖዶስ ስድሣ  ቀኖናዎችን ዐውጆአል፡፡ እንደዚሁም በድጋሚ በካርቴጅ በ419 ዓ.ም የተሰበሰበው ሲኖዶስ )138 ቀኖናዎችን ዐውጆአል፡፡ ይህ ሲኖዶስ «የአፍሪካ ኤጲስ ቆጶሳት ሲኖዶስ» በሚል መጠሪያ ይታወቃል፡፡
በአጠቃላይ ከሐዋርያት በኋላ የተነሡ ሐዋርያውያነ አበው /Apostolic Fatheres/ የቤተክርስቲያንን አስተዳደርና የቤተክርስቲያንን ችግር በሲኖዶስ እየተሰበሰቡ በመመርመርና አስፈላጊውንም በመወሰን ቤተክርስቲያንን መርተዋል፡፡ ያውም ከሰባ ዓ.ም ጀምሮ እስከ 313 ዓ.ም ድረስ የነበረው ጊዜ አሕዛብ በቁር የበዙ በትና በመንግሥት አስተዳደርም አጠቃላይ ሥልጣን ግን የጨበጡበት ዘመን ስለነበረ፤ በዚህ ዘመን ከፀረ እግዚአብሔርና ከፀረ ክርስትና ኃይሎች ጋር በመጋደል በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች ስለ ሀልዎተ እግዚአ ብሔርና ኦርቶዶክሳዊ ሃይማኖታቸው መሥዋዕት ሆነው የተሰውበት ዘመን ነበር፡፡ በመሆኑም ዘመኑ ዘመነ ሰማዕታት እየተባለ ይጠራል፡፡

ከቅዱሳን ሐዋርያት ቀጥለው የተነሡት አባቶችም ቤተክርስቲያንን በሚመሩበት ወቅት፡-
ሀ. የቤተክርስቲያንን ቅዱሳት መጻሕፍት ከመናፍቃን መጻሕፍት ለመለየትና ቁጥራቸውን
    በቀኖና /በሕግ/ ለመወሰን፤
ለ. ሥርዐተ ቅዳሴንና ሥርዐተ ጸሎትን በቀኖና /በሕግ/ ለመመደብ፤
ሐ. አጽዋማትንና በዓላትንም ለመወሰን የሲኖዶስ ስብሰባ በማድረግ ከላይ የተዘረዘሩትን ሁሉ ወስነዋል፡፡ በሌላ በኩልም ከመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በየጊዜው መናፍቃን /ሐራ ጥቃዎች/ በተነሡ ጊዜ ቅዱሳን የቤተክርስቲያን አባቶች ርትዕት፣ ስብሕት /ኦርቶዶክስ/ ሃይማኖትን ለመጠበቅ ሐራጥቃዎችን በቀኖናዋ ውግዘት ለማስወገድ በሲኖዶስ እየተሰበሰቡ ይወስኑ ነበር፡፡ በዚህ መሠረት ከሦስተኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ጀምሮ በየሀገሩ የአካባቢ ሲኖዶሶች /Regional or Local synods/ ተደርገዋል፡፡ ከተደረጉት ሲኖዶሶችም ለአብነት ጥቂቶቹን ቀጥለን እንመለከታለን

1.    በ257ዓ.ም በካርቴጅ የተደረገው ሲኖዶስ፡- በዚህ የአካባቢ /regional/ ሲኖዶስ ሰማንያ አራት ኤጲስ ቆጶሳት ተሳትፈዋል፡፡ የሲኖዶሱ ሰብሳቢ ቅዱስ ሲፕሪያኖስ ነበር፡፡ በዚህ ጉባኤ ሥርዓተ ጥምቀትንና መናፍቃንን፣ ቅዱሳት መጻሕፍትንና የኤጲስ ቆጶሳትን ሥልጣን የተመለከቱ ቀኖናዎች ተወስነዋል፡፡
2.    268 – 270 ዓ.ም በተከታታይ በአንጾኪያ ሲኖዶስ ተደርጎአል፡፡ በዚህ ሲኖዶስ ዐሥራ አራት ኤጲስ ቆጶሳት ተሰብስበው በምስጢረ ሥጋዌ የኅድረትንና የፅምረትን /ምንታዌ አካላትን/ ትምህርት ማስፋፋት የሞከረውን ኤጲስ ቆጶስ ጳውሎስ ሳምሳጢን መክረው አልመለስ ስላለ አውግዘው ከቤተክርስቲያን ለይተውታል፡፡
3.    በዚሁ ዓይነት በአንካራ በ314 ዓ.ም ፣በጋንግራ 365 ዓ.ም፣ በሳርዲካ በ343ዓ.ም፣ በአንጾኪያ በድጋሚ በ341 ዓ.ም፤ በላኦዶቂያ በ334 እና በ381 ዓ.ም የተጠራው ሲኖዶስ ስድሣ  ቀኖናዎችን ዐውጆአል፡፡ እንደዚሁም በድጋሚ በካርቴጅ በ419 ዓ.ም የተሰበሰበው ሲኖዶስ )138 ቀኖናዎችን ዐውጆአል፡፡ ይህ ሲኖዶስ «የአፍሪካ ኤጲስ ቆጶሳት ሲኖዶስ» በሚል መጠሪያ ይታወቃል፡፡
በአጠቃላይ ከሐዋርያት በኋላ የተነሡ ሐዋርያውያነ አበው /Apostolic Fatheres/ የቤተክርስቲያንን አስተዳደርና የቤተክርስቲያንን ችግር በሲኖዶስ እየተሰበሰቡ በመመርመርና አስፈላጊውንም በመወሰን ቤተክርስቲያንን መርተዋል፡፡ ያውም ከሰባ ዓ.ም ጀምሮ እስከ 313 ዓ.ም ድረስ የነበረው ጊዜ አሕዛብ በቁር የበዙ በትና በመንግሥት አስተዳደርም አጠቃላይ ሥልጣን ግን የጨበጡበት ዘመን ስለነበረ፤ በዚህ ዘመን ከፀረ እግዚአብሔርና ከፀረ ክርስትና ኃይሎች ጋር በመጋደል በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች ስለ ሀልዎተ እግዚአ ብሔርና ኦርቶዶክሳዊ ሃይማኖታቸው መሥዋዕት ሆነው የተሰውበት ዘመን ነበር፡፡ በመሆኑም ዘመኑ ዘመነ ሰማዕታት እየተባለ ይጠራል፡፡

ዓለም አቀፍ ሲኖዶሶች

ከዚህ በላይ ለማየት እንደተሞ ከረው በአካባቢ በሚገኙት አብያተ ክርስቲያናት ዙሪያ ወይም ውስጥ የቀኖና ወይም የዶግማ ችግሮች ሲከሰቱ በአቅራቢያ ሀገሮች ከሚገኙ ኤጲስ ቆጳሳት ሲኖዶሶች እየተጠሩ ለተነሡት ችግሮች መፍትሔ ይሰጡ ነበር፡፡

ነገር ግን በአካባቢ በሚደረጉት ሲኖዶሶች የማይፈቱ ከሆኑ በዚያኑ ጊዜ ዓለም አቀፍ ከሚባለው የዓለም ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስ ቆጶሳት የጋራ የሆነ ዐቢይ ዓለም አቀፍ ጉባኤ /Ecumerical council/ እያደረጉ ችግሮቹን በመመርመር መፍትሔ ይሰጡ ነበር፡፡

የመጀመሪያው የኒቂያ ዓለም አቀፍ ሲኖዶስ በ325ዓ.ም ኒቂያ በተባለች ከተማ ከመደረጉ በፊት አርዮስና ኑፋቄአዊ ትምህርቱን መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት አርዮስ በኖረበትና በተነሣ በት ሀገር በእስክንድርያ በመጀመሪያ በ320 ዓ.ም፤ ቀጥሎም በ321 ዓ.ም ሲኖዶስ ተደረገ፡፡ የዚያሲኖዶስ ሰብሳቢ የእስክንድርያ ሊቀ ጰጳስ የነበረው እለ እስክንድሮስ ዘእስክንድርያ ነበር፡፡ ችግሩ በዚያ ዓይነት ይፈታል ተብሎ ቢሞከርም ሰባት መቶ ደናግል፣ ዐሥራ ሁለት ዲያቆናት፣ ስድስት ቀሳውስት /የደብር አለቆች/ ከሦስት የሚበልጡ ኤጲስ ቆጶሳት ትምህርቱን ተቀብለው አርዮስን ስለደገፉ አርዮስ በሲኖዶሱ ምክር ሊመለስ አልቻለም፡፡ ስለዚህ ከአራት ዓመት በኋላ በሊቀ ኤጲስ ቆጶሳት እለእስክንድሮስ አስተባባሪነት በንጉሠ ነገሥቱ በቆስጠንጢኖስ ተባባሪነት 318 አበው ሊቃነ ኤጲስ ቆጶሳት በኒቂያ ከተማ በ325 ዓ.ም የሲኖዶስ ስብሰባ አድርገው ከኑፋቄው አልመለስ ያለውን እልከኛውን አርዮስንና ትምህርቱን አውግዘው ሃይማኖትን አጸኑ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት በአንድ ልብ ሆነው «አንቀጸ ሃይማኖት /ጸሎተ ሃይማኖት/» የተባለውን የዶክትሪን ዐዋጅ አጸደቁ፡፡ ከሃያም ያላነሱ ቀኖናዎችን አጽድቀው አሠራጩ ፡፡

ከዚያም በመቀጠል ከሃምሳ ስድስት ዓመት በኋላ መንፈስ ቅዱስ ፍጹም አምላክ መሆኑን የካዱ መናፍቃን /ሐራጥቃዎች/ /heretics/ ተነሥተው በምሥራቅ በኩል የነበረችውን ቤተ ክርስቲያን ባስቸገሩ ጊዜ በቁስጥንጥንያ ከተማ በ381 ዓ.ም ከመላው ዓለም አንድ መቶ ሃምሳ አበው ሊቃነ ኤጲስ ቆጶሳት ተሰበሰቡ፡፡ «መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ ያነሰ ነው /ሕጹጽ ነው/» ብለው የተነሡትን መቅዶን ዮስንና ተከታዮቹን ተመክረውና ተለምነው ከክሕደታቸው ስላልተ መለሱ አወገዙአቸው፡፡ ትምህርታቸውንም በማውገዝ ውሳኔ አሳለፉ፡፡ በመቀጠልም ቅዱሳት መጻሕፍትን በመመርኮዝ «መንፈስ ቅዱስ እንደ አብና እንደ ወልድ ፍጹም አምላክ መሆኑን፣ ጌታና ማኅየዊ እየተባለም ከአብና ከወልድ ጋር አንድ ባሕርይ ስለሆነ ከሁለቱ አካላት ጋር በአንድ መለኮት እንደ ሚመሰገንና እንደሚሰገድለት፤ እንዲሁም ከአብ ብቻ መሥረጹን ገልጸው ወሰኑ» ውሳኔውም ከኒቂያው አንቀጸ ሃይማኖት/ከጸሎተ ሃይማኖት/ ጋር ተጨምሮ እንዲጻፍ አደረጉ፡፡ በዚሁም መሠረት በአሁኑ ዘመን በመላው ዓለም በየቤተክር ስቲያኑ በተለያየ ቋንቋ የሚጸለየው ጸሎተ ሃይማኖት «የኒቂያ- ቁስጥ ንጥንያ አንቀጸ ሃይማኖት»/ Nicene-constantinople creed/ እየተባለ ይጠራል፡፡

ከቁስጥንጥንያው ዓለም አቀፍ ሲኖዶስ በኋላ ሃምሳ ዓመታት ቆይቶ ንስጥሮስ የተባለ መናፍቅ ተነሣ ፡፡ እሱም የቁስጥንጥንያ ትርያርክ ነበር፡፡ ከ426ዓ.ም ጀምሮ በቁስጥንጥንያ ምስጢረ ሥጋዌን በማፋለስ «ክርስቶስ ሁለት አካላት፣ ሁለት ገጻት፣ ሁለት በመስተጻምር /በሲናፊያ/ አንድ የሆኑ ባሕርያት ያሉት ነው» እያለ አስተማረ፡፡ በዚህም መርሖ መሠረት «ቃለ እግዚአብሔር /ሎጎስ/ እና ክርስቶስ በመስተፃመር /በሲናፊያ/ አንድ ስለሆኑ ክርስቶስ አንድ ነው» ብሎ አስተማረ፡፡

ከዚሁም አያይዞ «ድንግል ማርያም እግዚአብሔርን ልትወልድ አትችልም፤ ከእርስዋ የተወለደው ክርስቶስ ነው፡፡ ስለሆነም እርስዋን ወላዲተ ክርስቶስ እንጂ ወላዲተ እግዚአብሔር /ወላዲተ አምላክ/ አንላትም» በማለት አስተማረ፡፡ በዚሁ ችግር ምክንያት በ431 ዓ.ም ከመላው ዓለም አበው ሊቃነ ኤጲስ ቆጶሳትና ኤጲስ ቆጶሳት በኤፌሶን ተሰብስበው ሦስተኛውን ዓለም አቀፍ ሲኖዶስ አደረጉ፡፡

ንስጥሮስን ሦስት ጊዜ ጠርተውት አልቀርብም ስላለ የጻፋቸውን መልእክታት ተመልክተውና ስሙን ጠርተው አወገዙት፡፡ ክርስቶስንም «ወልድ ዋሕድ፣ ፍጹም  አምላክ፣ ፍጹም ሰው፣ ከሁለት ባሕርይ / ከመለኮትና ከትስብእት/ አንድ ባሕርይ፣ አንድ አካል» መሆኑን የሚያረጋግጡትን የቅዱስ ቄርሎስን መልእክታት ተቀብለው አጸደቁ፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያምንም «በአማን ወላዲተ አምላክ» መሆንዋን አረጋገጡ፡፡

በሊቀ ኤጲስ ቆጶስ ዮሐንስ ዘአንጾኪያ እየተመራ ወደ ኤፌሶን የመጣው የአንጾኪያ ኤጲስ ቆጶሳት ቡድን ግን የንስጥሮስን ውግዘት ተቃወመ፡፡ በዚህ ምክንያት የአንጾኪያ ቤተክርስቲያን በኤፌሶን ከተሰበሰቡት የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ተለየች፡፡ እስከ 433 ዓ.ም በእስክ ንድርያና በአንጾኪያ አብያተ ክርስቲያናት መካከል መለያየት ጠነከረ፤ የጠብ ግድግዳም ተመሠረተ፡፡ በ433 ዓ.ም ግን በንጉሠ ነገሥት ቴኦዶስዮስ ካልዕ አስታራቂነት ሁለቱም አብያተ ክርስቲያናት ታረቁ፡፡ በቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንደርያና በዮሐንስ ዘአንጾኪያ መካከልም ሰላም ተመሠረተ፡፡ በዚሁ ዕርቅ መሠረት አንጾኪያውያን አበው በኤፌሶን የተወሰነውን ውሳኔ ተቀበሉ፡፡ በንስጥሮስ መወገዝና መወገድም ተስማሙ፡፡ አንድነትም ተመሠረተ፡፡

ቅዱስ ቄርሎስ በ444 ዓ.ም ሲያርፍ በኋላ የሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ  የነበረው ዲዮስቆሮስ ዘእስክንድርያ ትርያርክ ሆኖ ተሾመ፡፡ ከጥቂት ዓመታት በኋላ በ488ዓ.ም ከቁስጥ ንጥንያ በሊቀ ኤጲስ ቆጶስ ፍላቭያን የሚመራ የአካባቢው ኤጲስ ቆጶሳት የተሳተፉበት ሲኖዶስ /Local Synods/ ተደረገ፡፡ ወደዚህም ሲኖዶስ አውጣኪ ተከሶ ቀረበና ተወገዘ፡፡ እርሱም ወደ ሮምና ወደ እስክንድርያ ትርያክ«አላግባብ ተወገዝሁ» ብሎ አቤቱታ ጻፈ፡፡

