“የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ. . . ይጠቅማል” ክፍል ሁለት
ግንቦት 23 ቀን 2006 ዓ.ም.
ዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ
አዋልድ መጻሕፍት ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ያላቸው ተዛምዶ፡–
ቀደም ተብሎ እንደተለጠው አዋልድ መጻሕፍት ልጅነታቸው ለአሥራው መጻሕፍት (ለመጻሕፍት አምላካውያት) ነው፡፡ ልጅ ከአባቱ አብራክ፣ ከእናቱ ማኅጸን ተከፍሎ ወላጆቹንመስሎ እንዲወጣ እነዚህም በምሥጢርም በእምነትም በሥርአትም የአሥራውን መጻሕፍት ሥርና መሠረት ይዘው ተገኝተዋል፡፡ በምሥጢርም ኾነ በሥርዓት ከአሥራው መጻሕፍት ጋር የሚቃረኑት መጻሕፍት ከአዋልድ አይቆጠሩም፡፡ ምክንያቱም በሐዋርያው ቃል “ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን” ተብሏልና (ገላ.፩፥፰)፡፡
አዋልድ መጻሕፍት ከአሥራው መጻሕፍት ጋር ያላቸውን ተዛምዶ በሚከተሉት ነጥቦች መረዳት ይቻላል፡፡
ሀ. በዓይነታቸው፡- አሥራው መጻሕፍት ተብለው የሚታወቁት ሰማንያ አንዱ መጻሕፍት የሕግ፣ የታሪክ፣ የጥበብ፣ የትንቢት ተብለው ይመደባሉ፡፡
እንደዚሁም ሁሉ አዋልድ መጻሕፍት በዚሁ አንጻር የተዘጋጁ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ያህል ይህንን የማሳያ ሰንጠረዥ እንመልከት፡-
|
የመጻሕፍቱ ዓይነት |
የመጻሕፍቱ ይዘት |
|||
|
የሕግ |
የታሪክ |
የጥበብ |
የትንቢት |
|
|
አሥራው |
ብሔረ ኦሪት |
መጽሐፈ ሳሙኤል |
መዝሙረ ዳዊት |
ትንቢተ ኢሳይያስ |
|
አዋልድ |
ፍትሐ ነገሥት |
ተአምረ ማርያም |
ውዳሴ ማርያም |
ፍካሬ ኢየሱስ |
ለ. በባለቤታቸው፡-የቅዱሳት መጻሕፍት ባለቤታቸው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ምክንያቱም ቅዱሳት መጻሕፍት የእግዚአብሔር ገንዘቦች፣ በእርሱም ፈቃድና ምሪት የተፃፉ ሲሆኑ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ እግዚአብሔር በደሙ የዋጃት በምድር የእግዚአብሔር እንደራሴ የሆነች፣ የጸጋው ግምጅ ቤት ናት (የሐዋ.፳፥፳፰)፡፡ ስለሆነም ከእግዚአብሔር የተላኩ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስ ገልጦላቸው ወንጌልንና መልእክታትን የጻፉት ለቤተ ክርስቲያን ነው፡፡
