Entries by Mahibere Kidusan

ለሲኖዶሳዊ ልዕልና መከበር የምእመናን ድርሻ ከፍተኛ ነው!

በሀገር አቀፍ ደረጃ የፖለቲካ ተሰሚነት እና ውክልና እንዳይኖራት፣ እጅግ ብዙ ችግር እንዲከባት ተሠርቷል፤ አሁንም እየተሠራ ይገኛል፡፡ ይህንም ለማድረግ የተቻለው በተቀናጀ ስልት ሲሆን ሲኖዶሱ ክብሩ ልዕልናው እንዳይጠበቅ በማድረግ፣ የመሪነት ሚናውን እንዳይወጣ፣ የተጠራበትን ሰማያዊ ተልእኮውን እንዳያሳካ፣ በመከፋፈል እና በራሱ ውስጣዊ አጀንዳ እንዲጠለፍና፣ ውሳኔው መሬት እንዳይነካ በማድረግ ነው፡፡ ከምንም በላይ መሪና ተመሪ እንዳይገናኙ፣ ሲኖዶሱ በምእመናን ዘንድ ተቀባይነት እንዲያጣ አድርጎታል፡

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል

መልአኩ ዑራኤል “አፍህን ክፈት፤ እኔም የማጠጣህን ጠጣ” … ብሎ አእምሮ ለብዎውን ገልጦለታል። (ዕዝ.ሱት. ፲፫፥፴፰) የዚህን ተአምር መታሰቢያ ሐምሌ ፳፪ በየዓመቱ ቤተ ክርስቲያናችን ታከብራለች።

“ልጄ ሆይ ከእንግዲህ አባቴ ነህ!”

መኮንኑ አፈረና ጽኑ ሥቃይ ሊያሠቃያቸው ወድዶ እንደ ክረምት ነጎድጓድ ድምፅ ወደ ሚያስተጋባው የፈላ ውኃ እንዲጥሏቸው አዘዘ፤ ያን ጊዜ እናቱ ፈራች፤  ሕፃኑ ግን ለእናቱ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እንዲህም አላት፤ “እናቴ ሆይ አትፍሪ! ጨክኝ፤ አናንያ አዛርያ ሚሳኤልን ያዳነ አምላክ እኛንም ያድነናል” አላት። እናቱ ቀና ብላ ብትመለከት ለቅዱሳን ሰማዕታት የተዘጋጁትን የብርሃን ማደርያቸውን ተመለከተች፤ ደስም ተሰኝታ እንዲህ አለች፤ “ልጄ ሆይ ከእንግዲህ አባቴ ነህ፤ እኔም ልጅህ ነኝ፤ አንተን የወለድኩባት ቀን የተባረከች ናት፡፡”

ቅዱስ ኤፍሬም

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁ? ወርኃ ክረምትን እንዴት እያሳለፋችሁ ነው? ዘመናዊ ትምህርት ተጠናቆ አሁን ዕረፍት ላይ እንደመሆናችሁ መጠን ጊዜያችሁን በተገቢው መንገድ እየተጠቀማችሁበት እንደሆነ ተስፋ እናደርጋለን! በጥሩ ውጤት ከክፍል ክፍል እንደተዘዋወራችሁም ተስፋ አለን፡:ልጆች! ዛሬ የምንነግራችሁ የቅዱስ ኤፍሬምን ታሪክ ነው፡፡

ለሲኖዶሳዊ ልዕልና መከበር የምእመናን ድርሻ አስፈላጊ ነው!

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ቤተ ክርስቲያን የመልካም አስተዳደር ችግሮች እና የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና አለመከበር እንዲሁም በርካታ ምእመናን በቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ጉዳዮች  ባይታዋር የሆኑበት፣ ቤተ  ክርስቲያንን ለካህናቱና ጳጳሳቱ ብቻ እየተው የመጡበት ሁኔታ ይታያል፡፡

ቅድስት ቤተ ክርስትያንን ፖለቲከኞች፣ አማሳኞች፣ ምንደኞች አገልጋዮች እንዲሁም የውስጥም ሆነ የውጭ ጠላቶቿ  አጀንዳ ሲያደርጓት፣ ባልዋለችበት ሲያውሏት፣ የማይገልጻትን ጥላሸት ሲቀቧት፣ ታሪኳን ሲሰርዙ፣ ሲደልዙ፣ የፕሮፖጋንዳ ሰለባ ሲያደርጓት፣ በባሰ ሁኔታ ኵላዊትነቷን፣ ዓለማቀፋዊነቷን  ወደ ጎን በማለት በርካሽ የጎሳ ከረጢት ሊከቷት ሲሞክሩ እያዩ ዝም ማለታቸው ነው፡

እግዚአብሔር ዝም ይላልን?

