ዘመነ ስብከት
ዘመነ ስብከት ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በፊት ከታኅሣሥ ፯ ጀምሮ እስከ ፳፱ ያለው ወቅት ነው፡፡ ሳምንታቱም ስብከት፣ ብርሃንና ኖላዊ ይባላሉ፡፡ በዚህም ወቅት ስለ ጌታችን ኢየሱስ መወለድ ነቢያት የተናገሩት ትንቢት ይሰበክበታል፡፡
ዘመነ ስብከት ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በፊት ከታኅሣሥ ፯ ጀምሮ እስከ ፳፱ ያለው ወቅት ነው፡፡ ሳምንታቱም ስብከት፣ ብርሃንና ኖላዊ ይባላሉ፡፡ በዚህም ወቅት ስለ ጌታችን ኢየሱስ መወለድ ነቢያት የተናገሩት ትንቢት ይሰበክበታል፡፡
ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት መካከል አንዱ የሆነውን ጾመ ነቢያት በየዓመቱ ከኅዳር ፲፭ ጀምሮ እስከ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ድረስ በአምላካችን ቅዱስ ፈቃዱ እንጾማለን!
ደብረ ቊስቋም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተወደደ ልጇ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመግደል ከሚፈልጉት ሸሽተው መጠጊያ ያገኙበት እንዲሁም ቅዱስ ገብርኤል ንጉሥ ሄሮድስ መሞቱን ለቅዱስ ዮሴፍ በሕልሙ የገለጸበት ስፍራ ነው፡፡ ‹‹የሕፃኑን ነፍስ የሚሹ ሞተዋልና፥ ተነሥተህ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ እስራኤል ሀገር ሂድ›› እንዲል። (ማቴ.፪፥፲፱-፳)
በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ መሠረት ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፮ ያለው ወቅት ወርኃ ጽጌ (የጽጌ/የአበባ ወር) ይባላል፡፡ በወርኃ ጽጌ አበባዎች ያብባሉ፤ ፍሬም ያፈራሉ፤ በዚህም ወቅት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ እንዲጠብቃት ከታዘዘው አረጋዊው ዮሴፍ ጋር ስትኖር መልኳ አንዳንድ ጊዜ እንደ ጽጌረዳ አበባ ቀይ ሁና፣ በሌላ ጊዜ ደግሞ እንደ ሮማን አበባ ነጭ ሁና ስትታየው፣ ቀይ የነበረው መልኳ ተለውጦ እንደ ሮማን አበባ ጸዓዳ ነጭ፣ ነጭ የነበረው እንደ ጽጌረዳ ቀይ ሲለወጥ በመደንገጥ እርሷ መሆኗን ለማረጋገጥ ‹‹ማርያም›› ብሎ እየጠራ ያረጋግጥ ነበር፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለዚህ ምሥጢር ሲያስረዳ ‹‹መልኳ እንደ ጽጌረዳና እንደ ሮማን አበባ ይለዋወጥበት ስለነበር በአንድ ዓይነት መልክ አላወቃትም›› ብሏል፡፡ በዚህም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እመቤታችንን በአበባ፣ ጌታችንን ደግሞ በፍሬ እየመሰሉ ለማመስገንና ለማወደስ በሚያስችል ምሥጢር የስደቱ ጊዜ በወርኃ ጽጌ እንዲዘከር አድርገዋል፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለዘለዓለሙ የማይደርቀውን የሕይወት ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስን ያስገኘችልን ንጽሕት የማትጠወልግ አበባ ናትና፡፡