የአዋልድ መጻሕፍት ጸሐፊዎች የቤተ ክርስቲያን ልጆች ሲሆኑ እነርሱም መንፈሰ እግዚአብሔር እንደገለጠላቸው መጠን መጻፍቱን የጻፉት ለቤተክርስቲያን ልጆች ለምእመናን ነው፡፡ በመሆኑም ባለቤታቸው ቤተ ክርስቲያን በመሆኗ ለትርጉማቸው፣ ለታሪካቸውና ለምሥጢራቸው መጠየቅ ያለባት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡
ሐ. በቅድስናቸው፡- አሥራው መጻሕፍትንም ሆነ አዋልድ መጻሕፍትን ያጻፈው መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ የአሥራው መጻሕፍትን ጸሐፍት እንደመረጠ እንዳተጋ ምሥጢር እንደገለጠላቸው፣ የአዋልድ መጻሕፍትን ጸሐፍት የመረጠ፣ ያተጋ፤ ምሥጢር የገለጠላቸው መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ ከአንዱ ምንጭ ከመንፈስ ቅዱስ በመገኘታቸውም የአሥራውም ሆኑ የአዋልድ መጻሕፍት ዓላማቸው ነገረ ሃይማኖትን ማስረዳት ደግሞም ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር መጥቀም ነው፡፡(፪ኛ.ጢሞ.፫፥፲፮)
በልዩ ልዩ ዘመናትና ሰዎች በተራራቀ ሀገር ተጽፈው ለየብቻቸው የነበሩትን አሥራው መጻሕፍት ከመሠረተ ሃይማኖት አንጻር መርምራ አረጋግጣ በአሥራው መጻሕፍትነት የተቀበለችው ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ አዋልድ መጻሕፍትንም የምትቀበለው በተመሳሳይ መልኩ ከትምህርቷ አንፃር መርምራ አረጋግጣ ነው፡፡
መ. የእግዚአብሔርን ሥራ በመግለጥ፡- የቅዱሳት መጻሕፍት ተቀዳሚ ዓላማ የእግዚአብሔርን ሥራ መግለጥ ነው፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍት እግዚአብሔር በቀጥታ ራሱ ወይም በወዳጆቹ አድሮ ለሕዝቡ ያደረገውን ተአምር፣ መግቦት፣ ቸርነት ያብራራሉ፡፡ይህ እውነታ በአሥራው መጻሕፍት በስፋትና በይፋ የተገለጠ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ዓላማቸው የእግዚአብሔርን ሥራ መግለጥ ከመሆኑ የተነሣ የእግዚአብሔር ሥራ ተአምር የተፈጸመላቸውንና የተፈጸመባቸውን ሰዎች፣ ቦታዎች እምብዛም ትኩረት አይሰጧቸውም፡፡ ተአምሩን ብቻ ገልጠው የሰዎችንና የቦታዎችንስምእገሌ፣አንድሰው ብለው ያልፋሉ፡፡ (ማቴ.፳፮፥፲፰፣፩ኛ. ነገ፲፫፥፩፣ ማቴ.፰፥፪፣ ሉቃ.፲፩፥፲፭) ይህ በአሥራው መጻሕፍት ብቻ የሚንጸባረቅ ሳይሆን የአዋልድ መጻሕፍትም ዓላማ ነው፡፡ በገድለ ተክለሃይማኖት፣ በገድለ ጊዮርጊስ፣ በተአምረ ማርያም ውስጥ በቅዱሳን አማላጅነት የእግዚአብሔር ሥራ (ተአምር) የተፈጸመላቸው ወይም የተፈጸመባቸው ሰዎችን ስም፣ ቦታ ሳያነሡ እገሌ፤ እገሊት አንድ ሰው ብለው የሚጠሩት ሰዎቹና ቦታዎቹ መጠሪያ ስለሌላቸው ሳይሆን ዓላማቸው የእግዚአብሔርን ሥራ መግለጥ ስለሆነ ነው፡፡