«የአውጣኪን ጉዳይ ለመመርመርና ተረፈ ንስጥሮሳውያንን ለማስወገድ» በሚል አጀንዳ ለሁለተኛ ጊዜ በ449 ዓ.ም በኤፌሶን ሲኖዶስ ተደረገ፡፡ በስብሰባውም አንድ መቶ ሠላሳ ስአምስት ኤጲስ ቆጶሳት ተሰበሰቡ፡፡ የሲኖዶሱ ሊቀ መንበር ትርያክ ዲዮስቆሮስ ሆነ፡፡ በአጀንዳው መሠረትጉዳዮች ተመረመሩ፡፡ አውጣኪንም መረመሩት፡፡ ሊቀ ኤጲስ ቆጶስ ፍላቭያኖንስና ፌኦዶሪትን ግን ጉባኤው መርምሮ መንፈቀ ንስጥሮሳውያን ሆነው ስላገኛቸው በጊዜያዊ ውግዘት ተቀጥተውና ታስረው እንዲቆዩ ተደረገ፡፡ የፖፕ ልዮን ጦማረ ሃይማኖትም ቀርቦ በዲዮስቆሮስና በሌሎች የጉባኤው አባላት ተመርምሮ ከንስጥሮስ ትምህርት ጋር ተዛምዶ ስለተገኘ በጦማሩና በጦማሩ ባለቤት ላይ ውግዘት አከል ተግሳጽ እንዲተላለፍባቸው ተደረገ፡፡ ፖፕ ልዮን ግን ይህንን ታሪክ ሰምቶ በዲዮስቆሮስ ጥርሱን ነከሰ፡፡

ጉባኤውንም «የወረበሎች ጉባኤ» /Synodd of listriks/ ብሎ ጠራው፡፡ ከዚህ ንዴት የተነሣ  በሁለተኛው ዓመት በ451 ዓ.ም በኬልቄዶን ጉባኤ እንዲደረግ ተወሰነ፡፡ በዚህ ጉባኤስድስት መቶ ሠላሳ ኤጲስ ቆጶሳት ተሰብስበው በልዮን መልእክተኞች እየተመሩ ቅዱስ ዲዮስቆሮስን ከንጉሡ ጋር ተሻርከው ከመንበሩ አወረዱት፡፡ ታስሮም በደሴተ ጋግሪ ሦስት ዓመት ተቀመጠ፡፡ ከዚያም እንዳለ በእስራትና በበሽታ ምክንያት 454 ዓ.ም ዐረፈ፡፡ከቅዱሳን ሐዋርያት ዘመን ጀምሮ እስከ አምስተኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ድረስ ያየነው ታሪክ እንደሚያስረዳን ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተክርስቲያን መሪ እንደሆነ ነው፡፡ ቤተክርስቲያንምከተጠቀሰው የመጀመሪያው ዘመን ጀምሮ እስካለንበት ዘመን ድረስ መለኮታዊ አገልግሎትዋን ስታካሒድ የኖረችው በመንፈስ ቅዱስ በሚመራው በቅዱስ ሲኖዶስ በመመራት ነው፡፡ በቤተክርስቲያናችን ትውፊት መሠረትም የሐዋርያትንና የአርድእት ቀኖናዎች የሊቃውንትም ጭምር ሲኖዶስ /መጽሐፈ ሲኖዶስ/ እየተባለ ይጠራል፡፡ ከዚህ በላይ እንደተ መለከትነውና እንደምናውቀው በአካባቢ የተነሡትን የሃይማኖትም ሆኑ የቀኖና ችግሮች በመጀመሪያ በአካባቢው ሀገሮች ባሉት ሊቃነ ኤጲስ ቆጶሳት ሲኖዶስ ወሳኝነት ይፈቱ ነበር፡፡ ከእነርሱም አቅም በላይ ሆነው የተገኙ ችግሮች ደግሞ «ዓለም አቀፍ ሲኖዶስ» /Ecumerical Synods/ እየተጠራ ሲወሰን እንደነበረ ተመልክተናል፡፡

ከዚያም ሌላ በየትኛውም ሀገር የምትገኘው የክርስቶስ ቤተክርስቲያን /Local Synods/ ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ እስካለንበት ዘመን ድረስ አንድ ማእከል አንድ ሲኖዶስ ብቻ እንዳላት ተገንዝ በናል፡፡ ለምሳሌ የኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን በአንድ የኢየሩሳሌም ቅዱስ
ሲኖዶስ፣ የእስክንድርያ ቤተክርስቲያን በአንድ የእስክንድርያ ቅዱስ ሲኖዶስ፣ የቁስጥንጥንያ ቤተክርስቲያን በአንድ የቁስጥንጥንያ ቅዱስ ሲኖዶስ፣ የግሪክ ቤተክርስቲያን በአንድ የግሪክ ቅዱስ ሲኖዶስ ብቻ ሲመሩ መኖራቸውን እናውቃለን፡፡

ለአንዲት ነጻ ሀገር አንድ ርላ ሜነት /One Panriament/ ብቻ እንዳላት ሁሉ ለአንዲት ነጻ ቤተክርስቲያንም አንድ ቅዱስ ሲኖዶስ /Autocephalous Church/ ብቻ እንዳላት የታወቀና የተረጋገጠ ነው፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ ስንል /በተለይ ሀገራዊ Local/ የሚከተሉትን ነገሮች ይይዛል፡-
– ኤጲስ ቆጶሳት
– የታወቀ ሕጋዊ መንበር
– ታሪካዊና ሕጋዊ መሠረት
ለምሳሌ የግብፅን ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ ብንመለከት
– ወደ ሃምሳ የሚጠጉ ኤጲስ ቆጶሳት
– የእስክንድርያ /የቅዱስ ማርቆስ/ መንበር
– በታሪክ የታወቀና ቅዱስ ሲኖዶሱ ያጸደቀው ሕግ አላቸው

 የኢትዮጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ፦

–    ኤጲስ ቆጶሳት
–    የአዲስ አበባ መንበር /መንበረ ፓትርያክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም የሚገኝ/
በቤተክርስቲያን ሕግ የጸደቀ ከመነሻውም /ሲኖዶስ በኢትዮጵያ ሲጀመር የነበረ ሕግ አላት፡፡
 

ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ /መዝ 2፡11-12/

በዲ/ን አሉላ መብራቱ

 

የዐቢይ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት (ዘወረደ) ለአጠቃላይ ጾሙ መግቢያ የሚሆኑ ሦስት መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ትምህርቶች(መልዕክቶች) ይተላለፉበታል። እነዚህን ቀጥለን እንመለከታለን።

1.    ስለ ጾም

ዘወረደ የታላቁ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት ስለሆነ ቤተ ክርስቲያን የጾም አዋጅ ታውጅበታለች፤ ስለ ጾም ጥቅምና እንዴት መጾም እንዳለብን ታስተምረናለች፡፡ጾመ ድጓው “አከለክሙ መዋእል ዘኃለፈ ዘተቀነይክሙ ለግእዘ ሥጋክሙ፤ ለሥጋቸሁ ፈቃድ የተገዛችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃችኋል፤ ከአሁን በኋላ ግን ጹሙ፣ ጸልዩ ለእግዚአብሔር ተገዙ” እያለ የጾም አዋጅ ያውጃል።

ጾም ፈቃደ ስጋን ለፈቃደ ነፍስ፣ ፈቃደ ነፍስን ለፈቃደ እግዚአብሔር/ለመንፈስ ቅዱስ/ የምናስገዛበት መንፈሳዊ መሳሪያ ነው፡፡ጾሙ ይህ የሚደረግበት መሆኑን ቤተክርስቲያን ሳምንቱ በሚጀመርበት ሰንበት በሚሰበከው ምስባክ እንዲህ ብላ ታሳስባለች፤ “ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ፣በረዓድም ደስ ይበላችሁ” /መዝ 2፡11-12/ ጾም ከምግብና ከመጠጥ እንዲሁም ከሌሎች ምቾቶችና ደስታዎች ከመከልከል ያለፈ ጥልቅ ትርጉም ያለው ተግባር ነው። ጾም ውጤታማ እንዲሆን እነዚህ መከልከሎች ከጸሎት ፣ ከፍቅርና ራስን ከማዋረድ ጋር መተባበር አለባቸውና በዚህ ሳምንት ቤተ ክርስቲያን እንዲህ እያለች ታስተምራለች፦“ንጹም ጾመ ወናፍቅር ቢጸነ ከመ ያብርህ ብርሃነ ስብሃቲሁ በላዕሌነ፤ (የእግዚአብሔር) የክብሩ ብርሃን በላያችን ላይ ያበራ ዘንድ ጾምን እንጹም ፤ወንድማችንንም እንውደድ”

(ጾመ ድጓ)።በዘወረደ እሁድ የሚነበቡት ምንባባትም ይህንን መልዕክት የያዙ ናቸው።“ነገር ግን ፈጣሪያችን የምትበልጠውን ጸጋ ይሰጣል፤ ስለዚህም “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል” ይላል፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔርን እሺ በሉት፤ ሰይጣንን ግን እንቢ በሉት፤ ከእናንተም ይሸሻል፡፡ እግዚአብሔርን ቅረቡት፤ ይቀርባችሁማል፤ እናንተ ኃጥኣን እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት ዐሳብም ያላችሁ እናንተ ልባችሁን አጥሩ፡፡ እዘኑና አልቅሱ፤ ሳቃችሁን ወደ ልቅሶ÷ ደስታችሁንም ወደ ኀዘን መልሱ፡፡ በእግዚአብሔር ፊት ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤ እርሱም ከፍ ከፍ ያደርጋችኋል፡፡” /ያዕ 4÷6-10/

 “ በውኑ እንግዲህ በስሙ እናምን ዘንድ የከንፈሮቻችን ፍሬ የሚሆን የምስጋና መሥዋዕትን በየጊዜው ለእግዚአብሔር ልናቀርብ አይገባንምን? ነገር ግን ለድሆች መራራትን÷ከእነርሱም ጋር መተባበርን አትርሱ፤ እንዲህ ያለው መሥዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋልና፡፡” /ዕብ 13÷15-16/

“ ልባችሁ በመብል ያይደለ በጸጋ ቢጸና ይበልጣልና፤ በዚያ ይሄዱ የነበሩ እነዚያ አልተጠቀሙምና ። ” /ዕብ. 13፥9/በጾም የተጠቀሙ ቅዱሳንን እያሰብን ለጾም እንድንተጋም ወደ እነርሱ እንድንመለከት ቤተክርስቲያን ትጠቁማለች፡፡ ሳምንቱ በሚጀምርበት ሳምንት የሚነበበው የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክትእንዲህ ይላል፡፡

“የእግዚአብሔርን ቃል የነገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነት ምሰሉአቸው።” /ዕብ. 13፥7/ጾመ ድጓው ከእነዚህ መካከል ጥቂቶቹን እንዲህ እያለ ያስታውሰናል፤“የእግዚአብሔር የክብሩ ብርሃን በላያችን ላይ ያበራ ዘንድ ጾምን እንጹም፤ ወንድሞቻችንም እንውደድ፤ ኤልያስ በጾም ወደ ሰማይ አርጓልና፤ዳንኤልም ከአናብስት አፍ ድኗልና፡፡”

2.    ስለ እግዚአብሔር ወልድ መውረድ (ሥጋዌ)

ከዐቢይ ጾም ጀምሮ እስከ ጰራቅሊጦስ ድረስ ያሉት ዕለታት ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጆች ለማዳን ያደረጋቸው ነገሮች (ማስተማሩ፣ ተአምራት ማድረጉ፣ በፈቃዱ ተላልፎ መሰጠቱ፣ ሞቱ፣ ትንሣኤው፣ ዕርገቱ፣ መንፈስ ቅዱስን መላኩ…) በስፋት የሚነገርባቸው ናቸው።

የእነዚህ ሁሉ ነገሮች መሠረትና ያገኘናቸው ጸጋዎች ሁሉ ምንጭ የእግዚአብሔር ወልድ መውረድ (ሰው መሆን) ነው።ይህ ሣምንት የዐቢይ ጾም የመጀመሪያ ሣምንት እንደመሆኑ ቀጥለው ለሚነገሩት ነገሮች መሠረት የሆነው ይህ የእግዚአብሔር መውረድ ይነገርበታል። ዘወረደ (የወረደው) የሚል ስያሜ የተሰጠውም ከዚህ በመነሳት ነው።

ሣምንቱ በሚጀመርበት ሰንበት የሚነበበው ወንጌል ይህን መልእክት የሚያስተላልፍ ነው።“እውነት እውነት እልሃለሁ፥ የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን፥ ነገር ግን ምስክርነታችንንም አትቀበሉትም። በምድር ያለውን ስነግራችሁ ካላመናችሁኝ፥ በሰማይ  ያለውን ብነግራችሁ እንዴት ታምኑኛላችሁ? ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ  በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው ነው። ሙሴ በምድረ በዳ እባቡን እንደ ሰቀለው የሰው ልጅ እንዲሁ ይሰቀል ዘንድ አለው፡፡ያመነበት ሁሉ ለዘለዓለም ሕያው ሆኖ እንዲኖር እንጂ እንዳይጠፋ።በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወትን እንዲያገኝ እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ቤዛ አድርጎ እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶታልና።” /ዮሐ. 3፥11-16/ጾመ ድጓው የሚጀምረውም እንዲህ በማለት ነው፣ “ዘወረደ እምላዕሉ፣ አይሁድ ሰቀሉ…. እግዚአ ኩሉ ዘየሀዩ በቃሉ፤ ….በቃሉ የሚያድነውን ከላይ የወረደውን የሁሉን ጌታ አይሁድ ሰቀሉት… ”

3. ስለ ትምህርት

 ዐቢይ ጾም የትምህርት ዘመን ነው። በጥንት ቤተ ክርስቲያን አዳዲስ አማንያን /ንዑሰ ክርስቲያን/ የሚጠመቁት በትንሣኤ በዓል ስለነበር በዐቢይ ጾም ሰፊ ትምህርት ይሰጣቸው ነበር።ዛሬም ዐቢይ ጾም ጌታችን በዚህ ምድር በእግረ ሥጋ በተመላለሰባቸው ዘመናት ያደረጋቸው  ነገሮች (ትምህርቱ፣ ተአምራቱ፣ ሞቱ፣ ትንሣኤው … ) በሣምንታት ተከፋፍለውና ተደራጅተው የምንማርበት የትምህርት ዘመን ነው። በአብነት ትምህርት ቤቶቻችንም ዐቢይ ጾም ዋነኛ የትምህርት ዘመን መሆኑ ይታወቃል።

ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን የትምህርት ዘመን በሆነው ዐቢይ ጾም መግቢያ ላይ ስለ ትምህርትና ስለ መምህራን እንዲህ እያለች ትሰብካለች፤

“የእግዚአብሔርን ቃል የነገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነት ምሰሉአቸው። ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም የሚኖር እርሱ ነውና። ሌላ ልዩ ትምህርት አታምጡ።” /ዕብ. 13፥7-9/

“ለመምህሮቻችሁ ታዘዙ፤ ተገዙላቸውም፤ስለ እናንተ በእግዚአብሔር ፊት ምላሽ የሚሰጡ እንደመሆናቸው፣ ይህን ሳያዝኑ ደስ ብሎአቸው ያደርጉት ዘንድ ስለ ነፍሳችሁ ይተጋሉና፡፡” /ዕብ. 13፥17/

አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ መዋዕለ ጾሙን በሠላም አሳልፈህ የትንሣኤህን ብርሃን ለማየት እንድታበቃን እንለምንሃለን። አሜን።

የዘወረደ መዝሙርና ምንባባቱ በዜማ

ዘወረደ(የዐቢይ ጾም አንደኛ ሳምንት)

የዕለተ ሰንበት መዝሙር (ከጾመ ድጓ)

ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት ወተሐሠዩ ሎቱ በረዓድ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ ባኡ ቅድሜሁ በተጋንዮ ወውስተ አ|ዕፃዲሁ በስብሐት አምንዎ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ ንጹም ጾመ ወናፍቅር ቢጸነ ወንትፋቀር በበይናቲነ  እስመ ለዓለም ምሕረቱ አክብሩ ሰንበተ ተገበሩ ጽድቀ እስመ ሰንበትሰ በእንተ ሰብእ ተፈጥረት እስመ ለዓለም ምሕረቱ ምሕረተ ወፍትሐ አሐሊ ለከ እዜምር ወእሌቡ ፍኖተ ንጽሕ እስመ ለዓለም ምሕረቱ ለትውልደ ትውልድ ጽድቁ ንሕነሰ ሕዝቡ አባግዓ መርዔቱ።

