በዓለ ልደቱ ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሀገራቸው ንሂሳ ግብጽ ነው፡፡መላው ሕይወታቸውንም በምድረ በዳ የኖሩ አባት ናቸው፤ በዝቋላ ተራራ ባለው ባሕር ውስጥ ፻ (መቶ) ዓመት ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያውያን ምሕረትን በመለመን ለብዙዎች ድኅነት የሆኑ ታላቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ የተወለዱት ታኅሣሥ ፳፱ ቀን ቢሆንም በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል ምክንያት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በሠሩልን ሥርዓት መሠረት ጥር ፭ በድምቀት እናከብራለን፡፡