ርእሰ ዐውደ ዓመት
አምላካችን እግዚአብሔር ዕድሜ ለንስሓ ዘመን ለፍስሐ የሰጠን መልካም እንድንሠራበት ነውና በመጪው ዘመን የትላንት ስሕተታችንን አርመን፣ የተጣላን ታርቀን፣ የበደልን ክሰን፣ ያለው ለሌለው እያካፈለ ለመኖር ማቀድ ይገባናል!
አምላካችን እግዚአብሔር ዕድሜ ለንስሓ ዘመን ለፍስሐ የሰጠን መልካም እንድንሠራበት ነውና በመጪው ዘመን የትላንት ስሕተታችንን አርመን፣ የተጣላን ታርቀን፣ የበደልን ክሰን፣ ያለው ለሌለው እያካፈለ ለመኖር ማቀድ ይገባናል!
ጳጉሜን ሦስት ቀን የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሩፋኤል በዓል በየዓመቱ ይታሰባል፤ ይከበራልም፡፡ መልአኩ የጦቢትን ዓይን ያበራና ወለተ ራጉኤልን ተቆራኝቷት ከነበረው ጋኔን ያላቀቀ ነውና፡፡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ከመላእክት አለቆች ሦስተኛ የሆነ ነው፡፡ ደግሞም ከእስክንድርያ ውጭ በደሴት የታነጸች ቤተ ክርስቲያን በከበሩ ሊቀ ጳጳሳት ቴዎፍሎስ ዘመን በውስጧ ተአምር የተገለጸበትና የከበረችበት ዕለት ነው፡፡
አምላካችን እግዚአብሔር ለነቢዩ ኤርምያስ “በሆድ ሳልሰራህ አውቄሃለሁ፤ ከማኅፀን ሳትወጣ ቀድሸሃለሁ” በማለት እንደተናገረ የገናናው ጻድቅ የአባታችን ተክለ ሃይማኖት ዜና ሕይወቱን እንዘክራለን፡፡ (ኤር.፩፥፭)
ከ፹ ዓመት በላይ በበረሃ የተጋደሉ፣ በአስቄጥስ ገዳም ፭፼ መነኮሳትን በመመገብ የመሩ፣ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ ወደሙን ተቀብለው ስለ ሥጋ ወደሙ ክብር ሲሉ ለ፷ ዓመት ምራቃቸውን ሳይተፉ የኖሩት ታላቁ አባት አባ መቃርስ በነሐሴ ፲፱ ፍልሰተ አጽማቸው ሳስዊር ከሚባል ሀገር ወደ አስቄጥስ የተፈጸመበት የከበረ በዓል ነው፡፡
ከዚህ ዓለም ውጣ ውረድና ድካም በ፷፬ ዓመቷ በጥር ፳፩ ቀን በ፵፱ ዓ.ም ያረፈችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ትንሣኤዋም ሆነ ዕርገቷ በክብር የተፈጸመ እንደመሆኑ እኛም ልጆቿ ይህችን የተባረከች ቀን እናከብራለን፡፡
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! ለከበረው ጤንነታችሁ እንዴት አላችሁ? የጾምን ወቅት እንዴት እያሳለፋችሁት ነው? አባቶቻችን ሊቃውንት ስለ ጾም እንዲህ ይላሉ፤ ጾም ማለት ከምግብና ከውኃ መከልከል ብቻ ሳይሆን ከክፉ ሥራም መታቀብ (መከልከል) ነው፤ ጾም የጽድቅ በር ናት፣ ጾም ለመልካም ነገር የምታነሣሣን ናት፤ ውድ እግዚአብሔር ልጆች! ስንጾም ከጸሎትና ከስግደት ጋር፣ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ በማስቀደስ ፣ታዛዦች በመሆን የጾሙን ጊዜ ልናሳልፍ ይገባል፡፡ መልካም!
ውድ እግዚአብሔር ልጆች! ለዛሬ ያዘጋጀንላችሁ ታሪክ የቅድስት እንባመሪናን ነው፡፡
በተከበረች በነሐሴ ፲፫ በታቦር ተራራ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ዕለት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ”በዓለ ደብረ ታቦር‘ ተብሎ ይከበራል፡፡
ለዓለም ሁሉ የድኅነት መገኛ የሆነች ክብርት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተፀነሰችበት ዕለት ነሐሴ ሰባት የተባረከች እንደመሆና መላው ክርስቲያን በዓሏን ሊያከብር ይገባል፤ የመፀነሷ ነገርም እንዲህ ነው፡፡…
በመከራ ጊዜ ረዳት የሆነው የመላእክት አለቃ ቅዱስ ዑራኤል በዘመናት ለነገሡ የሀገራችን ነገሥታት ያደረገው ውለታ እጅግ ብዙ ነው፡፡ ዳግማዊ ቆስጠንጢኖስ የተባለ ንዋየ ማርያም በነገሠበት ዘመነ መንግሥት ቅዱስ ዑራኤል በጸሎቱ በመራዳትና እስከ ግዛቱ ፍጻሜ ባለመለየት ሀገሩን እንዲመራ አድርጓል፡፡…
ሜሶፖታሚያ በምትገኝ ንጽቢን ከተማ ከዋክብትን ከሚያመልኩ ሰዎች መካከል በ፫፻፮ ዓ.ም ገደማ የተወለደው ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም አባቱ ክርስትናን የሚጠላ ሰው እንደነበር ይነገራል፡፡ እንዲያውም ካህነ ጣዖት ስለመሆኑ መጽሐፈ ስንክሳር ይጠቅሳል፡፡ (ስንክሳር ሐምሌ ፲፭)