ትርጉም፦ እግዚአብሔርን በመፍራት ተገዙለት ለእርሱ መገዛትም ደስ ያሰኛችሁ። እግዚአብሔር ቸር ምሕረቱም ለዘላለም፣ እውነቱም ለልጅ ልጅ ነው ። እኛስ ሕዝቡ የመሰማሪያው በጎች ነን፡፤ ወደ ደጁ በመገዛት፣ ወደ አደባባዮችም በምስጋና ግቡ፤ ጾምን እንጹም፤ጓደኞቻችንን እናፍቅር፤እርስ በርሳችንም እንፋቀር ። ሰንበት ስለሰው ተሠርታለችና ሰንበትን እናክብር። እውነትንም እንሥራ፤ አቤቱ ምሕረትንና ፍርድን እቀኝልሃለሁ፤ እዘምራለሁ፤ንጹሕ መንገድንም አስተውላለሁ።

ምንባባት
መልዕክታት
ዕብ.13÷7-17የእግዚአብሔርን ቃል የነገሩአችሁን መምህሮቻችሁን ዐስቡ፤ መልካም ጠባያቸውን አይታችሁ በእምነት ምሰሉአቸው፡፡ (ተጨማሪ ያንብቡ)

ያዕ.4÷6-ፍጻ. ነገር ግን ፈጣሪያችን የምትበልጠውን ጸጋ ይሰጣል፤ ስለዚህም “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል” ይላል፡፡(ተጨማሪ ያንብቡ)
ግብረ ሐዋርያት
ሐዋ.25÷13-ፍጻ. ከጥቂት ቀን በኋላም ንጉሥ አግሪጳና በር ኒቄ ወደ ቂሣርያ ወርደው ፊስጦስን ተገናኙት፡፡ (ተጨማሪ ያንብቡ)

ምስባክ
መዝ. 2፡11 ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት ወተሐሠዩ ሎቱ በረዓድ።አጽንዕዋ ለጥበብ ከመ ኢይትመዐፅ እግዚአብሔር።

ትርጉም፦ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ፥ በረዓድም ደስ ይበላችሁ።ጥበብን አጽኑአት ፤ እግዚአብሔር እንዳይቆጣ።

ወንጌል
• ዮሐ.3÷10-24 ጌታችን ኢየሱስም መልሶ÷ “አንተ የእስራኤል መምህራቸው ነህ፤ ነገር ግን አንዴት ይህን አታውቅም?” አለው፡፡ (ተጨማሪ ያንብቡ)
ቅዳሴ
ዘእግዚእነ

የዘወረደ መዝሙርና ምንባባቱ በዜማ

መዝሙሩንና ምንባባቱ በዜማ ለማዳመጥ ይህን ይጫኑ

KidaneMihret

ኪዳነ ምሕረት

ዲ/ን ኅብረት የሺጥላ

KidaneMihret

‘ኪዳን’ የሚባለው ቃል “ቃል” ከሚለው ጋር እየተቀናጀ በብሉይ ኪዳን ለ280 ጊዜ ያህል ሲጠቀስ በአዲስ ኪዳን ደግሞ ከ33 ጊዜ በላይ ተጠቅሷል፡፡ “ኪዳን” ቃሉ “ተካየደ” ተማማለ፣ ቃል ተገባባ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ነው፡፡

 

“ምሕረት” የሚለው ቃል ደግሞ ማብራሪያ ሳያሻው ምሥጢሩ ከነዘይቤው ከግእዝ የተወረሰ ነው፡፡ ስለዚህ ኪዳነ ምሕረት ማለት የምሕረት፣ የይቅርታ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ ኪዳን ከተራ ውሎችና ስምምነቶች የበለጠ ጽኑና ቀዋሚ ነው፡፡ ከፍ ያለ ክብደትም አለው፡፡

“ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደርጋለሁ” ተብሎ በዳዊት መዝሙር እንደተጻፈ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳን አድርጓል፡፡ ወደ ፊትም ያደርጋል፡፡ /መዝ. 88÷3/ ቃል ኪዳኑም የምሕረት ቃል ኪዳን ነው፡፡ በቅዱሳን አበውና በቅዱሳት እማት/እናቶች/ ታሪክ፣ ገድልና ድርሳን እንደምናነበው እግዚአብሔር ለቅዱሳን ከመሞታቸው አስቀድሞ ይገለጥላቸዋል፤ የምሕረት ቃል ኪዳንም ይሰጣቸዋል፡፡ የእግዚአብሔር የምሕረት ቃል ኪዳን በቅዱሳኑ ሕይወት ዙሪያ ብቻ የሚያተኩር አይደለም፡፡ ለስማቸው፣ ለመስቀላቸው፣ ለልብሳቸው ገድላቸውን ለያዘ መጽሐፍ፣ አልፎ ተርፎም ለረገጡት አፈርና ለተጋደሉበት ቦታ ሁሉ ተርፎላቸዋል፡፡ ስለዚህ ልዩ ልዩ ቃል ኪዳን የተገባላቸው ቅዱሳት መካናት ሞልተዉናል፡፡

ለቅዱሳን ከሞት አስቀድሞ የእግዚአብሔር መገለጥ ወይም የሚሞቱበትን ጊዜና የአሟሟታቸውን መንገድ ገልጦ መንገር በቅዱሳት መጻሕፍት የተለመደ ነው እንጂ እንግዳ ነገር አይደለም፡፡ ጌታ ለቅዱስ ጴጥሮስ እንዴት ባለ አሟማት እንደሚሞት ነግሮታል፡፡ /ዮሐ.21÷39፤ 2ኛ ጴጥ.1÷14/ ለቅዱስ ጳዉሎስ ስለሚሞትበት ጊዜ ተነግሮታል፡፡ /የሐዋ.20÷25 ፣ 21÷10-13/ “ከሞቱ አስቀድሜ እገለጥለታለሁ” እንዲል፡፡ /ሰኔ ጎልጎታ/፡፡

 

እግዚአብሔር ከሞታቸው አስቀድሞ በመገለጥ ለቅዱሳን የምሕረት ቃል ኪዳን የሚሰጣቸው በእነርሱ በጎ ሥራ ከእነርሱ በኋላ ያሉ የሰው ልጆችን ለመጥቀም ፈልጎ ነው፡፡ ተጠቃሚዎቹ ራሳቸው ናቸው እንዳይባል ወደ ሞት አፋፍ የተጠጉ ከመሆናቸውም ባሻገር ለቃል ኪዳን የበቁት የሚጠቀሙበት በጎ ሥራ በመሥራታቸው ነው፡፡ የሰው ልጆች ያለፉ ቅዱሳንን በመዘከር የቃል ኪዳናቸው ተጠቃሚ ሲሆኑ ቅዱሳኑ ግን ከመታሰብ በቀር በሰው በኩል የሚጨመርላቸው የለም፡፡ ቅዱሳን የምሕረት ቃል ኪዳን ሲቀበሉ ለወገናቸው መትረፋቸውን እንረዳለን፡፡

የምሕረት ቃል ኪዳን ለምን ያስፈልጋል ቢባል ሕግ መተላለፍ ካለ ሁልጊዜ ተጠያቂነት ወይም ቅጣት ይኖራል፡፡ ይህም በአዳም ይታወቃል፡፡ የሰው ልጆች ደግሞ ከተጠያቂነት ነጻ የሚያደርግ አኗኗር ይዘው አይገኙም፡፡ በዚህ ምክንያት ቅጣት እንዳያገኛቸው የሚድኑበትን በርካታ መንገዶች እግዚአብሔር አዘጋጀ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አንዱ የምሕረት ቃል ኪዳን ነው፡፡

የምሕረት ቃል ኪዳን ሁሉ በጎ እንድንሠራ የሚያበረታታ ነው፡፡ ይህም ዘወትር ከቃል ኪዳኑ ጋር ተያይዘው በሚቀመጡ ግዴታዎች ይታወቃል፡፡ ለበጎ ሥራ ምክንያት የማይሆን ባዶ የምሕረት ቃል  ኪዳን የለም፡፡ “ስምሸን /ስምህን/ የጠራውን፣ ዝክር ያዘከረውን፣ የተራበ ያበላውን፣ የተጠማ ያጠጣውን፣ የታረዘ ያለበሰውን፣ እንግዳ በስምህ /በስምሽ/ የተቀበለውን፣ ገድልህን ያነበበውን፣ የሰማውን፣ የተረጎመውን ወዘተ ኃጢአቱን ይቅር እለዋለሁ፣ እምረዋለሁ” የሚሉ ቃል ኪዳናት በሙሉ ከባዱን መልካም ሥራ መፈጸም ባይቻለን እንኳን ቀላሉን መሥራት እንዳለብን ግዴታ የሚጥሉ ናቸው እንጂ አንዳንዶች እንደሚያስቡት መልካም እንዳንሠራ የሚያሳንፉ አይደሉም፡፡ ከዚህ ይልቅ ለበጎ ሥራ የሚያነሣሡና የታዘዙትን መሥራት ያልተቻላቸውን ሰዎች ተስፋ ሳይቆርጡ እስከ መጨረሻው ሰዓት የሚድኑበት መንገድ እንዳለ አውቀው የተቻላቸውን እንዲያደርጉ የሚጠቁሙ ናቸው፡፡

የእግዚአብሔር ቸርነት ከአእምሮ በላይ ነው፡፡ ይህም ሰዎች በእግዚአብሔር ቸርነት ላይ በሚያነሡት ጥያቄ ይታወቃል፡፡ ለምሳሌ በየዜና ገድላቸው እንደምናነበው እግዚአብሔር ለብዙ ቅዱሳን “እስከ አሥር፣ ሠላሳ፣ ሃምሳ አምስት ወዘተ ትውልድ ድረስ እምርልሃለሁ” እያለ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል፡፡ ይህን በማንበብ እምነት የጎደላቸው አንዳንዶች “ይህ እንዴት ይሆናል?” እያሉ ይጠይቃሉ፡፡ ይህ ብቻ በራሱ የፈጣሪ ቸርነት ከሕሊና በላይ መሆኑን አያስረዳምን ?

ፈጣሪ ስለ ፈራጅነቱና ስለ መሐሪነቱ ሲናገር “በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ ለሚወዱኝ ትእዛዜን ለሚጠብቁ እስከ ሺሕ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝ” ይላል፡፡ /ዘጸ.20÷2-6/ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እስከ ሺሕ ትውልድ የሚደርስ የእግዚአብሔርን ምሕረት መናገሩ በአዋልድ መጻሕፍት ላይ ያለው የሠላሳና የሃምሳ ትውልድን ምሕረት የሚያወሳው ኃይለ ቃል ሊስተባበል አለመቻሉን ያሳያል፡፡ ያን   ማክፋፋት ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እንደመቃወም ይቆጠራል፡፡

ዓለም ከተፈጠረች ሰባት ሺሕ አምስት መቶ ዓመት ገደማ ሊሆናት ነው፡፡ የሰው ልጅን አማካይ እድሜ እጅግ አሳንሰን በመቁጠር የአንድ ትውልድ ዘመን ሠላሳ ዓመት ነው ብንል እንኳን ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ያለው ትውልድ ከሁለት መቶ ሃምሳ አይበልጥም፡፡ ነገር ግን ፈጣሪ የሚወደውና ትእዛዙን የሚጠብቅ እውነተኛ ሰው ከተገኘ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ያን ያህል ትውልድ እስከዓለም ፍፃሜ የሚኖር ከሆነም “እስከ ሺሕ ትውል” ድረስ እንኳን ይቅር ሊል ቃል ኪዳን ገብቷል፡፡ ይህ የሚያሳየው የእግዚአብሔርን የቸርነት ስፋት ነው፡፡ ሺሕ ትውልድ ባይኖር እንኳን ሺሕ ትውልድ ስለሌለ እግዚአብሔር ሺሕ ትውልድ ሊምር አይችልም አይባልም፡፡ ስለዚህ የፈጣሪን ቃል ኪዳን ከመሐሪነቱ አንጻር እንጂ ከዓመታቱ መብዛት አንጻር ሊመለከቱት አይገባም፡፡

ፈጣሪ ለቅዱሳኑ በየዕለቱ ብዙ ነፍሳትን ከሲዖል እንዲያወጡ የምሕረት ቃል ኪዳን ሊሰጣቸው ይችላል፡፡ የተሰጣቸውም ቅዱሳን አሉ፡፡ ነገር ግን ተፈጻሚነቱን ስንመለከት በቀን የተባለውን ያህል ነፍሳት ከሲዖል ሊወጡ ወይም አንድም ነፍስ ከሲዖል ላትወጣ ትችላለች፡፡ ይህ ግን በተገባላቸው ቃል ኪዳን ላይ ምንም ዓይነት አሉታ የለውም፡፡ ምክንያቱም ለቅዱሳኑ ይህ ቃል ኪዳን ሲሰጥ ሲዖል ካለችው ነፍስ ደግሞ የሚጠበቅ ነገር ይኖራልና፡፡ ያን የምታሟላ ነፍስ ካልተገኘች ኪዳኑ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡ ይህም በመሆኑ ቃል ኪዳኑ ከንቱ ነው አይባልም፡፡ ከላይ እንዳየነው ተፈጻሚ ሊሆን ባለመቻሉ ብቻ ለሺሕ ትውልድ የተገባው ቃል ኪዳን ከንቱ ነው ሊባል አይቻልምና፡፡

ስለዚህ ምእመናን ቅዱሳን የተገባላቸው ቃል ኪዳን ለሰው ልጆች የተሰጠ የመዳን ጸጋ መሆኑን መረዳት ይገባቸዋል፡፡ በኃጢአት ወድቀን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ፍርድ ፊት የሚያፍር ነፍስ እንዳለን ስንረዳ ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ ለወዳጆቹ ስለገባው ቃልኪዳን ብሎ እንዲምረን መማጸን ይገባል፡፡«ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደርጋለሁ» ባለው መሠረት ጌታ ከእመቤታችን ጋር ብዙ ቃል ኪዳን አድርጓል፡፡ እርሷ የተመረጠች ብቻ ሳትሆን ከተመረጡትም ሁሉ የተመረጠች ናትና፡፡ ከቅዱሳን ሁሉ እመቤታችን ድንግል ማርያም በሁሉም ረገድ ስለምትበልጥ ከተሰጣቸውም የምሕረት ቃል ኪዳን ለሷ የተሰጣት ኪዳን ኪዳነ ምሕረት ተብሎ ተለይቶ ይታወቃል፤ ማለትም ትጠራበታለች፤ ኪዳነ ምሕረት ትባላለች፡፡ ስለዚህ የኃጥአን ሁሉ ዓይን የእርሷን የምሕረት ቃል ኪዳን ተስፋ ያደርጋል፡፡ የሚገባቸውን ሁሉ አድርገው ላወቁትና ላላወቁት ጉድለቶቻቸው ሁሉ ስሟን ለሚጠሩ ቃል ኪዳንን ለመቀበል ያበቃትን ለሰው ልጆች ነጻነት ልጇ ለሰጠው ፍፁም መድኃኒት ምክንያት የሆነችበት ጸጋዋ ሁሉ በሥላሴ ፊት ይታሰብላቸዋል፡፡

                                           ቅድስት ድንግል ማርያም በቃል  ኪዳኗ አትለየን! 

Jesus.JPG

ዐቢይ ጾም፤ ወደ ትንሣኤ የሚደረግ ጉዞ

 

በዲ/ን ዘላለም ቻላቸው

 

አንድ ሰው ለጉዞ ሲነሣ ወዴት እንደሚሄድ ማወቅ አለበት፡፡ በዐቢይ ጾምም እንዲሁ፡፡ ከሁሉም በላይ ዐቢይ Jesus.JPGጾም መንፈሳዊ ጉዞ ነው፤ መድረሻውም ትንሣኤ ነው፡፡ ለእውነተኛው መገለጥ ለፋሲካ መሟላት የሚደረግ ዝግጅት ነው፡፡ ስለዚህ በጣም አስፈላጊ የሆነና ስለ ክርስትና እምነታችንና ሕይወታችን በጣም ወሳኝ የሆነ ነገር ስለሚገልጥልን ይህን በዐቢይ ጾም እና በትንሣኤ መካከል ያለውን ግንኙነት ለመረዳት በመሞከር መጀመር አለብን፡፡

 

የትንሣኤ በዓል ከበዓላት አንዱ ከመሆን እና የአንድ ያለፈ ክስተት መታሰቢያ ከመሆን በላይ ሊታሰብ ያስፈልገዋል፡፡ አንድ ጊዜም ብቻ እንኳን ቢሆን የትንሣኤን በዓል በሚገባው መልኩ አክብሮ በዚያም ከቀን ይልቅ በሚያበራው ሌሊት የተሳተፈና ያንን ልዩ ደስታ የቀመሰ ማንም ሰው ያውቀዋል፡፡ ያ ደስታ ግን ስለ ምንድን ነው? በትንሣኤ በዓል ዕለት እንደምናደርገው «ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሀጺባ በደመ ክርስቶስ»፤ «ትንሣኤከ ለእለ አመነ ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ»፣ «ዛሬ ሁሉም ነገር፣ ሰማይም፣ ምድርም፣ ከምድር በታች ያሉ ነገሮችም በብርሃን ተሞሉ» እያልን መዘመር የምንችለው ለምንድነው? «የሞት መሞት፤ የሲኦል መበዝበዝ፣ የአዲስና የዘለዓለማዊ ሕይወት መጀመሪያ…» እያልን ማክበር የምንችለው እንዴት ነው?

