ዓለመ ምድር

ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ምድር በገነት ወይም በሲኦል ልትመሰል እንደምትችል ያስረዳሉ፡፡ በቤተ ክርስቲያን ወርቃማ ዘመናት ተብሎ የሚጠሩትንም በመጥቀስ የተመረጡ ቅዱሳን ነገሥታት የነገሡበት፣ ደጋግ አባቶች የኖሩበት፣ ሊቀ ጳጳሳትና ጳጳሳት እንዲሁም ቀሳውስትና ካህናት በበጎና በመልካም መንገድ ምእመናንን መርተው በቅድስና ሕይወት ለርስተ መንግሥተ ሰማያት ባበቁበት ጊዜ ምድር በገነት ትመሰል እንደነበር ያስረዳሉ፡፡

‹‹ብርሃን ይሁን!›› (ዘፍ.፩፥፫)

በሥነ ፍጥረት መጀመሪያ ቀን ‹‹ብርሃን ይሁን›› በማለት የተናገረው አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ነው፡፡ (ዘፍ.፩፥፫) ‹‹ብርሃን ይሁን›› በማለት በተናገረ ጊዜም ጨለማ ተገፈፈ፡፡ መጽሐፈ ሥነ ፍጥረት እንደሚነግረን ቅዱሳን መላእክትም ይህ ብርሃን ዕውቀት ሆኗቸው አምላካቸው እግዚአብሔርን ‹‹ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ›› በማለት በአዲስ ምስጋና አመሰገኑት፡፡ ‹‹እኔ ፈጣሪያችሁ ነኝ›› ያለ የሰይጣን ክህደትም በብርሃኑ ተጋለጠ፡፡ (ሊቀ መዘምራን ሞገስ ዕቁበ ጊዮርጊስ መጽሐፈ ሥነ ፍጥረት)

ዓለመ ሰማይ

በዓለመ ሰማይ እግዚአብሔር አምላክ ፍጥረቱን መፍጠር በጀመረበት በመጀመሪያው ቀን እሑድ አስቀድሞ የተፈጠሩት ሰባቱ ሰማያትና መላእክት ናቸው፡፡ ሰማያቱም እንደ ስያሜያቸው የራሳቸው ትርጓሜ አላቸው፡፡