ሠ. የሃይማኖትን ታላቅነት በመግለጥ፡- ቅዱሳት መጻሕፍት በሃይማኖት፣ ለሃይማኖት፣ ስለሃይማኖት የተጻፉ ናቸው፡፡ ከጥርጥር፣ ከአጉል አሳብ ተጠብቆ በመጻሕፍቱ የተገለጠውን፣ የታዘዘውን ለጠበቀ የተባለው ይፈጸምለታል፡፡ ሠለስቱ ደቂቅ ሃይማኖትን ገንዘብ አደረጉ፡፡ በሃይማኖትም ሕግ ታዝዘው ለጣዖት መስገድን እምቢ አሉ፡፡ በዚህ የተነሣ ከእሳት ቢጣሉ በሃይማኖት የእሳትን ኃይል አጠፉ፡፡ ነቢዩ ዳንኤል በሃይማኖት የአናብስትን አፍ ዘጋ፡፡ ጌዴዎን ያለ ጦር መሣሪያ አእላፍ የአሕዛብን ሠራዊት ድል አደረገ፡፡ ይህ የሃይማኖትን ታላቅነት ያስረዳል (ዕብ.፲፩፥፴፫-፴፬)፡፡ በአዋልድ መጻሕፍትም አቡነ ኤውስጣቴዎስ በአጽፋቸው (በመጎናጸፊያቸው) ባሕር ሲከፍሉ፣ ፃድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ከንብ ቀፎ ተከተው በቆዳ ተጠቅልለው ከተወረወሩበት ገደል ሲወጡ፣ ከእሳት መካከል ቆመው እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ፤ቅዱስ ጊዮርጊስ የሚቆራርጥ መርዝ ሲያጠጡት ሕያው ሆኖ የሚያሳየን የሃይማኖትን ታላቅነት ነው፡፡
በአሥራውም ሆነ በአዋልድ መጻሕፍት የተጠቀሱት ሰዎች ታላላቅ ተአምራት ሲፈጽሙ የምንመለከተው መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌሉ “አማን አማን እብለክሙ ዘየአምን ብየ ዘአነ እገብር ውእቱሂ ይገብር ወዘየዐቢ ይገብር፤ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል፤” ያለው ቃል ተፈጽሞላቸው ነው፡፡(ዮሐ.፲፬፥፲፪)፡፡
ረ. የሃይማኖትሰዎች ያደረጓቸውን ልዩ ልዩ ተጋድሎዎችን መግለጥ፡- እግዚአብሔር ድንቅ የሆነ ሥራውን ለፍጥረቱ የሚሠራው በፍጥረቱ አማካኝነት ነው፡፡ ይህም በልዩ ልዩ መንገድ ይፈጸማል፡፡ የእግዚአብሔር ሥራ በስፋትና በግልጥ ከሚሠራባቸው ፍጡራን መካከል ደግሞ ቅዱሳን ዋንኞቹ ናቸው፡፡ ቅዱሳን ለሕገ እግዚአብሔር ተገዝተው ፈቃዱን በመፈጸማቸው ንጽሐ ልቡናን ገንዘብ አደረጉ፡፡ በዚህ ሰውነታቸውም ከእግዚአብሔር በተቀበሉት ኃይል ብዙ ተጋድሎ ፈጽመዋል፡፡ የአሥራውም ሆኑ አዋልድ መጻሕፍት ይህን የቅዱሳንን የተጋድሎ ሕይወት ይገልጣሉ፡፡ ነሕምያ የኢየሩሳሌምን ቅጥር መሥራቱ፣ አስቴር በጾም በጸሎት ሕዝበ እሥራኤልን ስለመታደጓ፣ ዮዲት በጥበብ ሆሊፎርንስን መግደሏ፣ ቅዱስ ጴጥሮስ በጥላው ሕሙማንን መፈወሱ፣ እመቤታችን፣ጻድቃን ሰማእታት ልዩ ልዩ ገቢረ ተአምራት መፈጸማቸው በየቅዱሳት መጻሕፍቱ ተገልጦ እናገኛለን፡፡
አዋልድ መጻሕፍትን ቤተ ክርስቲያን የምትቀበለው እንዴት ነው?