 

ለእነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች መልሱ ይህ ነው፡፡ ከሁለት ሺሕ ዓመታት በፊት ከመቃብር ወጥቶ ያበራው አዲስ ሕይወት በክርስቶስ ለምናምን ለሁላችንም ተሰጥቶናል፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ «በሞቱም እንመስለው ዘንድ ከእርሱ ጋር በጥምቀት ተቀበርን፤ እርሱ ክርስቶስ በአባቱ ጌትነት ከሙታን እንደተነሣ እኛም እንደ እርሱ በሐዲስ ሕይወት እንኖራለን» /ሮሜ.6:4/ እንዳለው ይህ አዲስ ሕይወት እና ብርሃን ለእኛ የተሰጠን በጥምቀታችን ዕለት ነው፡፡

 

ስለዚህ የትንሣኤን በዓል ስናከብር፣ የክርስቶስን ትንሣኤ በእኛ ላይ እንደ ተደረገ እና አሁንም እንደሚደረግ አድርገን እናከብራለን፡፡ ምክንያቱም እያንዳንዳችን የዚያን የአዲስ ሕይወት ስጦታ እና ያንን የምንቀበልበት እና በእርሱም የምንኖርበትን ኃይል ተቀብለናል፡፡ ይህ ስጦታ በዚህ ዓለም ስላለው ነገር ሁሉ ስለ ሞትም ጭምር ያለንን አመለካከት የሚቀይር ነው፡፡ በደስታ «ሞት የለም» ብለን በእርግጠኝነትም መናገር እንድንችል የሚያደርገን ነው፡፡

 

ኦ! ሞት ግን አሁንም አለ፤ በእርግጠኝነት እንጋፈጠዋለን፤ አንድ ቀንም መጥቶ ይወስደናል፡፡ ነገር ግን ክርስቶስ በራሱ ሞት፣ የሞትን ባሕርይ /ምንነት/ እንደቀየረው ይህ ሙሉ እምነታችን ነው፤ ሞትን ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት መሸጋገሪያ፣ ማለፊያ፣ ፋሲካ አድርጎታል፤ ከአሳዛኝ ነገሮች ሁሉ የበለጠ አሳዛኝ የነበ ረውን ሞት ወደ ፍጹም ድልነት ቀይሮታል፡፡ «ሞትን በሞቱ ደምስሶ» የትንሣኤው ተካፋዮች አድርጎናል፡፡ ለዚህም ነው «ክርስቶስ ተነሥቷል፣ ሕይወትም ሆኗል፤ ማንም በመቃብር አይቀርም» የምንለው፡፡

 

ቁጥር በሌላቸው በቅዱሳኖቿ የተረጋገጠውና ግልጽ የተደረገው የቤተክርስቲያን እምነት ይህ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ እምነት በእኛ ውስጥ ሁልጊዜ አለመኖሩ [ይህንን ሁል ጊዜ አለማሰባችን]፤ እንዲሁም እንደ ስጦታ የተቀበልነውን አዲስ ሕይወት ሁልጊዜ መጣላችንና መካዳችን እንዲሁም ክርስቶስ ከሞት እንዳልተነሣ ሆነን የመኖራችን ነገር እና ያ ልዩ ክስተት ለእኛ ምንም ዓይነት ትርጉም የሌለው መሆኑ የዕለት ተዕለት ተሞክሮአችን አይደለምን?

ይህ ሁሉ የሆነው በድካማችን ምክንያት ነው፡፡ ማለትም ጌታ «አስቀድማችሁ መንግሥቱንና ጽድቁን ፈልጉ» ባለን ጊዜ በወሰነልን ደረጃ «በእምነት፣ በተስፋ እና በፍቅር» መኖር ለእኛ የማይቻለን በመሆኑ ነው፡፡ ይህንን ሁሉ በቀላሉ እንረሳዋለን፤ ምክንያቱም ሁልጊዜም በተለያዩ ሥራዎች የተጠመድን እና በዕለት ተዕለት ተግባሮቻችን የተዋጥን ነን፤ ስለ ምንረሳም እንወድቃለን፤ በጥምቀት የተቀበልነውን አዲስ ሕይወት እና ብርሃንም እንጠራለን፡፡

 

በዚህ በመርሳት፣ በመውደቅ እና ኃጢአት በመሥራት በኩልም ሕይወታችን በድጋሜ «አሮጌ» ይሆናል፤ ጥቅም /ረብ/ የሌለው፤ ጨለማ እና ትርጉም አልባ፤ ትርጉም የሌለው ጉዞ፤ ትርጉም ወደሌለው ፍጻሜ ይሆናል፡፡

ሞትን እንኳን ሳይቀር ረስተነው ከቆየን በኋላ በድንገት «ደስታ በሞላበት ሕይወታችን» መሐል አስፈሪ፣ ሊያመልጡት የማይችሉት እና አስጨናቂ ሆኖ ወደ እኛ ይመጣል፡፡

በየጊዜው ኃጢአታችንን ልንናዘዝ እንችላለን፤ ነገር ግን ሕይወታችንን ከዚያ ክርስቶስ ለእኛ ከገለጠውና ከሰጠው ከአዲሱ ሕይወት ጋር ማዛመድና ሕይወታችንን በዚያ ላይ መመሥረት እናቆማለን፡፡ ትልቁና እውነተኛው ኃጢአት፣ የኃጢአቶች ሁሉ ኃጢአት፣ የስም ብቻ የሆነው ክርስትናችን በጣም አሳዛኝ ገጽታ ይህ ነው፡፡ የሕይወታችንን ትርጉም በክርስቶስ ትንሣኤ ላይ አለመመሥረት፡፡

 

ይህንን ልብ ካልን፣ የትንሣኤ በዓል ምን እንደሆነና ዐቢይ ጾም ለምን ከእርሱ በፊት እንዲኖር እንዳስፈለገ እንረዳለን፡፡

በዐቢይ ጾም በቤተክርስቲያን የሚደረገው ሥርዓተ አምልኮ ዓላማም በቀላሉ የምንጥለውንና የምንወስደውን የዚያን የአዲስ ሕይወት ርእይ እና ጣዕም በውስጣችን እንድናድሰው ለመርዳት እና ተጸጽተን ወደ እርሱ እንድንመለስ ለማድረግ ነው፡፡ ምክንያቱም የማናውቀውን ነገር እንዴት ልንወድና ልንፈልግ እንችላለን? አይተነው እና አጣጥመነው የማናውቀውን ነገር እንዴት በሕይወታችን ካሉ ነገሮች ሁሉ በላይ ልናደርገው እንችላለን? በአጭሩ ስለ እርሱ ምንም አሳብ የሌለንን መንግሥት እንዴት ልንፈልግ እንችላለን? አንችልም፡፡ ስለዚህም ቤተክርስቲያን በእነዚህ ሥርዓተ አምልኮዎች ይህን እንድናደርግ ትረዳናለች፡፡

 

በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ወዳለው ሕይወት መግቢያችን፤ ከዚያም ጋር ያለን ኅብረት መሠረት በቤተክርስቲያን ያለው አምልኮ ነው፡፡ ቤተክርስቲያን «ጆሮ ያልሰማውን፣ ዓይንም ያላየውን በሰው ልብም ያልታሰበውን፤ ነገር ግን እግዚአብሔር እርሱን ለሚወዱት ያዘጋጀውን» ከዚያ ነገር ጥቂቱን ለእኛ የም ትገልጥልን በአምልኮ ሕይወቷ አማካኝነት /through her liturgical life/ ነው፡፡ በዚያ በአምልኮ ሕይወት መሐል ላይ ደግሞ፣ እንደ  ጠቅላላው የአምልኮ ሥርዓት ልብ እና ከፍታ፣ እንዲሁም ጨረሮቿ ሁሉም ቦታ እንደሚደርሰው ፀሐይ ሆኖ የትንሣኤ በዓል ይቆማል፡፡

የትንሣኤ በዓል በየዓመቱ ወደ ክርስቶስ መንግሥት ግርማ እና ውበት ለማሳየት የሚከፈት በር ነው፡፡ የሚጠብቀን ዘለዓለማዊ ደስታ ቅምሻ ነው፡፡ ምንም እንኳን በስውር ቢሆንም ፍጥረትን ሁሉ የሞላው፣ «ሞት የለም!» የሚለው የዚያ ድል ክብር መገለጫ ነው፡፡

 

አጠቃላይ የቤተክርስቲያን የአምልኮ ሕይወት ዓመታዊው የአምልኮ መርኀ ግብር /liturgical year/ የተደራጀው በትንሣኤ ዙሪያ ነው፤ ማለትም በዓመቱ በተከታታይ የሚመጡት ወቅቶች እና በዓላት ወደ ፋሲካ፣ ወደ ፍጻሜው የሚደረጉ ጉዞዎች ይሆናሉ፡፡ ፋሲካ ፍጻሜ ብቻ ሳይሆን ጅማሬም ነው፤ «አሮጌ» የሆነው ነገር ሁሉ ፍጻሜ እና የአዲስ ሕይወት መጀመሪያ፤ ከዚህ ዓለም በክርስቶስ ወደ ተገለጠው መንግሥት መሸጋገሪያ ነው፡፡

 

ይሁን እንጂ የኃጢአት እና የማይረቡ ነገሮች መንገድ የሆነው «አሮጌው» ሕይወት ግን በቀላሉ የሚሸነፍ እና የሚቀየር አይደለም፡፡ የሰው ልጅ አሁን ባለበት ሁኔታ ሊፈጽመው የማይችለውን ነገር የወንጌል ሕግ ትጠብቅበታለች፡፡ ከአቅማችን እና ከምንችለው እጅግ በጣም በሚበልጥ ርእይ፣ ግብ እና የሕይወት መንገድ እንፈተናለን ምክንያቱም ሐዋርያት እንኳን ሳይቀሩ የጌታን ትምህርት ሲሰሙ ተስፋ በመቁረጥ «ይህ እንዴት ይቻላል?» ብለው ጠይቀውታል፡፡ በእርግጥም በየዕለቱ በሚያስፈልጉን ነገሮች በመጨነቅ፣ ቀላል ነገሮችን፣ ዋስትናን እና ደስታን በመፈለግ የተሞላን የማይረባ የሕይወት እሳቤ ትቶ «ሰማያዊ አባታችሁ ፍጹም እንደሆነ እናንተም ፍጹማን ሁኑ» የተባለለትንና ከፍጽምና በቀር ሌላ ምንም ግቡ ያልሆነውን የሕይወት እሳቤ መያዝ ቀላል አይደለም፡፡

 

ዓለም በመገናኛ ብዙኃኖቿ በሙሉ «ተደሰቱ፣ ቀለል አድርጋችሁ እዩት /take it easy/፣ ሰፊውን መንገድ ተከተሉ» ትለናለች፡፡ ክርስቶስ ደግሞ በወንጌል «ጠባቡን መንገድ ምረጡ፣ ተዋጉና መከራን ተቀበሉ፤ ይህ ወደ እውነተኛው ደስታ የሚያደርስ ብቸኛው መንገድ ነውና» ይለናል፡፡ ቤተክርስቲያን ካልረዳችን ካልደገፈችን እንዴት ያንን አስጨናቂ ምርጫ መምረጥ እንችላልን? እንዴትስ መጸጸት /ንስሐ መግባት/ እና በየዓመቱ በትንሣኤ በዓል ዕለት ወደሚሰጠው የከበረ ቃል ኪዳን መመለስ እንችላለን? የዐቢይ ጾም አስፈላጊነቱ እዚህ ላይ ነው ይህ በቤተ ክርስቲያን የተዘጋጀልን ዕርዳታ፣ የትንሣኤ በዓልን የመብላት የመጠጣት እና የመዝናናት ፈቃድ የሚገኝበት ዕለት ነው ብለን ሳይሆን፣ በውስጣችን ያለው የአሮጌው መጨረሻ እና የእኛ ወደ አዲሱ መግቢያ አድርገን እንድንቀበለው የሚያስችለን የንስሐ ትምህርት ቤት ነው፡፡

 

በጥንታዊቷ ቤተክርስቲያን የዐቢይ ጾም ዋና ዓላማ ንኡሰ ክርስቲያንን ማለትም አዳዲስ አማንያንን በዚያን ጊዜ በትንሣኤ ዕለት ለሚፈጸመው ጥምቀት ማዘጋጀት ነበር፡፡ ነገር ግን /ክርስትና ከተስፋፋና/ የሚጠመቁ ሰዎች ቁጥር ከቀነሰ በኋላም ግን ቢሆን የዐቢይ ጾም መሠረታዊ ትርጉም በዚያው ጸንቷል፡፡ ስለዚህም ትንሣኤ በየዓመቱ ወደ ጥምቀታችን መመለሻ ሲሆን ዐቢይ ጾም ደግሞ ለመመለስ መዘጋጃችን ነው፤ በክርስቶስ ወደሆነው አዲስ ሕይወት ለመተላለፍ የምናደርገው ትጋትና ጥረታችን ነው፡፡

 

ዐቢይ ጾም ጉዞ ነው፤ መንፈሳዊ ጉዞ ነው፡፡ ገና ስንጀምረው፣ በዐቢይ ጾም ብሩህ ሐዘን /bright sadness/ ውስጥ የመጀመሪያውን እርምጃ ስንራመድ ከር. . . ቀት ፍጻሜውን /መጨረሻውን/ እናያለን፡፡ ይህም የትንሣኤ በዓል ደስታ ነው፤ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ክብር መግባት ነው፡፡ የዐቢይ ጾምን ሐዘን ብሩህ የሚያደርገውና በወቅቱ የምናደርገውን ጥረት «መንፈሳዊ ምንጭ» የሚያደርገውም ይህ የትንሣኤ በዓል ቅምሻ የሆነው ብሩህ ርእይ ነው፡፡

ሌሊቱ ጨለማ እና ረጅም ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን በመንገዱ ሁሉ ምስጢራዊ የሆነ ብሩህ ወገግታ በአድማሱ ላይ ያንፀባርቃል፡፡«ሰውን ወዳጅ /መፍቀሬ ሰብእ/ ሆይ! አቤቱ ተስፋ ያደረግነውን ነገር አታስቀርብን» አሜን፡፡

 

ምንጭ፡- [The Lent, Father Alexander Schemaman, St. vladmir’s Seminary Press,].

