“ቄስ” ገዳሙ ደምሳሽ በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ ከቤተ ክርስቲያን አንድነት ተለዩ
ጥቅምት 5 ቀን 2007 ዓ.ም
በዲ/ን ፍቃዱ ዓለሙ
በኑፋቄ ትምህርታቸው ምእመናንን ሲቀስጡና የማኅበረ ካህናቱንና ምእመናኑን አንድነት ሲጎዱ የቆዩት “ቄስ” ገዳሙ ደምሳሽ በቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ ከቅስናና ከቤተ ክርስቲያን ሓላፊነት እንዲሁም ከማንኛውም ክህነታዊ አገልግሎትና ትምህርተ ወንጌል ከመስጠት ታገዱ፡፡
ቋሚ ሲኖዶሱ ሰኔ 18 ቀን 2006 ዓ.ም ውሳኔውን ያስተላለፈው ግለሰቡ ግልጽ ባልኾነ ሁኔታ የቪዝባደን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ኾነው ከመቀመጣቸው በፊት ወደ ፕሮቴስታንት የእምነት ተቋም ሔደው በቆዩባቸው ጊዜያት ጽፈው ያሳተሟቸው መጻሕፍት ይዘት በሊቃውንት ጉባኤ እንዲመረመር ካደረገ በኋላ መኾኑ በመግለጫው ታትቷል፡፡
በተጨማሪም ግልጽ ባልኾነ ሁኔታ ተመልሰዋል ተብሎ በሀገረ ጀርመን ካሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት አንዱ በኾነው ቪዝባደን ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተሾሙም በኋላ በልዩ ልዩ የጀርመን ግዛቶች እየተዘዋወሩ ሲያስተምሩ የነበረውን ፀረ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት በመቃወም በየጊዜው ከምእመናንና ካህናት የተላኩትን አቤቱታዎች እንደመረመረ መግለጫው ያብራራል፡፡
በሊቃውንት ጉባኤው ምርመራ መሠረት ጽሑፎቻቸው ግለሰቡ “የቤተ ክርስቲያናችንን የአብነት ትምህርት በውል ያልተማሩና ምሥጢራትን ያልተረዱ መኾናቸውን” የሚያሳዩ ከመኾናቸው በላይ የተሳሳቱና ኦርቶዶክሳዊ ያልኾኑ የኑፋቄ አስተምህሮዎችን የያዙ ናቸው፡፡ በመኾኑም እነዚህ መጻሕፍት በማንኛውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዙሪያ እንዳይሠራጩና ለማስተማሪያነትም እንዳይቀርቡ ታዝዟል፡፡ ይህ በቅዱስ ሲኖዶስ ተላልፎ ለደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅና ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት የተላከው ውሳኔ መስከረም 23 ቀን 2007 ዓ.ም በፍራክፈርት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሙሴ ሰብሳቢነት በተደረገ አጠቃላይ የአድባራት አስተዳዳሪዎችና የሰበካ ጉባኤ ተወካዮች ስብሰባ በውሳኔው የተለዩት ግለሰብም ባሉበት በንባብ መሰማቱን፤ በዚህም ወቅት ግለሰቡ ጉባኤውን ረግጠው መውጣታቸውን መግለጫው ያትታል፡፡
እኒህ ሰው በሀገረ ጀርመን ሲፈጠሯቸው የነበሩ ችግሮችን አስመልክቶ ከቦታው በሚደርሱን መረጃዎች በመመሥረት በኅትመቶቻችን ስንዘግብ መቆየታችን ይታወሳል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ዝርዝር በሚቀጥለው የስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ እናቀርባለን፡፡


በመንፈሳዊ ጉባኤው ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፤በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ተመድበው ቤተ ክርስቲያንን እያገለገሉ የሚገኙ፤ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የመምሪያ ሓላፊዎች፣ የየሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በማፍራት ላይ ቢገኝም በርካታ ችግሮች አሉበት፡፤ በዚህም መሠረት ደቀዛሙርቱ ከዘመኑ የቴክኖሎጂ ሽግግር ጋር ለማገናኘትና ከኢንተርኔት አጠቃቀም አንጻር ያለባቸውን ክፍተት ለመፍታት ለማኅበረ ቅዱሳን ባቀረብነው ጥያቄ መሠረት የኮምፒዩተሮችና የመጻሕፍት ድጋፍ በማድረጉ በመላው የኮሌጁ ማኅበረሰብና ደቀመዛሙርት ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡ ማኅበሩ እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነቱ እሰየሠጠ ካለው አገልግሎት አንጻር ወደፊት ተጨማሪ ድጋፎችንም እንደሚያደርግልን ተስፋ አደርጋለሁ” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የጅማ ሀገረ ስብከት ያስገነባው ባለ 5 ፎቅ ሁለገብ ዘመናዊ ሕንፃ መስከረም 25 ቀን 2007 ዓ.ም. በቅዱስ ፓትርያርኩና በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዚዳንት ተመረቀ፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፤ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት የልዩ ልዩ መምሪያ ሓላፊዎችና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ክፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በመሆን የጅማ ሀገረ ስብከት ከሃያ ስምንት ሚሊዮን አምስት መቶ አራት ሺሕ ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባውን ባለ አምስት ፎቅ ዘመናዊ ሁለገብ ሕንፃ ባርከው ሲመርቁ በሰጡት ቃለ ምእዳን “ይህ ሁለገብ ዘመናዊ ሕንፃ በጣም የሚያስደንቅና ለቤተ ክርስቲያናችን ተጨማሪ ሀብት መሆን የቻለ ነው፡፡ ለሌሎች ሀገረ ስብከቶችም ታላቅ ምሳሌና በአርአያነቱም ተጠቃሽ የሚሆን ነው” ብለዋል፡፡
ምክንያት የተቸገሩ በመሆናቸው ሕንፃው ተከራይቶ በሚያስገኘው ገቢ እነዚህን አብያተ ክርስቲያናት በመደገፍ አገልግሎት እንዳይቋረጥ ለማስቻል እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊት፣ ሐዋርያዊትና ታሪካዊት እንደ መሆኗ፣ ሁሉም ሃይማታዊ በዓላት ከመንፈሳዊ ባህላዊ ሥርዓቶች ጋር ተሣሥረው እንዲከበሩ መሠረት ናት፡፡ ለዚህ ነው ከሀገራዊና ከሃይማታዊ በዓላት ጋር ተያይዘው የሚከናወኑት መንፈሳዊና ባሕላዊ ሥርዓቶች ምንጫቸው/መነሻቸው/ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ናት የምንለው፡፡ ቀድሞም በኦሪቱ በኋላም በሐዲሱ ሕግጋት ጸንታ የቆየች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ወንጌልን በመላው ኢትዮጵያ ተዟዙራ አስተምራለች፡፡ ለመስቀሉም ሆነ ለሌሎች ሃይማታዊ በዓላት መነሻቸው የቀደሙት አባቶቻችን ከ4ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ የዘሩት የወንጌል ዘር ነው፡፡
በዓሉን ስናከብርም ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በማጉላት ሊሆን ይገባል፡፡ በስመ ዓለማቀፋዊነት ከሃይማኖታዊና ከባህላዊ ሥርዓቶች ውጭ ያሉትን እንደ ርችት መተኮስ፣ ጭፈራና ጩኸት ያሉ ሰርጎ ገብ ድርጊቶችን ወይም ልማዶችን መተው ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ድርጊቶች የበዓሉን ሃይማኖታዊ ይዘት ከመሸርሸራቸው ባለፈ የሀገራችንንም መልካም ገጽታ ስለሚያጎድፉ ነው፡፡