‹‹ቀድሱ ጾመ ወስብኩ ምሕላ፤ ጾምን ለዩ! ምሕላንም ዐውጁ›› (ኢዮ.፩፥፲፬)
የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተገልጦ ፍርሃትና ሥጋታቸው የተወገደላቸው ቅዱሳን ሐዋርያት ለወንጌል አገልግሎት ከመሠማራታቸው በፊትና ሕገ ወንጌልን ከማስተማራቸው አስቀድሞ አገልግሎታቸው እንዲቃና፣ መንፈስ ቅዱስ እንዳይለያቸውና የመንፈስ ቅዱስን ምሪትና ኃይል ለመቀበል ሱባኤ ያዙ፤ ሀብተ መንፈስ ቅዱስም በአገልግሎታቸው እንደሚበዛ ሲያረጋግጡ ቅዱሱን ወንጌል የሚያገለግሉበትን ክፍለ ዓለም ዕጣ በመጣጣል ዕጣው ወደ ደረሳቸው የአገልግሎት ቦታ መሰማራታቸውን የቤተ ክርስቲያን የታሪክ መዛግብትና ሊቃውንት አባቶቻችን ያስረዳሉ::