ሐመር መጋቢት 2002

St_Anthony_Icon_3.jpg

የበረሃዉ መልአክ ቅዱስ እንጦንስ

በተ/ሥላሴ ጸጋ ኪሮስ
 
St_Anthony_Icon_3.jpgእንደተለመደው የኦሪት ዘፍጥረትን ትርጓሜ መሠረት ያደረገውን ተከታታይ ትምህርት ለመማር በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ ውስጥ ካሉት አዳራሾች በአንዱ ተሰብስበናል፡፡  ትምህርቱ ከመጀመሩ በፊት በወረቀት ለሚጠየቁት ጥያቄዎች የሚሰጡት መልሶች ሁላችንም ስለሚያጓጓን በመጠባበቅ ተቀምጠናል። ከመምህራችን የቀረበው የዕለቱ ጥያቄ ግን ሌላ ነበር። «ዛሬ ቀኑ ስንት ነው?» የሚል፡፡ ጥር 22 በማለት መለስን፡፡ «ዛሬ የዕለቱ መታሰቢያነት ለማን ነው?» ቀጥሎ ጠየቀን፡፡ መቼም ቅዱስ ዑራኤል መሆኑን አያጣውም፣ ግን ለምን ጠየቀን? በአእምሮዬ የሚመላለስ ጥያቄ ነበር፡፡ ለነገሩ ዕለቱ የተለየ ነገር ቢኖረው ነው እንጂ አይጠይቀንም ነበር፡፡ ይሄን እያሰብኩኝ ዝምታ በሰፈነበት፥ አንድ ልጅ እጁን አነሳና «የመልአኩ የቅዱስ ዑራኤል በዓል ነው» በማለት መለሰ፡፡ መምህራችንም ጥሩ ነው በማለት ተናገረና  «ሌላስ?» አለ በተረጋጋ አንደበት፡፡ ከዚህ በላይ እንኳን የማውቀው ነገር የለም አልኩኝ ለራሴ፡፡
 
ለማንኛውም በዚህ ዕለት ታላቁ አባት ርእሰ መነኮሳት ቅዱስ እንጦንስ ያረፈበት ዕለት ነው፡፡ ጽሌውም (የጽላት ነጥላ ቁጥር) በዋና ከተማችን አዲስ አበባ በምትገኘው መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ይገኛል፡፡ በርግጥ በራሱ ስም የተሰሩ ገዳማትም አሉ። ይህ የአዲስ አበባዉ ግን የእመቤታችን ጽሌ ከመምጣቱ በፊት  በቅዱስ እንጦንስ ስም ይጠራ እንደ ነበር ሁሉ ተነገረን። ይሄንን ስንቶቻችን እናውቅ ይሆን? የእኔ ጥያቄ ነበር። ለምን ለሌሎች አላካፍለውም? ሌላ ጥያቄ፤ እነሆ። (ሥዕል፦ቅዱስ እንጦንስ፥  ከታች በግራ በኩል ቅዱስ እንጦንስና የዋህ ጳውሊ ሲገናኙ )

ቅዱስ እንጦንስ በ25ዐ ዓ.ም ቅማን/Qimn El-Arouse/ በሚባል በማዕከላዊ ግብጽ ነው የተወለደው፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን በቤተክርስቲያን ሳለ ወንጌል ሲነበብ ጌታችን ለባለፀጋው ጎልማሳ የነገረውን «ፍፁም ልትሆን ብትወድ ያለህን ሁሉ ሸጠህ ለድኾች  ሰጥተህ ተከተለኝ» የሚለውን የእግዚአብሔርን ጥሪ ስለሰማ ወላጆቹ ከታናሽ እህቱ ጋር ትተውለት የሞቱትን ሰፊና በመስኖ የሚለማ መሬት ቶሎ ሽጦ ለድሆች ከሰጠ በኋላ እህቱን ለደናግል ማኅበር አደራ ሰጥቶ የብሕትውና ኑሮውን ጀምሯል፡፡

ቅዱስ እንጦንስ በብዙ ተጋድሎና ፈተና በመካከለኛው የግብጽ በረሃ ውስጥ ብቻውን የኖረ ከዚያም ብዙ ተከታዮችን ያፈራ፣ የምንኩስና ሕይወትም ጀማሪ የሆነ አባት ነው፡፡

ቅዱስ እንጦንስ፣ የቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ወዳጁም ነበር፡፡ ርእሰ ባህታውያን የዋህ ጳውሊንም ከፍኖ የቀበረው ቅዱስ አትናቴዎስ በሰጠው ካባ ሲሆን በመልሱም ለቅዱስ አትናቴዎስ የቅዱስ ጳውሊን ለራሱ ከዘንባባ የሠራውን እንደታታ ቅርጫት የመሰለውን ዐፅፍ ልብስ ሰጥቶታል፡፡ ቅዱስ አትናቴዎስም በበዓለ ትንሣኤና በበዓለ ሃምሣ በውስጥ ይለብሳት ነበር፡፡

ቅዱስ እንጦንስና ዘመነ ሰማዕታት

በክርስቲያኖች ላይ መከራና ሞት በዓላውናን ነገሠታትና መኳንንት በታዘዘ ጊዜ ብዙ ክርስቲያኖች ስለ ክርስቶስ ፍቅር እንደበግ እየተነዱ ወደሞት ይሔዱ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ቅዱስ እንጦንስ ከበአቱ ወጥቶ ወደ እስክንድርያ ሔደ÷ ተጠርተንም እንደሁ በእሽቅድምድም ለመሳተፍ አለበለዚያ ተሽቀዳዳሚዎችን ለመጎብኘት እንሒድ በማለት እንጦንዮስ ሰማዕትነትን ለመቀበል ከፍተኛ ጉጉት ነበረው፡፡ ነገር ግን እርሱን የብሕትውናና የምንኩስና ሕይወት አስተማሪ ይሆን ዘንድ ስለ ብዙዎች ጥቅም ጠበቀው፡፡ ሰማዕታት ለፍርድ ሲጠሩ አጅቦ ይሸኛቸዋል÷ እስኪገደሉም ድረስ አይለያቸውም፡፡ ዳኛው ድፍረቱንና የተከታዮቹን ብዛት ጽኑ መንፈሳቸውንም ባየ ጊዜ ማንም መነኩሴ ወደ ፍርድ ቤት አካባቢና በከተማው ውስጥ እንዳይታይ አዘዘ፡፡
እንጦንስ ግን ሰማዕታትን አጅቦ ከፍርድ ቤት ፊት ለፊት ዳኛው ሊያየው በሚችል ስፍራ ተገኘ። ሁሉም በመገኘቱ ሲደነቁ ኃላፊው በትሩን ይዞ ወደ እርሱ መጣ፥ እርሱ ግን የክርስቲያኖችን ጽኑ መንፈስ ያሳይ ዘንድ ምንም ሳይፈራ ቆመ።
 
    ምንጭ፡ ያረጋል አበጋዝ (ዲ/ን) ና አሉላ ጥላሁን ፣ 1997። ነገረ ቅዱሳን 3። ማኅበረ ቅዱሳን፣ አ.አ።

የልደትን ብርሃን መናፈቅ ስብከት፣ ብርሃን ኖላዊ

            በዲ/ን ዘላለም ቻላቸው
መግቢያ

ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ መልእክቱ «በሞቱ እንመስለው ዘንድ ከእርሱ ጋር በጥምቀት ተቀበርን እርሱ ክርስቶስ በአባቱ ጌትነት ከሙታን እንደተነሳ እየተወ እንደ እርሱ አዲስ ሕይወት እንኖራለን» /ሮሜ. 6.4/፤ እንዳለው ክርስትና በጥምቀታችን ከክርስቶስ ጋር ሞተን ከእርሱም ጋር ተነስተን በትንሳኤው ብርሃን በአዲስ ሕይወት የምንመላለስበት የእግዚአብሔርን ፍቅር እየቀመስን ያደረገልንን እያደነቅን ፀጋውን እለት እለት እየተቀበልን፣ እኛ ሞተን ክርስቶስ በእኛ ውስጥ ህያው ሁኖ የምንኖረው ኑሮ ነው፡፡

ይህንንም ዓይነት ኑሮ ለመኖር አምላካችን ያደረገልንን የማዳን ሥራ፣ ስለ ሰው ልጆች ብሎ ያደረጋቸውን ነገሮች ሁሉ /ልደቱን፣ ጥምቀቱን ፣ጾሙን ፣ መከራውን ፣ ስቅለቱን / በተለይም ደግሞ ለትንሳኤያችን በኩር የሆነበትን ትንሳኤውን እና እርገቱን እንዲሁም ዳግም ምጽአቱን ዘወትር ማሰብ ያስፈልጋል፡፡

እነዚህን ድርጊቶች /ነገሮች/ እንደ ትዝታ ማሰብ ብቻ ሳይሆን ልክ በተደረጉበት ወቅት እንደተገኙ ሁኖ መካፈልና መቅመስም የግድ ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም ቅዳሴ ዋነኛው መንገድ ነው፡፡ ቅዳሴ ለማስቀደስ በመሰዊያውና በመስዋእቱ ዙሪያ ስንሰበሰብ ልክ ጌታ በተሰቀለበት በዕለት አርብ በቀራንዮ አደባባይ እንደተገኘን ሆነን እንቆማለን፡፡

በአጠቃላይ ሕይወታችን እነዚህን ነገሮች በማስታወስ፣ በማሰብ እና በመካፈል ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት፡፡

ዳሩ ግን በኃጢአታችን ምክንያት በጥምቀት የተቀበልነውን አዲስ ሰውነት በማቆሸሻችን እና ራሳችንን ከፀጋ በማራቃችን፣ እንዲሁም በተለያዩ አስፈላጊ እና አላስፈላጊ ጉዳዮች ተጠምደን በወከባ በመኖራችን ይህንን ማድረግ ከባድ ይሆን ብናል፡፡

ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን እነዚህን በነገረ ድኅነት ውስጥ ትልቅ ቦታ ያላቸውን ታላላቅ ድርጊቶች ቢያነስ በዓመት አንድ ጊዜ እንድናስባቸው አድርጋለች፡፡ የልደትን፣ የጥምቀትን፣ የስቅለትን፣ የትንሳኤን፣ የዕርገትን … በዓላት የማክበራችን ዋናው ምክንያትም ይኸው ነው፡፡

ነገር ግን አሁንም ቢሆን እነዚህን በዓላት ስናከብር ከሚያስጨንቁንና ህሊናችንን ከሞሉት ነገሮች መልሰን በአንድ ጊዜ ወደ መንፈሳዊ ሃሳብና ተመስጦ መምጣት ስለምንቸገር ቤተ ክርስቲያን ከበዓላቱ በፊት የዝግጅትና የማንቂያ ጊዜያት እና አጽዋማት እንዲኖሩም አድርጋለች፡፡

በእነዚህ ወቅቶች ህሊናችንን ቀስ በቀስ ወደ መንፈሳዊው ሃሳብ እና ወደ በዓሉ ጉዳይ ተመልሶና በዓሉን በናፍቆት ጠብቀን በተገቢው ሁኔታ እንድናከብረው ታደርጋለች፡፡

በዚህም ምክንያት አብዛኞቹ በዓላት ከመከበራቸው በፊት አጽዋማት ይኖራሉ ሥጋ ወደሙን ከመቀበላችንም በፊት እንጾማለን፡፡ ሌሎቹም ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ከመፈፀማቸው በፊት የጾምና የዝግጅት ወቅቶችን ማሳለፍ ጥንታዊ የቤተ ክርስቲያን ትውፊት ነው፡፡

በዚህ ጽሑፍ ርእስ አድርገን የምንነጋገርበት ጾመ ነቢያት ዋነኛ ዓላማም ምእመናንን የጌታችንን የልደት በዓል እንዲያከብሩ ማዘጋጀት ነው፡፡ በተለይም ከልደት በፊት ያሉት ሦስት ሳምንታት ይህ ጎልቶ እንደሚነገርባቸው ቀጥለን እንመለከታለን፡፡

ብሉይ ኪዳን እና ጾመ ነቢያት

የአዳምን በደል ካሳ ከፍሎ ከራሱ ጋር ሊያስታርቀው ወደዚህ ምድር የመጣውና በተዋህዶ ሰው የሆነው እግዚአብሔር ወልድ በዚህ ምድር ላይ በሥጋ የተገለጠው አዳም የድኅነት ቃልኪዳንን ከእግዚአብሔር ከተቀበለ ከብዙ ሺህ ዓመታት በኋላ ነው፡፡

እነዚህ ዓመታት ለሰው ልጆች በኋላ የሚደረገውን የድኅነት ሥራ /ሥጋዌ፣ ሞት፣ ትንሳኤ/ እንዲረዱ ለማስቻል ዝግጅት የተደረገባቸው ዘመናት ናቸው፡፡ በእነዚህ ዘመናት እግዚአብሔር የራሱ የሆኑ ሕዝቦችን እና ሰዎችን በመምረጥና ከእነዚህ ጋር ቃል ኪዳን በመግባት፣ ለእነዚህ ሕዝቦች ተአምራትን በማድረግና ከጠላቶቻቸው በማዳን፣ ከእነዚህም በላይ ደግሞ ነቢያትን በመላክና በእነርሱ አማካኝነት ሕዝቡን በማስተማር፣ ትንቢት በማስነገርና ተስፋ በመስጠት /በማጽናናት/፣ ሱባኤም በማስቆጠር ማንነቱን እና የሰው ልጆችን ለማዳን ያቀደውን ዕቅድ ቀስ በቀስ፣ በጥቂት በጥቂቱ ገልጧል፡፡

በየዘመኑ የተነሱ ነቢያትም ምንም እንኳን አምላክ ይህን ዓለም እንዴት እንደሚያድነው ሙሉ በሙሉ ግልጥልጥ ብሎ ባይረዱትም እግዚአብሔር ዓለሙን የሚያድንበትን ቀን እንዲያቀርበው እንዲህ እያሉ ይማፀኑ ነበር፡፡

– «አቤቱ እጅህን ከሰማያት ልከህ አድነን» /መዝ. 143.17/
– «ሰማያትን ቀደህ ብትወርድ ምነው)» /ኢሳ.64.1/
ቅዱስ ጴጥሮስ በሁለተኛው መልእክቱ እንደሚነግረንም በመንፈስ እየተነዱ ስለሚመጣው ነገር ሁሉ ትንቢት ተናግረዋል፤ ሱባዔ ቀጥረዋል፤ ህዝቡም የጌታን ማዳን በተስፋ እንዲጠብቅ አስተምረዋል፡፡ ጌታ ሰው ሁኖ የተወለደው ከዚህ ሁሉ ዝግጅት በኋላ ነው፡፡ የአዳኙ መሲህ መወለድ በተለይ ከእስራኤል ዘንድ በጉጉት ይጠበቅ ነበር፡፡

በዚህም ምክንያት ከእስራኤል መካከል ቅን የነበሩትና በእግዚአብሔር መንገድ የተጓዙት፤ «መሲሁን አገኘነው»፤ «ሙሴ በህግ መጻሕፍት፣ ነቢያትም ስለ እርሱ የጻፉለትን የናዝሬቱን ኢየሱስን አገኘነው» /ዮሐ. 1.41፣ ዮሐ. 1.45/ እያሉ ተከትለውታል፡፡

እንግዲህ ይህ ታሪክ ከተፈፀመ ጌታችንም ከተወለደ እነሆ ከ2000 ዓመታት በላይ አልፎታል፡፡ እኛም የተደረገውን ሁሉ በትውፊት ተቀብለን በምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን አማካኝነት በዚህ በድኅነት ጉዞ የተሰጡትን ፀጋዎች ተካፍለን ክርስቲያኖች ሆነናል፡፡ በመግቢያችን እንዳየነው ክርስትና እነዚህን ነገሮች ሁሉ ዘወትር እያሰብንና፣ በተመስጦ እንደ አዲስ እየተካፈልን ልንኖረው የሚገባ ኑሮ ነው፡፡

ቤተ ክርስቲያን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል እንዲከበር ያደረገችው ከእነዚህ ዘወትር ልናስባቸው ከሚገቡ ነገሮች አንዱ የሆነውን ብርሃኑንና ዘወትር ልናየው የሚገባውን የጌታችንን ልደትን ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ በተመስጦ እንድናስበውና ብርሃኑን እንድናየው ነው፡፡

ይህችን በዓመት አንድ ጊዜ የምትመጣዋን በዓልም ቢሆን ከማክበራችን በፊት አርባ ሦስት ቀናትን በመጾም እንዘጋጃለን፡፡ በመጾም ብቻ ሳይሆን እነዚህ አርባ ሦስት ቀናት ተከፋፍለው የልደት በዓልን በተገቢው መንገድ እንድናከብር የሚያዘጋጁ ትምህርቶችን እንማርባቸዋለን፡፡ በተለይም ከልደት በዓል በፊት ያሉት ሦስት ሳምንታት ይህ ዓላማ አላቸው፡፡

ቤተ ክርስቲያን የጌታችንን የልደቱን ብርሃን ለማየት እንዘጋጅ ዘንድ እነዚህን ሦስት ሳምንታት የጌታችንን ልደት በናፍቆት መበጠበቅ እንደ ብሉይ ኪዳን ሰዎች ሆነን እንድናሳልፍ ታደርጋለች፡፡

