‹‹መጠራጠር የእምነትና የጽናት ጉድለት ነው›› ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

መጠራጠር የእምነትና የጽናት ጉድለት ነው፤ መድኃኒታችን ኢየሱስ በባሕር ላይ እየሄደ ወደ ደቀ መዛሙርቱም በመጣ ጊዜ ምትሐት ምስሎአቸው ታወከው በፍርሃት ጮኹ።  ጌታችን ኢየሱስም ‹‹አይዞአችሁ፥ እኔ ነኝ አትፍሩ›› አላቸው፤  ቅድስ ጴጥሮስም መልሶ፥ አቤቱ፥ አንተስ ከሆንህ በውኃው ላይ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ›› አለው። እርሱም ‹‹ና›› አለው። ጴጥሮስም ከታንኳው ወርዶ ወደ ኢየሱስ ሊደርስ በውኃው ላይ ሄደ።  ነገር ግን ነፋሱ በርትቶ ባየ ጊዜ ፈራ፥ ሊሰጥምም በጀመረ ጊዜ ጌታ ሆይ፥ አድነኝ ብሎ ጮኸ። ወዲያውም ጌታችን ኢየሱስ እጁን ዘርግቶ ያዘው ‹‹አንተ እምነት የጎደለህ፥ ስለምን ተጠራጠርህ?›› ብሎታል፡፡ መጠራጠር ያለመጽናት፣ ያለማመን ውጤት ነውና፡፡ (ማቴ. ፲፬፥፳፬-፴፩)

“ሃይማኖትና ሀገር ወጣት ሲረከበው ነው ሀገርነቱም፣ እምነቱም ሊቀጥል የሚችለው”

የዛሬው የቤተ አብርሃም እንግዳችን መጋቤ ምሥጢር ቀሲስ ቀጸላ ፈንቴ ይባላሉ፡፡ ከአባታቸው ከቄስ ፈንቴ ታረቀ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ጎንደር በቀለ በ፲፱፻፶፰ ዓ.ም በምዕራብ ጎጃም ሰከላ ወረዳ ልዩ ስሙ ጉሌ ኪዳነ ምሕረት ተብሎ  በሚጠራ ቦታ ተወለዱ፡፡ በአብነት ትምህርቱ ቅኔን ጨምሮ ሌሎቹንም ትምህርቶች ተጨልፎ ከማያልቀው ከቤተ ክርስቲያን ማዕድ በአባቶች እግር ሥር ቁጭ ብለው ተምረዋል፡፡ ወደ አዲስ አበባ በመምጣትም በሰዋሰው ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ የካህናት ማሠልጠኛ ለአራት ዓመት የነገረ መለኮት ትምህርት ተምረዋል፡፡ በትውልድ አካባቢያቸው ለ፲፫ ዓመት የቅኔና የሐዲሳት መምህር ሆነው አገልግለዋል፣ ከዚያም ወደ ከተማ በመምጣት ከ፳፪ ዓመታት በላይ የቅኔ፣ የሐዲሳትና የብሉያት መምህር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን፣ በርካታ ተማሪዎችን አስተምረው ለአገልግሎት አብቅተዋል፡፡ በአጠቃላይ ባሳለፉት የአገልግሎት ዘመን የቅኔና የትርጓሜ መምህር ሆነው በማገልገል ከ፴፱ ዓመት በላይ አስቆጥረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የሃይማኖተ አበው ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ፡፡ ከመጋቤ ምሥጢር ቀሲስ ቀጸላ ፈንታ ጋር በሕይወት ተሞክሯቸው ዙሪያ ልምዳቸውን፣ እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ያጋሩን ዘንድ የቤተ አብርሃም እንግዳችን አድርገናቸዋል፤ መልካም ንባብ፡፡

‹‹በሕማም፣ በመከራና መሥዋዕት በመሆን ፍቅራችን ይፈተናል›› ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

ፍቅርን የሚያውቅ ሰው ለእግዚአብሔር እና ለሌሎች ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባል፡፡ ሰው በመጀመሪያ መሥዋዕት ለማድረግ መልመድ ያለበት ከእርሱ ውጪ በሆኑ ነገሮች ማለትም ገንዘቡን፣ ጊዜውን እና ሀብቱን በመለገስ ነው፤ መስጠት ከመቀበል አንድ ነውና፡፡ ለሰዎች ደስታ እንደራሱ የሚጨነቅ እርሱ ፍቅርን ያውቃል፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ይኖራል፡፡ መሥዋዕትነት መክፈል ካልቻልን ግን ፍቅር አልገባንም ማለት ነው፤ አምላካችን እግዚአብሔርን ማፍቀር ካልቻልን ደግሞ ድኅነተ ሥጋንም ሆነ ድኅነተ ነፍስን ማግኘት አንችልም፡፡

‹‹ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ›› (ዮሐ. ፲፬፥፳፯)