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አዋልድ መጻሕፍትን የምትቀበልበት ሥርዓት አላት፡፡ ቀደም ተብሎ በተደጋጋሚ እንደተገለጠው የአዋልድ መጻሕፍት ልጅነታቸው በይዘት፣በመንፈስ፣ በምሥጢርና በመሠረተ ሐሳብ ነው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት “አሥራው መጻሕፍት” ይባላሉ፡፡ አሥራው ማለት ሥሮች ማለት ሲሆን፣ አሥራው መጻሕፍት ሲላቸው ደግሞ የሌሎች መጻሕፍት መገኛዎች፣ ሥሮች ማለት መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ ይህም ማለት ለአዋልድ መጻሕፍት በይዘትና በመንፈስ፣ በምሥጢርና በመሠረተ ሐሳብ አስገኚ ሥራቸውና ወላጃቸው መጽሐፍ ቅዱስ ኾኖ በእርሱ ሥርነት የሚበቅሉና የሚያድጉ ማለት ነው፡፡
ይህ ኾኖ ሳለ በአንዳንድ ይዘታቸው፣ መጽሐፍ ቅዱስን ቢመስሉም ከመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ፣በጌታችን ከተገለጠውና ከሐዋርያት ጀምሮ ሲያያዝ ከመጣው የቤተክርስቲያንእምነትና ትምህርት ጋር ተቃርኖ ያላቸውን መጻሕፍት ቤተ ክርስቲያን ታወግዛለች እንጂ አትቀበልም፡፡ መጻሕፍቱም “ዲቃሎች” እንጂ “አዋልድ” አይባሉም፡፡
አዋልድ መጻሕፍትን በተመለከተ በሚከተሉት ነጥቦች መለየት እንደሚቻል ሕንዳዊው የነገረ መለኮት ሊቅ ጢሞቴዎስ አለን ይገልጡታል፡-
-
ዓላማቸው መንግሥተ እግዚአብሔር የሆነ፣
-
በሃሳብ፣ በመንፈስ፣ በምሥጢር፣ በነገረ መለኮት ከአሥራው መጻሕፍትና ከቅዱሳት የቤተ ክርስቲያን ትውፊት ጋር የማይጋጩ፣
-
ለክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር፣ ሕይወትና አኗኗር ተስማሚ የሆኑ፣
-
የቤተ ክርስቲያን አበው፣ትውፊት ወይም ጉዞ ምስክር ያላቸው፣
-
ውስጣዊ ተቃርኖ የሌለባቸው፡፡
እንግዲህ በጎ ትምህርት የሚያስተምሩንን፣ ስለ ቅዱሳን አበውና እመው ሃይማኖታዊ ተጋድሎ የምንረዳባቸውን፣ አሥራው መጻሕፍትንም የሚያብራሩልንና የሚተረጉሙልንን አዋልድ መጻሕፍትን በመጠቀም በሃይማኖት ለመጽናት፣ በጎ ሥራ ለመሥራት ፈጣሪያችን ልዑል እግዚአብሔር ይርዳን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር


ከግንቦት 6 ቀን 2006 ዓ. ም. ጀምሮ ሲካሔድ የቆየው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ግንቦት 19 ቀን 2006 ዓ. ም. መግለጫ በመስጠት ተጠናቋል፡፡ ጉባኤው ሲጠናቀቅ በቀረበው መግለጫም ውሳኔ ሳያገኙ የቀሩ አጀንዳዎችን አካቷል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ፡-