በእነዚህ ሳምንታት /በተለይም በእሑዶቹ/ የብሉይ ኪዳን ነቢያት የአዳኙን መምጣትና የጌታን ቀን መገለጥ በመናፈቅ ስላሳለፏቸው ጊዜያት ደጋግመን በመማር እነዚያን የጨለማ ዘመናት እንድናስታውስና እኛም በእነርሱ መንፈስ ተቃኝተን ያለንበትን ሁኔታ በመመርመርና ዘወትር ልንመላለስበት ያጣነውን ነገር ግን በሃጢአታችን ያጣነውን የልደቱን ብርሃን ለማየት እንድንናፍቅ እንደረጋለን፡፡

ሦስቱን ሳምንታት በዚህ ሁኔታ ካሳለፍንና የልደቱን ብርሃን የማየት ፍላጎታችን ከተነሳሳ በኋላ የልደትን በዓል እናከብራለን፡፡ ደጋግመን እንዳልነውም የልደትን በዓል የምናከብረው እንዳለፈ ታሪክ መታሰቢያ አይደለም፡፡ ልክ በዚያች በልደቱ ቀን ከሰብአ ሰገልና ከእረኞች ጋር እንደተገኘን ሆነን እናከብራለን የልደቱን ብርሃን እናያለን እንጂ፡፡

ለዚህም ነው የልደትን በዓል ስናከብር
«ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደቱ ለክርስቶስ»
«ዛሬ በክርስቶስ ልደት ደስታ ሃሴት ሆነ፡፡» የምንለው፡፡
«ዮም፣ ዛሬ» ማለታችን በዓሉ የልደት መታሰቢያ /ትዝታ/ ብቻ ሳይሆን በዚያ በልደት ቀን እንደነበርን የምንሆንበት መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡

ስብከት፣ ብርሃን፣ ኖላዊ

እነዚህ ከልደተ በዓል በፊት ያሉት ሦስቱ የጾመ ነቢያት ሳምንታት ስብከት፣ ብርሃን እና ኖላዊ ተብለው ይጠራሉ፡፡

እነዚህ ሳምንታት ነቢያት አምላክ ይህንን ዓለም እንዲያድን ያላቸውን ናፍቆት የገለጡባቸው እና ይህንን አስመልክተው ያስተማሩባቸው ሦስት የተለያዩ መንገዶች እና ጌታችንም ለእነዚህ መልስ የሰጠባቸው ሁኔታዎች ይታሰቡባቸዋል፡፡

1. ስብከት

ስብከት ማለት ማስተማር ማለት ነው፡፡ ይህ ሳምንት ከሙሴ ጀምሮ የነበሩ ነቢያት በሙሉ አዳኝ /መሲህ/ እንደሚመጣ ማስተማራቸው ጌታችንም እነርሱ ይመጣል ብለው ያስተማሩለት እኔ ነኝ ብሎ ራሱን መግለጡ የሚታሰብበት ነው፡፡
ሙሴ ለጊዜው የጌታችን ምሳሌ ለሆነው ለኢያሱ ፍጻሜው ግን ለጌታችን በሆነው ትንቢቱ «አምላክህ እግዚአብሔር ከወንድሞችህ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሳልሃል፤ እርሱንም ስሙት፡፡» ብሎ ለሕዝበ እስራኤል ነግሯቸው ነበር፡፡ /ዘዳ. 18.15/

እግዚአብሔር ወልድም በሥጋ ማርያም በተገለጠ ጊዜ ራሱን ያስተዋወቀው ያ ነቢያት የተናገሩለት አዳኝ /መሲህ/ እንደሆነ ነው፡፡ «ሙሴ እና ነቢያት ሁሉ ስለ እኔ ይናገራሉ፡፡» ይላቸው ነበር፡፡

ትንቢቱን ያውቁ የነበሩ በእግዚአብሔር መንገድ የሚሄዱ እስራኤላውያንም «መሲሁን አገኘነው»፣ «ሙሴ በህግ መጻሕፍት፣ ነበያትም ስለ እርሱ የጻፈለትን የናዝሬቱን ኢየሱስን አገኘነው» እያሉ ተከትለውታል፡፡ /ዮሐ. 1.41፣ ዮሐ. 1.45/

ሐዋርያትና ሌሎቹ ደቀመዛሙርቱም ከጌታችን ሞትና ትንሳኤ በተለይ የተነገሩትን ትንቢቶች ሁሉ ያውቁ ለነበሩት እስራኤላውያን ያስተማሩት እነዚህን የነቢያት ትምህርቶች እና ትንቢቶች እየጠቀሱ ነበር፤

ቅዱስ ጴጥሮስን በቤተ መቅደስ እንዲህ ብሎ አስተምሯል፤ «አሁንም ወንድሞቼ ሆይ አለቆቻችሁ እንዳደረጉ ይህን ባለማወቅ እንዳደረጋችሁት አውቃለሁ፡፡ እግዚአብሔር ግን ክርስቶስ መከራን እንዲቀበል በነቢያት ሁሉ አፍ እንደተናገረ እንዲሁ ፈፀመ» /ሐዋ. 3.17-18/፡፡

በሁለተኛው መልእክቱ ደግሞ እንዲህ ሲል ጽፏል፡- «ወንድሞች ሆይ የቀደሙ ቅዱሳን ነቢያት የተናገሩትን ቃልና ለእኛ ለሐዋርያትም ያዘዘውን የመድኃኒታችንና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ትእዛዝ ታስቡ ዘንድ… ዕወቁ» /2ኛ ጴጥ. 3.1-3/

ቅዱስ ጳውሎስም በዕብራውያን መልእክቱ መግቢያ ላይ እንዲህ ብሏል፤ «ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዐይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናገረ፤ በኋላ ዘመን ግን ሁሉን ወራሽ ባደረገው፣ ሁሉን በፈጠረበት በልጁ ነገረን፡፡» /ዕብ. 1.1-2/

2. ብርሃን

ነቢያት የአምላክን ማዳን ከጠበቁባቸው እና ከገለጡባቸው መንገዶች አንዱ ብርሃን ነው፡፡ ዘመነ ብሉይ መከራ ሥጋ፣ መከራ ነፍስ የፀናበት፣ ሁሉ ነገር አስጨናቂ የሆነበት፣ ሰው ብርሃን ከሆነው አምላክ ጋር የተራራቀበት ስለነበር ያሉበትን ዘመን «ጨለማ» ብለው በመግለጥ ይህንን ጨለማ የሚያስወግድና ወደ ትክክለኛው መንገድ የሚመራ ብርሃን እንዲመጣ እንዲህ እያሉ ይፀልዩ ነበር፡፡

«ብርሃንህንና ጽድቅህን ላክ፣ እነርሱም ይምሩኝ፣
አቤቱ ወደ መቅደስህ ተራራና ወደ ማደራያህ ይውሰዱኝ» /መዝ. 42.3/
ጌታችንም ወደዚህ ዓለም በመጣ ጊዜ ለዚህ መልስ ሰጥቷል፤
«እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ» /ዮሐ. 8.12/
ደቀመዛሙርቱም ስለ ብርሃንነቱ በመመስከር ተባብረዋል፤

– ቅዱስ ዮሐንስ ስለጌታችን ሰው መሆን /ሥጋዌ/ በተናገረበት በወንጌሉ የመጀመሪያ ክፍል ጌታችንን ብርሃን ብሎታል፤ «ሕይወት በእርሱ ነበረ፣ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረ፤ ብርሃንም በጨለማ ያበራል፤ ጨለማም አላሰነፈውም» /ዮሐ. 1.4-5/

ቅዱስ ጳውሎስም ጌታችን በሚያንፀባርቅ ብርሃን አምሳል እንደተገለጠበት ተናግሯል፡፡ «እኩል ቀን በሆነ ጊዜ በመንገድ በሄደ ከፀሐይ ይልቅ የሚበራ መብረቅ በእኔና ከእኔ ጋር ይሄዱ በነበሩት ላይ ከሰማይ ሲያንፀባርቅ አየሁ፤ … አንተ የምታሳድደኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ አለኝ፡፡» /ሐዋ. 26.13/

3. ኖላዊ

ኖላዊ ማለት እረኛ ማለት ነው፡፡ ነቢያቱ ራሳቸውን እና ሕዝበ እስራኤልን ብሎም ዓለምን እረኛቸው እንደተዋቸው እና እንደተቅበዘበዙ በጎች በመቁጠር እንዲሰበስባቸውና እንዲያሰማራቸው እንዲህ እያሉ እራሳቸውን ይማፀኑ ነበር»

«ዮሴፍን እንደ መንጋ የምትመራ የእስራኤል ጠባቂ /እረኛ/ ሆይ፣ አድምጥ በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ ተገለጥ፡፡» /መዝ. 79.1/

ጌታችንም ለዚህ ጥያቄ እንዲህ ሲል መልስ ሰጥቷል፤ «ቸር ጠባቂ /እረኛ/ እኔ ነኝ፡፡ ቸር ጠባቂ ስለ በጎቹ ነፍሱን ይሰጣል፡፡»  /ዮሐ10.11/

ምን እናድርግ ?

ዛሬም እኛ በኃጢአታችንና በምታዋክበን ዓለም ምክንያት ዘወትር ልናየውና ልንመላለስበት የሚገባን ብርሃነ ልደቱ ተሰውሮብናል፣ ከቸር እረኛችን የራቅን የተቅበዘበዝን በጎች ሁነናል፡፡ በምናስበው ሃሳብ፣ በምንሰራው ሥራ ውስጥም የአምላክ ሰው መሆን ቦታ የለውም፡፡ የምንኖረው ልክ ክርስቶስ እንዳልተወለደ /as if Christ was not born/ ነው፡፡ ስለዚህ እኛም እንደ ብሉይ ኪዳን ሰዎች ያጣነውን ይህንን ፀጋ ለማግኘት፣ ብርሃነ ልደቱን ለማየት፣ በዚያ ውስጥም ለመመላለስ የክርስትናችንን እና የመንፈሳዊነታችንን ጥልቀት ለመጨመር መሻት አለብን፡፡

ስለዚህ እስኪ እኛም በእነዚህ ሳምንታት የብሉይ ኪዳን ሰዎች የነበሩበትን ሁኔታ እየተዘከርን፣ እኛም ያለንበትን ሁኔታ እየመረመርን፣ ስላጣነው ብርሃን ለማሰብ፣ ያጣነውን መልሰን ማየትንና ማግኘትን ለመናፈቅ እንሞክር፡፡ መጻሕፍትን ለማንበብ፣ በጉዳዩ ላይ በተመስጦ ለማሰብ እና ለመወያየት ጊዜ እንውሰድ፡፡ ብርሃነ ልደቱን ለማየት እንዲያበቃን «አቤቱ ብርሃንህንና ጽድቅህን ላክ፤ ቸሩ እረኛችን ሆይ፣ ተቅበዝብዘናልና እባክህ ሰብስበን» እያልን እንፀልይ፡፡ ሰው ከነኃጢአቱ ወደ እግዚአብሔር ብርሃን ሊቀርብ /ሊያየው/ አይችልምና ራሳችንን በንስሃ እናድን፡፡ እነዚህን ቤተ ክርስቲያን ያስቀመጠችልንን የዝግጅት ጊዜያት በሚገባ ከተጠቀምን ትርጉም ያለው፣ በሕይወታችንና በመንገዳችን ላይ ለውጥ የሚያመጣ ልዩ የልደት በዓል እናከብራለን፡፡

አምላካችን ብርሃነ ልደቱን እንድንመለከት ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ሰሙነ ሕማማት

በመ/ር መንግሥተአብ አበጋዝ

በነቢዩ ኢሳይያስ «ነስአ ደዌነ ወፆረ ሕማመነ፤ በእውነት ደዌአችንን ተቀበለ፣ ሕመማችንንም ተሸከመ፣ እኛ ግን እንደተመታ፣ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሰፈ፣ እንደተቸገረም ቆጠርነው፡፡ እርሱ ግን ስለመተላለፋችን ቆሰለ፣ ስለ በደላችንም ደቀቀ፣ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፣ በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን፡፡» /ኢሳ. 53፣4-7/ ተብሎ የተነገረው ቃል ተፈጽሞ፣ ጌታችን ለድኅነተ ዓለም ሲል በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ የተቀበለው ጸዋትወ መከራ የሚዘከርበት ሳምንት ነው፡፡ ከሆሣዕና ማግስት እስከ ትንሣኤ ያለው የጾመ እግዚእነ መዝጊያ ሳምንት ሰሙነ ሕማማት ይባላል፡፡

በሰሙነ ሕማማት ካህናትና ምእመናን በአጸደ ቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው፣ ከሐሜት፣ ከነገርና ከኃጢአት ርቀው፤ የሕማሙን ነገር የሚያወሳውን ዜማ ሲያዜሙ፣ ግብረ ሕማም በመባል የሚታወቀውን መጽሐፍ ሲያነቡ፣ ሲሰሙ፣ ሲሰግዱና ሲጸልዩ ይሰነብታሉ፡፡ ካህናትና ምእመናን በቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ወዛቸው ጠብ እስኪል ድረስ በነግህ፣ በሠለስት፣ በስድስት፣ በተሰዓት /በዘጠኝ/ ሰዓት፣ በሰርክ /በዐሥራ አንድ/ ሰዓት መላልሰው ሲሰግዱና ሲጸልዩ ይሰነብታሉ፣ በተለይም ካህናት በማንኛውም አገልግሎት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፣ ምክንያቱም ጌታችን የደረሰበትን መከራ ሥቃይን እና 5ሺ 5መቶ ዘመን የሰው ልጅ በጨለማ ግዞት ይኖር እንደነበር ለማዘከር ነው፡፡ ሰሙነ ሕማማት የጌታችንን ሕማማት ከማሰብ ጋር በርካታ ድርጊቶች መፈጸማቸውንም የምናስታውስበት ሳም ንት ነው፡፡ በዕለት በዕለት ከፍለን በየትኛው ቀን ምን ተደረገ እያልን እንጠይቅ?

ሰኞ፡-ጌታችን የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ በምትባል መንደር ያድራል በማግስቱም ከቢታንያ ሲወጣ ተራበ /ማር. 11፣11-14/ ቅጠል ያላትን በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፣ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ከአሁን ጀምሮ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ ብሎ ረገማት፡፡ በዚህ ምክንያት ይህ ዕለት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል፡፡

ትርጓሜ፤ በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ናት፤ ፍሬ የተባለች፣ ሃይማኖትና ምግባር ናት፡፡ ከእስራኤል ፍቅርን፣ ሃይማኖትን፣ ምግባርን ፈለገ አላገኘም፡፡ እስራኤልን ሕዝበ እግዚአብሔር መባልን እንጂ፣ ነቢይነት፣ ካህንነት፣ መሥዋዕት አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፡፡ በመርገሙ ምክንያት ትንቢት ክህነት መሥዋዕት ከቤተ እስራኤል ጠፉ፡፡

በለስ ኦሪት ናት፡- ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት ኦሪትና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ በማለት ፈጸማት፤ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና ፍሬ ባንቺ አይሁን አላት፤ ድኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡ በአዲስ ኪዳን የድኅነት ዘመንም ተተካች፡፡

በለስ ኃጢአት ናት፡፡ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሠሩት ደስ ደስ ያሰኛል ኋላ ግን ያሳዝናል፡፡ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም፤ በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ለማለት ነው፡፡ በለሷም ስትረገም ፈጥና መድረቋ፣ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በእርሱ እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡

ከዚህ ቀጥሎ ወደ ቤተ መቅደስ ሔደ፤ ቤተ መቅደስ ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምሥያጥ /የንግድ ቤት/ ሆኖ ቢያገኘው፤ «ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች… እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት» ማቴ.21፣13 ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸዉ፣ ገርፎም አስወጣቸዉ፣ ይህም የሚያሳየዉ ማደሪያው ቤቱ የነበርን እኛ የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡ ከዚህም የተነሣ አንጽሖተ ቤተ መቅደስ የተፈጸመበት ሰኞም ይባላል፡፡

 ማክሰኞ፡- ሰኞ ባደረገው አንጽሖተ ቤተመቅደስ ምክንያት፣ ሹመትን ወይም ሥልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠ ጌታችን፣ ስለ ሥልጣኑ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋልና፤ የጥያቄ ቀን ይባላል፡፡