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል ለሕዝቡ ‹‹ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ…›› ብሎ በነገራቸው ቃሉ ሰላምን የሚሰጠው እርሱ እንደሆነ እንረዳለን፤  ይህም የተወልን ሰላም መንፍሰ ቅዱስ በመሆኑ መንፈስ ቅዱስ በአንድ ሰው ውስጥ ሲያድር የልብ ሰላምን ይጎናጸፋል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ስለዚህ ሰላም ሲጽፍ እንዲህ ብሏል፤‹‹አእምሮውንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና ሀሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል፤›› (ዮሐ. ፲፬፥፳፯፤ ፊል. ፬፥፯)

‹‹የሚሰማኝ ግን በተስፋ ይኖራል፤ ከክፉም ሁሉ ያለድንጋጤ ያርፋል›› (ምሳ.፩፥፴፫)

የእስራኤል ንጉሥ ጠቢቡ ሰሎሞን በግዛቱ ዘመን ለሕዝቡ በምሳሌ ቃሌን ስሙ እያለ በተደጋጋሚ ይናገር ነበር። ነገር ግን የእርሱን ሳይሆን የእግዚአብሔርን ቃል ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ቃልን መስማት ደግሞ ጥበበኛ ያደርጋል፤ ተስፋን ያለመልማል፤ ከክፉም ይታደጋል። ስለዚህ ‹‹ቃሌን የሚሰማ ግን በተስፋ ይኖራል፤ ከክፉም ሁሉ ያለድንጋጤ ያርፋል›› በማለት ያስረዳናል። በዚህ ኃይለ ቃል የእግዚአብሔርን ቃል መስማት፣ በተስፋ መኖርና ከክፉ መዳን የሚሉ መሠረታዊ ነጥቦችን እናገኛለን፤ እያንዳንዳቸውን እንመልከታቸው። (ምሳ.፩፥፴፫)

‹‹ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ›› (ዮሐ. ፲፬፥፲፭)

ሰው አምላኩ እግዚአብሔርን ከወደደ ሁለተናውን ለእርሱ ይሰጣል፤ ከኃጢአት የነጻ ሆኖ ልበ ንጽሕ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ኃጢአት በምንሠራበት ጊዜ ከፈጣሪያችን ስለምንረቅ ለሌላ ባዕድ ነገር ተገዢ እንሆናለን፡፡ ክርስቶስን በሙሉ ልባችን፤ ነፍሳችን፣ ኃይላችን ከወደድነው ግን ፍቅሩን ተረድተን ሁለመናችን ለእርሱ እንሰጣለን፤ እርሱም ደግሞ ከእኛ ጋር ይሆናል።

ወጣትነት እና የኮሮና ቫይረስ በሽታ ስርጭት

ሰው በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል ተፈጥሯል፣ይህም ከጥንተ ተፈጥሮ በበለጠ በአዲስ ተፈጥሮ እግዚአብሔር ሰውን ምን ያክል እንደወደደው በልጁ የማዳን ሥራው ላይ በወንጌል ተምረናል።

‹‹ኑ እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር›› (ኢሳ. ፩፥፲፰)

ብዙ ጊዜ በሕይወት በሚገጥመን ፈተናና ችግር ምክንያት ራሳችንን በመመርመር እግዚአብሔርን መማጸንን የመሰለ መፍትሔ ወይም የድኅነት መንገድ የለም፡፡ እስራኤል ከእግዚአብሔር ርቀው፤ ወደ ቃሉ መጠጋት በአቃታቸው ጊዜ ነቢዩ ኢሳይያስ የመጣባቸው መቅሠፍት የኃጢአታቸው ውጤት ስለነበረ እግዚአብሔር አጥቦ ቅዱሳን ልጆቹ ሊያደርጋቸው የተዘጋጀ አባት በመሆኑ ‹‹ኑ እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር›› አላቸው፡፡ (ኢሳ. ፩፥፲፰)

በዓለ ጰራቅሊጦስ

በዓለ ጰራቅሊጦስ የሚከበረው ርደተ መንፈስ ቅዱስን መሠረት በማድረግ በመሆኑ ምክንያት ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ለመቀበል ነው፤ በዕለቱም ኢየሩሳሌም በተባለችው ቤተክርስቲያን ስለመጽናት፤ ከግለኝነት ይልቅ መንፈሳዊ አንድነትን ስለማስቀደም እና ስለመጸለይ  እንማራለን፡፡  

ደብረ ምጥማቅ

ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት “ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኲሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር፤ የምድር ባለጠጎች አሕዛብ ሁሉ በፊትሽ ይማለላሉ፤” በማለት ትንቢትን እንደተናገረላት ብዙዎች ቅዱሳን ቅድስት ድንግል ማርያምን ተገልጻላቸው ለማየት ተመኝተዋል፤ ልመናቸው ተሰምቶላቸው የአምላክ እናት ተገልጻላቸው እጅግ አስደናቂ ውበቷን አይተዋል፡፡ ከነዚህ ውስጥ በደብረ ምጥማቅ የነበሩ ምእመናን ሌሎችም ብዙዎች ንጹሓን ክርስቲያኖች ይገኙበታል፡፡ (መዝ. ፵፬፥፲፪;)