የኢየሩሳሌም መታሰቢያ ድርጅት 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዩበልዩ በዓል ግንቦት 16 ቀን 2006 ዓ.ም. ቦሌ በሚገኘው በድርጅቱ ሕንፃ አከበረ፡፡ በመርሐ ግብሩ ላይ ቅዱስ ፓትርያርኩ፤ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፤ የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት አቶ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ፤ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶችና የድርጅቱ አባላት ተገኝተዋል፡፡
በኢየሩሳሌም ውስጥ ለሚገኙት ገዳማት ታላቅና ታሪካዊ የሆነ በዓል ነው፡፡ 50 ዓመታትን ተስፋ ሳይቆርጡ እዚህ ላደረሱት የድርጅቱ ሓላፊዎችና ምእመናን ሁሉ ምሥጋናዬን አቀርባለሁ፡፡ የኢየሩሳሌም መታሰቢያ ድርጅት አገልግሎት ወደፊትም ሳይቋረጥ እንዲቀጥል ከሥሩ ተተኪ ምእመናንን ማፍራት አለበት” ብለዋል፡፡
የድርጅቱ መሥራችና የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አለማየሁ ተስፋዬ የድርጅቱን አመሠራረት አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በ1955 ዓ.ም. ሠላሳ አባላት ያሉት የምእመናን ቡድን በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ውስጥ የሚገኙትን የኢትዮጵያ ገዳማትን ለመጎብኘት ተጉዘው እንደነበር ይገልጻሉ፡፡ አባላቱ በአውሮፕላኑ ሠራተኞች አማካይነት ወደ ዴር ሱልጣን ገዳም ተወስደው በዴር ሱልጣን ገዳም በሚገኙ ኢትዮጵያውያን መነኮሳት ላይ የኮፕት ኦርቶዶክሶች ያደርሱባቸው የነበረውን ከፍተኛ በደል ተመልክተዋል፡፡ መነኮሳቱም ተጎሳቁለው በከፍተኛ ችግር ውስጥ ወድቀው እንዳገኟቸው አቶ አለማየሁ ተስፋዬ ይናገራሉ፡፡

ቀጭን መንገድ ተያያዝነው፡፡ ወንዙ ምን ይባላል አልናቸው ለአንድ አዛውንት “ የማርያም ዥረት ነው የሚባለው” አሉን ፡፡ እንደመቀነት የሚጠማዘዘውን ቀጭን መንገድ እየተከተልን ወደ ዋሻው አፋፍ ደረስን፡፡ ወደ ዋሻው መግቢያ በስተቀኝ በኩል በመጠኑ የጎደጎደ ሥፍራ ይታያል፡፡ ምን እንደሆነ ጠየቅን፡፡ “ከተራራው ሥር እየፈለቀ የሚወርድ ማየገቦ የሚጠራቀምበት ጉድጓድ ነበር፤ (ማየገቦ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተሰቀለ ጊዜ በቦታው ያልነበረው አንድ ዓይና ሌንጊኖስ ከአይሁድ ጋር ለመተባበር ብሎ ኢየሱስ ክርስቶስን በጦር ቢወጋው ውኃና ደም እንደ ለ ፊደል ፈሷል ፡፡ የፈሰሰው ውኃ ማየገቦ ይባላል፡፡) ዋሻው ቤተ መቅደስ ከተደረመሰ በኋላ ደርቋል” አሉን አዛውንቱ፡፡
ዋሻው የተደረመሰበት ዋነኛ ምክንያት እንደሆነ የሚታመነውም በወቅቱ አንዲት ሴት ለአሰግድመኝ ቅድስት ማርያም ገዳም አንድ ጋሻ መሬት ለመገበሪያ ብላ በስጦታ ለግሳ ነበር፡፡ አገልግሎት ሲሰጥ የተወሰኑ ዓመታት እንደተቆጠሩም ሴትየዋ ቃሏን በማጠፍ መሬቱን ከእመቤታችን በመውሰድ ለሌላ ግለሰብ ሰጠችው፡፡ ሴትየዋም ይህንን በማድረጓ ለሰባት ዓመታት በደዌ ዳኛ ተይዛ ስትማቅቅ ቆይታ አርፋለች፡፡ አስከሬኗንም በዚሁ ገዳም አምጥተው ይቀብሩታል፡፡ እመቤታችን ለአባቶች እየተገለጠች “የዚህችን ሴት አስከሬን ከዚህ ቦታ አውጡልኝ፤ ሸተተኝ” እያለች ነግራቸዋለች፡፡ ነገር ግን ተግባራዊ ባለማድረጋቸው ሐምሌ 23 ቀን 1951 ዓ.ም. ዋሻ ቤተ ክርስቲያኑ ሊፈርስ ችሏል፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስም የሴትየዋ ግማሽ አስከሬን ከአንድ ድንጋይ ተጣብቆ ተንጠልጥሎ የነበረ ሲሆን አሁን የት እንደሔደ አይታወቅም በማለት የዋሻውን መደርመስ ምክንያት አወጉን፡፡