ጥያቄውም ከምድራውያን ነገሥታት፣ ከሌዋውያን ካህናት ያይደለህ ትምህርት ማስተማር፣ ተአምራት ማድረግ፣ ገበያ መፍታትን፣ በማን ሥልጣን ታደርጋለህ? ይህንንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ? የሚል ነበር፡፡ /ማቴ. 21፣23-27፣ ማር. 11፣7-35፣ ሉቃ. 21፣23-27፣ ማር. 11፣27-33፣ ሉቃ. 20፣1-8/፤ እርሱም ሲመልስ፤ «እኔም አንድ ነገር እጠይቃችኋለሁ፣ እናንተም ብትነግሩኝ በማን ሥልጣን እነዚህን እዳደርግ እነግራችኋለሁ፡፡ የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረ፣ ከሰማይን? ወይስ ከሰዉ? በእግዚአብሔር ፈቃድ፣ ወይስ በሰው ፈቃድ?» አላቸው፡፡ እነርሱም ከሰማይ ብንል ለምን አልተቀበላችሁትም ይለናል፤ ከሰው ብንል ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስን እንደ አባት ያከብሩታል፣ እንደ መምህርነቱ ይፈሩታልና ሕዝቡን እንፈራለን፤ ተባብለው ከወዴት እንደሆነ አናውቅም ብለው መለሱለት፡፡ እርሱም እኔም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ አልነግራችሁም አላቸው» ይህንንም መጠየቃቸው እርሱ የሚያደርጋቸውን ሁሉ በራሱ ሥልጣን እንዲያደርግ አጥተዉት አልነበረም፣ ልቡናቸው በክፋትና በጥርጥር ስለተሞላ እንጂ፡፡

በማቴ. 21፣28፣ ምዕ. 25፣46፣ ማር. 12፣2፣ ምዕ. 13፣37፣ ሉቃ. 20፣9፣ ምዕ. 21፣38 የሚገኙት ትምህርቶች ሁሉም የማክሰኞ ትምህርት ይባላሉ፡፡ በዚህ ዕለት በቤተ መቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረ፣ የትምህርት ቀንም ይባላል፡፡ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ከሥጋዊ ነገር ርቆ በዚህ ሰሞን የሃይማኖት ትምህርት ሲማር ሲጠይቅ  መሰንበቱ መጽሐፋዊ ሥርዓት ነው፡፡

ረቡዕ፡- ምክረ አይሁድ ይባላል፡፡ ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን ነውና፡፡ በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ፣ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ፣ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለ ነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡ በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ፣ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል፡፡ /ማቴ. 26፣1-14፣ ማር. 14፣1-2፣ ቁ 10፣11፣ ሉቃ. 22፣1-6/፤ የሐዲስ ኪዳን ካህናትና ምእመናን በዚሁ ዕለት በቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው መላ ሰውነታቸውን ለእግዚአብሔር አስገዝተው የሞት ፍርዱን በማሰብና በማልቀስ፣ ሐዋርያት ከጌታችን መያዝ በኋላ በኀዘን በፍርሐት እንደነበሩ እያሰቡ መጻሕፍትን በማንበብ በጾም፣ በጸሎ ትና በስግደት ተወስነው ይቆዩና ከአሥራ ሁለት ሰዓት በኋላ ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ፡፡

የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል፡፡ ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ፣ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት፣ /ባለሽቱዋ ማርያም/፤ «ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ፣ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ» ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ፣ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ፣ በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሔድ በጠጉሩ /በራሱ/ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው ነው፡፡ ረቡዕ የመዓዛ ቀን የተባለው፡፡

ረቡዕ የእንባ ቀንም ይባላል፡፡ ማርያም እንተ እፍረት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ፣ መላ ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት በእንባዋ እግሩን አጥባዋለችና፤ በጠጉሯም በእንባዋ ያጠበችውን እግሩን አብሳዋለችና፡፡ /ማቴ. 26፣6-13፣ ማር. 14፣.9፣ ዮሐ. 12፣8/ ኃጢአትን በማሰብ ማልቀስና ራስን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ማቅረብን ከምታስተምረን ማርያም እንተ እፍረት እንባን ለንስሐ ሕይወት ልንጠቀምበት ይገባል፡፡

ሐሙስ፡- በቤተ ክርስቲያን የተለያዩ ስያሜዎች ያሏቸው በርካታ ድርጊቶች የተፈጸሙበት ዕለት ነው፡፡

ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፡፡ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን የተዋሐደ አምላክ፣ መሆኑን ለመግለጥና ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ ሲጸልይ ያደረበት ነውና ጸሎተ ሐሙስ ተባለ፡፡ /ማቴ. 26፣36-46 ዮሐ. 17/፡፡

ሕፅበተ ሐሙስ ይባላል፡፡ ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀ መዛሙርቱን እግር በፍጹም ትሕትና ዝቅ ብሎ አጥቧል፡፡ ይህም የሚያሳየው የዓለምን ሁሉ ኃጢአት ለማጠብ የመጣ መሆኑን ነው፡፡ ይህን ለማስታወስ ዛሬም ካህናት በተለይም ሊቃነ ጳጳሳትና የደብር አስተዳዳሪዎች፤ «በመካከላችን ተገኝተህ የእኛንና የሕዝብህን ኃጢአት እጠብ እኛም የአንተን አርአያ አንዘነጋም የሌላውን እግር እናጥባለን፤» ሲሉ በቤተ ክርስቲያን የተገኙትን ምእመናንን እግር በወይንና በወይራ ቅጠል ያጥባሉ፡፡

የምስጢር ቀን ይባላል፡፡ ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ በዚህ ዕለት ተመሥርቷልና፡፡ ይኸውም «ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ሥጋዬ ነው፡፡ እንካችሁ ብሉ» ጽዋውንም አንስቶ አመሰገነ «ይህ ስለ እናንተ ነገ በመስቀል የሚፈስ ደሜ ነው ከእርሱም ጠጡ» በማለት፤ እኛ ከእርሱ ጋር፣ እርሱ ከእኛ ጋር አንድ የምንሆንበትን ምስጢር ከጠላት ዲያብሎስ ሰውሮ፣ ለደቀመዛሙርቱ የገለጠበት ቀን በመሆኑ የተሰጠ ሥያሜ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በንስሐ ታጥቦ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለመቀበል ይዘጋጃል፡፡

የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡፡ ምክንያቱም መሥዋዕተ ኦሪት ማለትም በእንስሳት ደም የሚቀርበው መሥዋዕት ማብቃቱን ገልጦ፣ ለድኅነተ ዓለም ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ «ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን ሐዲስ ኪዳን ነው፡፡ ከእርሱ ጠጡ» በማለቱ ይታወቃል /ሉቃ. 22፣20/ ኪዳን ማለት በሁለት ወገን መካከል የሚደረግ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ጌታችን ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ዘለዓለማዊውን ቃል ኪዳን በራሱ ደም የፈጸመበት ዕለት ስለሆነ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ተባለ፡፡

የነጻነት ሐሙስ ይባላል፡፡ ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱ፣ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ ጌታችን ስለ ሰው ልጅ ነጻነት ሲናገር «ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም ባርያ ጌታዉ የሚያደርገውን አያውቅምና ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ» በማለት /ዮሐ. 15፣15/፤ ከባርነት የወጣንበት ልጆች የተባል በትን ቀን የምናስብበት በመሆኑ ሊቃውንቱ የነጻነት ሐሙስ አሉት፡፡ እያንዳንዱ ክርስቲያንም ከኃጢአት ባርነት ርቆ፣ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያወዳጀውን መልካም ሥራ በመሥራት  ሕይወቱን መምራት ይኖርባታል፡፡ ባሮች አልላችሁም ተብለናልና፡፡

የጸሎተ ሐሙስ ምስጢራት በብሉይ ኪዳን

ለፋሲካ ዝግጅት ተደርጎበታል፡፡ ዝግጅቱም በሦስቱ ወንጌላት ላይ ተመዝግቧል /ማቴ. 26.7-13/፡፡ ፋሲካ ማለት ማለፍ ማለት ነው፡፡ ይኸውም እስራኤላውያን በግብፅ ምድር ሳሉ መልአኩን ልኮ እያንዳንዱ እስራኤላዊ የበግ ጠቦት እንዲያርድና ደሙን በበሩ ወይም በመቃኑ እንዲቀባ ለሙሴ ነገረው፡፡ ሙሴም ለሕዝቡ ነገረ፣ ሁሉም እንደታዘዙት ፈጸሙ፡፡ መቅሰፍት ከእግዚአብሔር ታዞ መልአኩ የደም ምልክት የሌለበትን የግብፃውያንን ቤት በሞተ በኲር ሲመታ፣ የበጉ ደም ምልክት ያለበትን የእስራኤላውያንን ቤት ምልክቱን እያየ ማለፉን ለማመልከት ነው፡፡ /ዘጸ. 12፣1-20/፡፡ በዚህ መነሻነት በየዓመቱ እስራኤላውያን በመጀመሪያ ወራቸው በ14ኛው ቀን በግ እያረዱ የፋሲካን በዓል ያከብራሉ፡፡ ሀገራችንም አስቀድማ ብሉይ ኪዳንን የተቀበለች ሀገር እንደመሆኗ ይህ ድርጊት ይፈጸምባት ነበር፡፡ በሐዲስ ኪዳንም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ፋሲካ ተብሎ የተጠራበት ምክንያት በዚህ በፋሲካ በዓል ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ደሙን ስላፈሰሰልን ነው፡፡ በደሙ መፍሰስ ሞተ በኲር የተባለ ሞተ ነፍስ ርቆልናልና፡፡ «ፋሲካችንም ክርስቶስ ነው» /1ቆሮ. 5፣7 1ጴጥ. 1፣18-19/

በዚህ ዕለት እንደ ማክሰኞ ሁሉ በዮሐ. 14፣16 የሚገኘውን ለደቀመዛሙርቱ ረጅም ትምህርት አስተምሯል፡፡ የትምህርቱም ዋና ዋና ክፍሎች ምስጢረ ሥላሴ የሦስትነት ትምህርት፣ ምስጢረ ሥጋዌ /የአምላክ ሰው መሆን/፣ ምስጢረ ትንሣኤ ሙታን /የዳግም ምጽአቱን ነገር/ ነው፡፡ እነዚህን ትምህርቶች በስፋትና በጥልቀት መማር እንደሚገባ ሲያስረዳ፣ በተአምራት ሊገልጥላቸው ሲችል በረጅም ትምህርት እንዲረዱት አድርጓል፡፡ ደቀ መዛሙርቱም እሱ እያስተማራቸው ሳለ ያልገባቸውንም እየጠየቁ ተረድ ተዋል፡፡ ምእመናንም በቤተ ክርስቲያን ተገኝተን መማርና ያልገባንን ጠይቆ መረዳት እንደሚገባን እንማራለን፡፡ በዚሁ ዕለት ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ራሱን ለአይሁድ አሳልፎ የሰጠበት ቀን ነው፡፡ ማቴ. 26፣47-58

ዓርብ-

የስቅለት ዓርብ ይባላል፡፡ የዓለም ሁሉ መድኃኒት የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ መዋሉን ለማስታወስ ነው፡፡ /ማቴ. 27፣35/፡፡

መልካሙ ዓርብ ይባላል፡፡ ይህም የሚያስገነዝበን ከስቅለተ ክርስቶስ በፊት አንድ ሰው ሲያጠፋ ተሰቅሎ ይሞታል፡፡ በሮማውያን ሕግ መስቀል የወንጀለኞች መቅጫ ምልክት ነበር፡፡ በዚህ ዕለት የወንጀለኞች መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምሕረት ምልክት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያብሎስ ድል መንሻ ስለ አደረገው፣ በሞቱ መልካሙን ሕይወትን ስለአገኘን መልካሙ ዓርብ ተብሏል፡፡

የትንሣኤን በዓል ለማክበር ወደ ኢየሩሳሌም የሚሔዱ ምእመናን ሁሉ በዕለተ ዓርብ መከራውን ለማሰብ ከቤተ ጲላጦስ እስከ ጎልጎታ መቃብረ ክርስቶስ ድረስ ጉዞ ያደርጋሉ፡፡ ጉዞ የሚደረግባቸውም አሥራ ሦስቱ ሕማማተ መስቀል የተፈጸሙባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡

በዚህ ዕለት በቤተ ክርስቲያን ተገኝተው መከራውን በማሰብ ሲሰግዱ የሚውሉ እንዳሉ ሁሉ፤ በአንጻሩ ደግሞ በስም ክርስቲያን ተብለን ከምንጠራው መካከል፣ ተድላ ደስታ በሚፈጸምባ ቸው ሥፍራዎች ክፉ ሥራ ስንፈጽም የምንውል አንጠፋም፡፡ እንዲህ የምናደርግ ሁሉ በአለፈው ልንጸጸትና በቀሪ ዘመናችን ልንታረም ይገባል፡፡ በዓመት አንዴ የምናገኘው ይህ ዕለት ቀራንዮን የምናስብበት፤ ነገረ መስቀሉን የምናስተውልበት እንጂ ስለ ምድራዊ ኑሮአችን ስንባክን ኃጢአት ስንሠራ የምንውልበት ሊሆን አይገባም፡፡

ቅዳሜ-

ቀዳም ሥዑር ይባላል፡፡ በዚች ዕለት ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምት ውል የተሻረችው ቅዳሜ ተብላለች፡፡

ለምለም ቅዳሜ ካህናቱ ለምእመ ናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሠይሟል፡፡ ቀጤ ማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡

ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል፡፡ ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው  ሁሉ ያረፈበት ሲሆን፤ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን  ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷ ታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘ ለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡ የዕለታ ቱን ክብርና ሥያሜ ከማወቅና ከመ ረዳት ጋር በዕለታቱ የታዘዙትን ሃይማኖታዊ ግዴታዎችን መወጣት ከሁላችንም ይጠበቃል፡፡

ምንጭ- መጽሐፈ ግብረ ሕማማት
-ሐመርና መለከት መጽሔቶች
ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ እግዚአብሔር በሰላም

ዕለታተ ሰሙነ ሕማማት ወምስጢራት

በዲ.ቸሬ አበበ

 

ከአባታችን አዳም በደል ወይንም ስሕተት በኋላ በሕማማት፣ በደዌያት፣ በመቅሰፍታት፣ ወዘተ በብዙ መከራ የሰው ልጅ ሊኖርባቸው ግድ የሆነባቸው ዘመናት ጥቂቶች አልነበሩም፡፡ ጥሮ ግሮ ወጥቶ ወርዶ ለፍቶ ማስኖ የዕለት ጉርስ የቀን ልብስ ማግኘት እጅግ አዳጋች ነበር፡፡ ሁልጊዜ የሰው ልጅ ቢያጠፋ ቢበድል ከሕገ እግዚአብሔር ቢወጣ እንኳ የዋህ፣ ታጋሽ፣ ቸር፣ አዛኝ የሆነ አምላክ የጠፋውን ሊፈለግ የተራበውን ሊያጠግብ የታረዘውን ሊያለብስ፣ ፍቅር ያጣውን ፍጹም ፍቅር ሊለግስ፣ ሰላም ለሌለው ፍጹም ሰላም ሊሰጥ፣ ተስፋ የሌለውን ተስፋ ሊያጐናጽፍ ከሰማይ ወረደ፤ ከድንግል ማርያም ተወለደ፤ በገዳመ ቆሮንቶስ አርባ ቀንና ሌሊት ጾመ፡፡ በጾሙም የኃጡአት ሥሮች ወይም ራሶች የተባሉትን ስስትን፣ ትዕቢትንና ፍቅረ ንዋይን ድል አደረገልን፡፡ እኛ እርሱ የጾመውን ጾም እንድናከብር እንድንጾም ምሳሌ ሆነን፡፡ ዲያብሎስን ድል አድርጐ ድል እንድንነሣው ኃይልና ምሳሌ ሆነን፡፡
 
ሰሙነ ሕማማት ምንድን ነው?