በየግል ሕይወታችን ችግር ሲገጥመን መፍትሔ ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር እንደምንጮኸው ሁሉ በቤተ ክርስቲያን ላይ መከራ ሲመጣም እንዲሁ ከርሱ መፍትሔ እንጠብቃለን። በእኛ መረዳት የዘገየ ወይም ዝም ያለ ሲመስለን “ለምን?” እንላለን። “ካህናት እየታረዱ፣ አብያተ ክርስቲያናት እየተቃጠሉ፣ ምእመናን እየተፈናቀሉ፣ ቅዱሳት መጻሕፍት እየተቆነጸሉ፣ ቤተ መቅደሱ እየተደፈረ፣ እንዴት እግዚአብሔር ዝም ይላል?” እንላለን። እንደዚህ የምንለው ምናልባትም አንዳች መቅሠፍት ወርዶ እንዲህ የሚያደርጉ ሰዎችን ያጠፋቸው ይሆናል ብለን ስለምንጠብቅና እንዳሰብነው ሳይሆን ሲቀር ሊሆን ይችላል። ምንም እናስብ ብቻ እኛ በጠበቅነው መንገድ ነገሮች ስላልሆኑ ግራ እንጋባለን፤ ከዚያም አልፈን ተስፋ እንቆርጣለን።

‹‹አቤቱ በፊትህስ ባለሟልነትን አግኝቼ እንደሆነ ባሪያህን አትለፈው›› (ዘፍ.፲፰፥፫)

ሥላሴ ሊቃውንት ‘የወይራ ዛፍ’ ብለው በተረጎሙት በመምሬ ዛፍ ሥር ተገለጠ፤ አብርሃምም ጎልማሳ እንግዶች መስለውት ወደ ቤቱ ወስዶ ያስተናገዳቸው ዘንድ ወደ እነርሱ ሮጠ፤ ‹‹ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ሮጠ›› እንዲል (ዘፍ.፲፰፥፪)። ቀርቦም ከምድር ወድቆ እጅ ነሣ፤ እንዲህም አላቸው። ‹‹አቤቱ በፊትህስ ባለሟልነትን አግኝቼ እንደሆነ ባሪያህን አትለፈው፤ ውኃ እናምጣላችሁ፤ እግራችሁን እንጠባችሁ።›› (ዘፍ.፲፰፥፫)

‹‹እስከ ሞት ድረስ የታመንክ ሁን›› (ራእ.፪፥፲)

የክርስትናን ሕይወትና ጉዞ መጀመር ቀላል ሲሆን ዳገት የሚሆነው መፈጸሙ ነው፡፡ ‹‹እስከ ሞት›› የመባሉም ዋናው ምክንያት ይህ ነው፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዕለተ ምጽአቱ ባስተማረበት የወንጌል ክፍልም ከዚህ ኃይለ ቃል ጋር በእጅጉ አንድ በሆነ መንገድ ‹‹እስከ መጨረሻ የሚጸና እርሱ ይድናል››  በማለት ያስተማረው ትምህርት መፈጸም እንደመጀመር ቀላል እንዳልሆነ የሚያስረዳን ነው፡፡ (ማቴ.፳፬፥፲፫)

እግዚአብሔር ዝም ይላልን?

በዓለም ስንኖር መከራና ደስታ፣ ውድቀትና ስኬት፣ ድካምና ብርታት ልዩ ልዩ ነገሮች ይፈራረቁብናል። በርግጥ ይህ አዲሳችን አይደለም። “በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ” ተብለናልና! እንኳን በክርስትና ሕይወት ውስጥ ያለንና መንፈሳዊ ጠላት ያለብን ሰዎች ማንኛውም ሰው ሰው በመሆኑ ብቻ ውጣ ውረድ ያጋጥመዋል። (ዮሐ.፲፮፥፴፫)