የሰው ልጅ እግዚአብሔር አምላኩ ባደለው ሥጦታ ‹ጊዜ› በሕይወት ዘመኑ በበጎ ምግባር እንዲኖርና በጸሎት በጾም እንዲተጋ በዓመታት፣ በወራት እና በቀናት ምልልስ በሚያገኘው ዕድል ዘወትር ፈጣሪውን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሊሠራ እንዲገባ የጊዜ ጭማሪ ተደረገለት፡፡ ይህችም የጭማሮ ጊዜ እስከ ዕድሜው(ዘመኑ) መጨረሻ ከኃጢአት በሙሉ ይነጻ እንዲሁም ጸጋ በረከትን ያገኝ ዘንድ የቀናት ምርቃት ሆነችለት፤ ‹የጳጉሜን ወር› (ወርኃ ጳጉሜን) ተብላም ተሰየመች፡፡ …
ቅድስት ድንግል ማርያም በምድር ላይ ለ፷፬ ዓመት በሕይወተ ሥጋ ከኖረች በኋላ ቅዱስ ያሬድ እንደተናገረው በጥር ፳፩ ቀን ከሚያልፈው ዓለም ወደ ማያልፈው ዓለም ተሻግራለች፡፡ «ፈለሰት እምዘይበሊ ኀበ ኢይበሊ፤ ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ዓለም፣ (ከምድር ሕይወት ወደ ሰማያዊ ሕይወት) ተሻገረች» እንዲል፤ (ዚቅ ዘቅዱስ ያሬድ ነሐሴ ፲፮)…
ከዚህም በኋላ ቅዱሳን መላእክት ክቡር ሥጋዋን በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር አኖራት፤ ከጥር ፳፩ እስከ ነሐሴ ዐሥራ ስድስት ቀን ለሁለት መቶ አምስት ቀናት ቆይታለች፡፡ …
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የምንሰማቸው አንዳንድ የኦርቶዶክሳዊ መዝሙራት ይዘታቸውን እየለወጡ በመሄዳቸው አንዳንዶቹ እንዲያውም ወደ ዘፈንና ወደ መናፍቃን ዝማሬ ተቀይረው የጠላት ማሳቻ መንገድ እየሆኑ መምጣቸውን ሳንገነዘብ አልቀረንም፡፡ ነቢዩ ዳዊትም ‹‹በማስተዋል ዘምሩ›› ሲል በመዝሙሩ እንደተናገረው ኦርቶዶክሳዊ መዝሙራትን መለየትና በተለይም አምላካችንን የምናመሰግንበት፣ አጽዋማትና ክብረ በዓላትን የምንዘክርበት እንዲሁም በችግርና መከራ ጊዜ የምንማጸንበት የንስሓ መዝሙራትን ማወቅ ይኖርብናል፡፡ (መዝ.፵፮፥፯)
ባሕር በስፍሐቱ መጠን ከማንኛውም የውኃ ሙላት ይበልጣል፤ በተለይም በዘመነ ክረምት የባሕር መሰልጠን (ሙላት) ይሆናል፡፡ ቅዱስ ያሬድም ‹‹ደምፀ እገሪሁ ለዝናም ሶበ ይዘንም ዝናም ይትፌሥሑ ነዳያን፤ ይጸግቡ ርኁባን ምድርኒ ርእየቶ ወአእኰተቶ ባሕርኒ ሰገደት ሎቱ፡፡ የዝናም ድምፅ ተሰማ፤ ዝናብም በዘነበ ጊዜ ድሆች ደስ ይሰኛሉ፤ ረኃብተኞችም ይጠግባሉ፤ ምድር አየችው፤ አመሰገነችውም፤ ባሕርም ሰገደችለት›› በማለት እንደዘመረው በዘመነ ክረምት ባሕር ይሰለጥናል፡፡ (ድጓ ዘክረምት)
ሰማይ በደመና ተሸፍኖ ዝናብ በሚዘንብበት በዘመነ ክረምት መብረቅ በነጎድጓዳማ ድምጽ በብልጭታ በሰማይ ይፈጠራል፤ የእሳት ሰይፍ፣ የእሳት ፍላፃ፣ በዝናም ጊዜ ከደመና አፍ የሚመዘዝ የሚወረወርና ውኃው በደመና አይበት ተቋጥሮ በነፋስ ወደል ጋዝ ተጭኖ ሲመጣ፣ ደመናና ደመና በተጋጨ ጊዜ መብረቅ እንደሚፈጠር መጽሐፍ ቅዱስ ይጠቅሳል፡፡
የሁሉ ፈጣሪ የዓለም ገዢ አምላካችን እግዚአብሔር በሐምሌ ፯ ቀን ወደ ጻድቁ አብርሃም ቤት በመግባት በአንድነትና በሦስትነት ክብሩ ተገለጠለት፡፡ምሥጢረ ሥላሴን በሚገባ መርምሮ መረዳት ለማንም ቢሆን ባይቻልም ምሥጢረ ሥላሴ በምሥጢረ ጥምቀት ተገልጧል፡፡…