ሰመነ ስምንት /ሳምንት/ አደረገ ማለት ነው፡፡ ይኸውም ከዕለተ ሆሣዕና ሰርክ እስከ ትንሣኤ ሌሊት ያለውን ጊዜ ወይም ቀናት የሚያመለክት ነው፡፡ ሐመ ማለት ታመመ ማለት ሲሆን ይህም የሰውን ዘር ሁሉ ከዲያብሎስ ባርነት ነፃ ለማውጣት ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈቃዱ የተቀበላቸውን ጸዋትወ መከራዎች የሚያሳስብ ነው፡፡ ዕለታቱ የዓመተ ኩነኔ ወይም የዓመተ ፍዳ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ክርስቲያኖች የክርስቶስን ውለታ እያሰቡ እጅግ የሚያዝኑበት፣ የሚያለቅሱበት፣ የሚሰግዱበት ቤት ንብረታቸውን ትተው ከሌላው ቀናትና ጊዜያት በተለየ መልኩ ቤተ ክርስቲያናቸውን የሚማጸኑበት፤ ጧት ማታ ደጅ የሚጠኑበት፤ ኃጢአታቸውን በቤተ ክርስቲያን አደባባይ ለካህኑ የሚናዘዙበት በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚገኝ ሳምንት ነው፡፡

በዚህ ሳምንት ብዙ አዝማደ መባልእት አይበሉም፤ ይልቁን በመራብ በመጠማት በመውጣት በመውረድ በመስገድ በመጸለይ በመጾም በየሰዓቱ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸዋትወ መከራዎች በማሰብ አብዝቶ ይሰገዳል፡፡ መከራውን፣ ሕማሙን፣ ድካሙን የሚያስታውሱ ከቅዱሳት መጻሕፍት ኢሳይያስ፣ ኤርምያስ መዝሙረ ዳዊት ግብረ ሕማማት ወዘተ በየሰዓቱ ይነበባል፡፡
መስቀል መሳለም የለም፡፡ ካህናትም እግዚአብሔር ይፍታህ አይሉም የሳምንቱ ሥርዓተ ፍትሐት አይደረግም፡፡ ይኸውም ይህ ሳምንት ከሞት ወደ ሕይወት የተሸጋገርንበት ከጨለማ ወደ ብርሃን የተጓዝንበት የመሸጋገሪያ ወቅት ምሳሌ በመሆኑ ነው፡፡ በዕለተ ምጽአት መላእክት የመለከት ድምጽ በማሰማት የዳግም ምጽአትን ዕለት ለማሳሰብ ምእመናን ጥሪውን ሰምተው ለዚህም አስቀድመው ተዘጋጅተው የበዓሉ ታዳሚዎች መሆናቸውን በማጠየቅ በዚህ ሳምንት ዲያቆኑ ቃጭል እየመታ በየሰዓቱ ምእመናኑን ያሳስባል፡፡

በሰሙነ ሕማማት የሚገኙ ዕለታትና ስያሜያት

ዕለተ ሰኑይ /ሰኞ/
ይህ ዕለት አንጾሖተ ቤተ መቅደስ /የቤተ መቅደስ መንጻት/ እና መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፡፡ /ማር.11-11፣ ማቴ.21-18-22 ሉቃ.13-6-9/፡፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ «ወመሰለ ሎሙ ወይቤሎሙ አሐዱ ብእሲ በለሰ ቦቱ ውስተ አጸደ ወይኑ ወየሐውር ይንሣእ ፍሬሃ ወኢይረክብ …»፤ ይህንም ምሳሌ አለ ለአንድ ሰው በወይኑ አትክልት የተተከለች በለስ ነበረችው ፍሬም ሊፈልግባት ወጥቶ ምንም አላገኘም፡፡ በማለት በበለስ ስለተመሰለ የሰው ልጅ ሕይወት በማሰብ እንዲመለስ ንስሐ እንዲገባ በሕይወትም እንዲኖር እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ማሳሰቡን ያጠይቃል፡፡ ንስሐ አልገባም አልመለስም ያለም በለሷ እንደጠወለገችና እንደተቆረጠች ሁሉ ፍሬ ባለማፍራታቸው እንደሚቆረጡ እንዲሁም ወደ እሳት እንደሚጣሉ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስረዳል፡፡ በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ፍሬ የተባለ ደግሞ ሃይማኖትና ምግባርን ነው፡፡ ሁላችን ቤተ እስራኤላውያን ፍሬ ሃይማኖት ወምግባር አስተባብረን ይዘን መገኘት ይገባናል፡፡ ፍሬ አልባ እንዳንሆን ጌታ ሲመጣም እንዳናፍር የመጽሐፉን ቃል ልንጠብቅና ልንፈጽም ይገባናል፡፡ በዚህ የሕማማት የመጀመሪያ ቀን ዕለተ ሰኑይ የምናስበው የምንዘክረው የሰው ልጅ ሕይወት በከንቱ በቸልተኝነት እንዳይደክም እንዳይጠወለግ እንዳይደርቅ ወደ እሳትም እንዳይጣል ማድረግ ይገባናል፡፡
ዕለተ ሠሉስ /ማክሰኞ/
ይህ ቀን ጌታችን ሰኞ በተናገረውና ባደረገው ላይ አይሁድ ጥያቄ ያቀረቡበት እርሱም መልስ በመስጠት ያስተማረበት ዕለት ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የጥያቄ እና የትምህርት ቀን በመባል ይታወቃል፡፡ ጥያቄውም ጌታ ባደረገው አንጽሖተ ቤተ መቅደስ ምክንያት ለጸሐፍትና ፈሪሳውያን ይኸውም ትምህርት ማስተማር፣ ተአምራት ማድረግ፣ ገበያ መፍታትን በማን ሥልጣን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ?» የሚል ነበር፡፡ /ማቴ.21-23-27/፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ማቴዎስ «ወይቤሎሙ ኢየሱስ አማን እብለክሙ ከመ መጸብሓውያን ወዘማውያት ይቀድሙክሙ ውስተ መንግሥተ እግዚአብሔር»፤ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው እውነት እላችኋለሁ ቀራጮችና ጋለሞቶች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በመግባት ይቀድሙአችኋል ሲል አስተምሯል፡፡ /ማቴ.21-28/
ዕለተ ረቡዕ

ይህ ዕለት ደግሞ የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚችሉ ምክር የጀመሩበት ቀን ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ዕለቱ የምክር ቀን በመባል ይጠራል፡፡

ዕለተ ሐሙስ
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዕለት ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑን ለመግለጥ እና ለአርአያነት ጸሐፍት ፈሪሳውያን የአይሁድ ካህናት መጥተው እስኪይዙት ድረስ ሲጸልይ በማደሩ ምክንያት ጸሎተ ሐሙስ በመባል ይታወቃል፡፡ ትሕትና ፍቅር መታዘዝ እንዲሁም የአገልግሎትን ትርጉም ለማስረዳትና ለማስገንዘብ የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠቡ ሕጽበተ ሐሙስ በመባልም እንደሚጠራ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ይናገራሉ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስም «ወሶበ ኀፀቦሙ እገሪሆሙ ነሥአ አልባሲሁ ወረፈቀ ካዕበ ወይቤሎሙ አእመርክሙኑ ዘገበርኩ ለክሙ … ወሶበ አነ እንከ ሊቅክሙ ወእግዚእክሙ ኀፀብኩክሙ እገሪክሙ ከማሁኬ አንትሙኒ ይደልወክሙ ትኅፅቡ እግረ ቢጽክሙ፡፡»፤ «እግራቸውንም አጥቦ ልብሱንም አንሥቶ ዳግመኛ ተቀመጠ እንዲህም አላቸው ያደረግሁላችሁን ታስተውሉታላችሁን?… እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ እናንተ ደግሞ እርስ በእርሳችሁ ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል ሲል ተናግሯል፡፡ /ዮሐ.13-12-20/፡፡
ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ሥጋዬ ነው እንካችሁ ብሉ፤ ይህ ስለ እናንተ የሚፈስ ደሜ ነው ከእርሱ ጠጡ በማለት ምሥጢረ ቁርባንን የመሠረተበት ወይም ራሱ ምስጢረ ቁርባንን የጀመረበት ቀን በመሆኑ የምስጢር ቀን ተብሎ ይጠራል፡፡ ይኸውም የሰው ልጆች ሥጋውንና ደሙን ተቀብለን ከእርሱ ጋር አንድነትና ኅብረት እንዲኖረን ጥንተ ጠላት ዲለብሎስንም ፍጹም ድል ነሥተን ሰማያዊት ርስት መንግሥተ ሰማያትን እንድንወርስ ለማስቻል ነው፡፡ /ማቴ.26-26-29/፡፡
አይሁድ ጌታችንን ለመያዝ በእነርሱ ጥበብና ፍላጐት ቀስ ብለው መጥተው የያዙበት ቀን ስለሆነ በዚህ ዕለት በለሆሳስ /ብዙ የድምጽ ጩኸት ሳይሰማ/ የቅዳሴ ሥርዓት ይፈጸማል፡፡ ስለሆነም መላው ሕዝበ ክርስቲያን በዚህ የሕጽበት፣ የምስጢር፣ የጸሎት ቀን በተባለው በዚህ ዕለት በንስሓ ታጥበው ሥጋ ወደሙ እንዲቀበሉ ቤተ ክርስቲያን በአጽንኦት ታስተምራለች፡፡
ዕለተ ዐርብ
ሐዋርያው ቅዱስ ጳዉሎስ «አውቀውስ ቢሆን የክብርን ጌታ ባልሰቀሉት» /1ቆሮ.1-18/፡፡ እንዳለ ይህ ዕለት የአይሁድ ካህናት ያለበደል ያለጥፋት ንጹሕና ጻድቅ የሆነውን ጌታ የሰቀሉበት ዕለት ነው፡፡ ዕለቱም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም ሁሉ መድኃኒት ለአዳምና ለልጆቹ ሲል በመልእልተ መስቀል በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ መዋሉን የምናስብበት ታላቅ ቀን ነው፡፡ /ማቴ.27-35-75/፡፡ በዚያን ጊዜ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ እንደተፈረደበት አይቶ ተጸጸተ ሠላሳውንም ብር ለካህናት አለቆችና ለሽማግሎች መልሶ ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ አለ፡፡ እነርሱ ግን እኛስ ምን አግዶን?  አንተው ተጠንቀቅ አሉ፡፡ ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሔደና ታንቆ ሞተ፡፡ የካህናት አለቆችም ብሩን አንሥተው የደም ዋጋ ነውና ወደ መባ ልንጨምረው አልተፈቀደም አሉ፡፡ ተማክረውም የሸክላ ሠሪ መሬት ለእንግዶች መቃብር ገዙበት፡፡ ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ የደም መሬት ተባለ፡፡ /ማቴ.27-3-9/
የሰው ልጆች በዘር ኃጢአት /ቁራኝነት/ ይኖሩበት የነበረው የጨለማ ሕይወት ያከተመበት ፍጹም ድኅነት ያገኙባት ታላቅ ዕለት ናት፡፡ ክርስቲያኖች ሁልጊዜም ዕለተ ዓርብ ሲመጣ ሕማሙን ስቅለቱን ሞቱን የሚያስቡበት ጊዜ ነው፡፡ በሮማውያን ሕግና ሥርዓት መስቀል የወንጀለኞች መቅጫ ምልክት የሕይወት መቅጫ አርማ ሆኖ ሳለ ለእኛ የዲያብሎስ ድል መንሻ ስላደረገው በስቅለቱና በሞቱም ሕይወትን ስለአገኘን በዚህም ምክንያት መልካሙ ዓርብ በመባል እንደሚታወቅ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ያትታሉ፡፡
ቀዳሜ ስዑር
ዕለተ ቅዳሜ እግዚአብሔር የሚታዩትንና የማይታዩትን፣ በእግር የሚሄዱትን እና በክንፍ የሚበሩትን በባሕር የሚዋኙትን እንስሳትን በመጨረሻም ሰውን በአርአያውና በአምሳሉ ፈጥሮ ያረፈበት ዕለት ነች፡፡ ይህች የመጀመሪያው ቅዳሜ ለእግዚአብሔር የዕረፍት ዕለት ናት እግዚአብሔርን ሥነ ፍጥረት ፈጥሮ ስላረፈበት ሰንበት ዐባይ /ታላቋ ሰንበት/ ትባላለች ታላቋን ሰንበት እስራኤላውያን እንዲያከብሯት ታዟል፡፡ ዘፍ.1፡3፡፡
ዕለተ ቀዳሚት /ሰንበት ዐባይ/ በዘመነ ሐዲስም የተለየ የደኅነት ሥራ ተከናውኖባታል፡፡ ጥንት ሥነ ፈጥረትን በመፍጠር ዕረፍት እንደ ተደረገባት ሁሉ የፍጥረት ሁሉ ቁንጮ የሆነውን አዳምን ለማዳን ሕማምና ሞት የተቀበለው ቸሩ አምላክ በመቃብር አርፎባታል፡፡ ማቴ.27፡61፡፡
በዚህች ዕለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከርሰ መቃብር ዐርፎ የዋለባት ዕለት በመሆኗ «ቀዳሜ ስዑር » ትሰኛለች፡፡ ስዑር ቀዳሜ የተባለችው በዓመት አንድ ቀን ስለ ምትጾም ነው፡፡ ምክንያቱም እናቱ ድንግል ማርያም ወዳጆቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታ ተላልፎ ከተሰጠበት ዕለት አንስተው ብርሃነ ትንሣኤውን እስኪያዩ ድረስ እህል ውኃ በአፋቸው አልዞረም፡፡ ይመኩበትና ተስፋ ያደረጉት የነበረ አምላካቸው በመቃብር ስላረፈ ዕለቷን ሞቱን በማሰብ ትንሣኤውን በመናፈቅ በጾም አክብረዋታል፡፡
ከቅዱሳን ሐዋርያት ሲወርድ ሲወራረድ በመጣው ትውፊት መሠረት ቅዱሳን ሐዋርያት በማዘን በመጾምና በመጸለይ ዕለቷ እንዳከበሯት የተዋሕዶ ልጆች የተቻላቸው ከዓርብ ጀምረው የሚያከፍሉ /የሚጾሙ/ ለሁለት ቀን እህል ውኃ ሳይቀምሱ ያድራሉ ያልተቻላቸው ደግሞ ዓርብ ማታ በልተው ቅዳሜን በመጾም ትንሣኤን ያከብራሉ፡፡
በዚህ ዕለት ከሰኞ ከሆሣዕና ማግሥት ጀምረው እስከ ስቅለተ ዓርብ ድረስ በስግደት እና በጾም ያሳለፉ ምእመናን በዕለተ ቅዳሜ በቅጽረ ቤተ ክርስቲያን ይሰበሰባሉ፡፡ የጠዋቱ ጸሎት ሲፈጸም ካህናቱ «ገብረ ሰላመ በመስቀሉ፡-በመስቀሉ ሰላምን መሠረተ» የምሥራች እያሉ በቤተ ክርስቲያን ለተሰበሰቡት ምእመናን ቄጠማ ይታደላል ቄጠማው የምሥራች ምልክት ነው፡፡ ቄጠማው የምሥራች ምልክት ተደርጐ የተወሰደው በኖህ ዘመን ከተፈጸመው ታሪክ ጋር በማቆራኘት ነው፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን በጻድቁ ኖኅ ዘመን የነበሩ ሕዝቦች ከሕገ እግዚአብሔር ውጪ ሆነው እጅግ የሚያሳዝን ኃጢአት በሠሩ ጊዜ በንፍር ውኃ ተጥለቅልቀዋል፡፡ በወቅቱ ጻድቁ ኖኅ ወደ መርከብ ይዞአቸው ከገባው እንስሳት መካከል የውኃውን መጉደል ለመረዳት ርግብን በመርከብ መስኮት አሾልኮ ይለቃታል፤ እርሷም ቄጠማ በአፍዋ ይዛ ትመልሳለች፡፡ ዘፍ.9-1-29፡፡ ኖኅም በዚህ ቄጠማ የውኃውን መድረቅ ተረድቶ ተደስቷል፡፡
«ቄጠማ»፣ ለጥፋት ውኃ መድረቅ የምሥራች መንገሪያ እንደሆነ አሁንም በክርስቶስ ሞት ሞተ ነፍስ ከሰው ልጆች ተወገደ ስትል ቤተ ክርስቲያን ለልጆቿ ቄጠማ ታድላለች፡፡ ምእመናንም የምሥራች ተምሳሌት የሆነውን ቄጠማ በግንባራቸው ያስሩታል፡፡
የክርስቶስ ተከታዮች ሁሉ ከጨለማ ወደ ብርሃን ከሚያቃጥለው ዋዕየ ሲኦል /የሲኦል ቃጠሎ/ ወደ ልምላሜ ገነት ጥንተ ማኅደራቸው መመለሳቸውን በዚህ አኳሃን እየገለጡ በዓለ ትንሣኤን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያከብራሉ፡፡ 
 

ከበዓሉ ረድኤት በረከት ያሳትፈን፡፡አሜን፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር