‹‹የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ›› (ምሳ. ፩፥፯)
‹‹እግዚአብሔርን መፍራት ለጥበብ ዘውድዋ ነው›› እንደተባለ ከእግዚአብሔር የሆነው ጥበብ መጀመሪያው እርሱን መፍራት ነው፤ (ሲራክ ፩፥፲፰)፡፡ እግዚአብሔርን መፍራት ስንል በቁጣው ይቀሥፈኛል፣ በኃያልነቱ ያጠፋኛል ከሚል የሥጋትና የጭንቀት መንፈስ ሳይሆን የዓለሙ ፈጣሪና መጋቢ እርሱ መሆኑን በማመን በፈቃዱ መገዛትና መኖር ማለታችን ነው፡፡