“ጾምን ቀድሱ፥ ጉባኤውንም አውጁ” (ኢዩ.፩፥፲፬)
ከጾም የሥጋ ንጽሕና፣ የነፍስ ቅድስናና ድንግልና ይወለዳሉ። ይህች ጾምም የጽድቅ ሥራዎች ሁሉ መርከብ ናት፤ በውስጧ የተከበሩ ዕቃዎች ሁሉ ይኖራሉ። ሩቅ ሀገር የሚሄዱት ያለ መርከብ በባሕር ላይ ፈጽሞ መሄድ እንዳይቻላቸው ሁሉ እንዲሁ ስለጽድቅ የሚጓዙትም በመንፈሳዊት ሐመር ካልታሳፈሩ አንዲት እርምጃ ስንኳን መራመድ አይቻላቸውም።” (ርቱዓ ሃይማኖት ገጽ ፺፩-፺፪)