የተዘጋጀውን መገበሪያ የበላችው አቃቢት አስከሬን እንደሆነና እንደ ሎጥ ሚስት የጨው አምድ ሆና መድረቋን ነገሩን፡፡ ሳጥኑ በቀላሉ የሚከፈት ሲሆን በአቡጀዲ የተጠቀለለውን አስከሬን ለማየት ቻልን፡፡ አስከሬኑ ሙሉ ለሙሉ አልፈረሰም፡፡
ትኩረታችንን ሳበውና ጅብ ዋሻ ማርያም የት ነው? ጅብ ዋሻ ለምን ተባለ? ጅብ ዋሻ እንዴት ይኬድ ነበር? በማለት ለጠየቅነው ጥያቅ የጅብ ዋሻ ማርያም የተባለበትንም ምክንያት የቀይት ወረዳ ቤተ ክህነት ሊቀ ካህናት ቀሲስ ብርሃኑ ለገሰ እንዲህ በማለት ያስረዱን ጀመር “ጀብ ዋሻ ማርያም /አሁን ገነት ዋሻ ቅድስት ማርያም ተብሎ ይጠራል/ ከተመሠረተ 620 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ በአካባቢው አንድ ሰው ሞቶ ፍታት ለማድረግ በቤተ ክርስቲያን የነበረውን ከበሮ ወደ ውጪ ወጥቶ ፀሐይ እንዲሞቅ ይደረጋል፡፡
ታቦት ነች፡፡ ስዕለት ሰሚ፤ ተአምር አድራጊ በመሆኗ ወደዚህ ቦታ የማይመጣ ክርስቲያን አልነበረም፡፡ ልጅ ስለነበርን “እስከ ጅብ ዋሻ ማርያም ድረስ ውስጥ ለውስጥ የሚያስኬድ መንገድ አለ፡፡” ሲሉ ሰምተን ከጓደኞቼ ጋር ቅብዓ ኑግ የኑግ ጭማቂ በገል አድርገን እያበራን ውስጥ ለውስጥ ሄደናል፡፡ በጣም ያስፈራል፤ በዋሻው ውስጥ ባህር አለ፡፡ ማን እንዳዘጋጀው ለምን እንደተዘጋጀ ባናውቅም በዋሻው ውስጥ ወደ ጅብ ዋሻ ሄደናል” ሲሉ የቦታዋን ታሪክ ነገረውናል፡፡
ቅዱስ እንጦንስ ገዳም (Sankt-Antonius Kloster) በደማቅ ሁኔታ አካሄደ።



“መንፈሰ እግዚአብሔር ያለበት፣ ሰውን ከክፋት፣ ከኃጢአት፣ ከበደል የሚመልስ፤ ይልቁንም ሃይማኖቱን የሚያጸናለት መጽሐፍ ከእግዚአብሔር ነውና ይጠቅማል” በማለት ቅዱስ ጳውሎስ የተናገረው ቃል ነው፡፡ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን ቃል ያስተላለፈው ለጊዜው በሃይማኖት ትምህርት ወልዶ ላሳደገው ለደቀመዝሙሩ ጢሞቴዎስ ቢኾንም ፍጻሜው ግን እስከ ሕልፈተ ዓለም ለሚነሡ ክርስቲያኖች ሁሉ የተናገረው ነው፡፡ “የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።” (፪ኛ. ጢሞ.፫፥፲፮-፲፯)
በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በቀይት ወረዳ ቤተ ክህነት ሥር በጉዶ በረት አካባቢ የምትገኘውን ጥንታዊትና ታምረኛዋን ገዳም እንድንዘግብላቸው በተደጋጋሚ ቢሯችን በመምጣትና ስልክ በመደወል ቀጠሮ ያስያዙንን የርዕሰ አድባራት ወገዳማት ዳግሚት ፅዮን አዲስ ዓለም ማርያም ገዳም አስተዳዳሪ ንቡረ ዕድ አባ ገብረ ሕይወት መልሴ ጋር በነበረን ቀጠሮ መሠረት ሚያዚያ 15 ቀን 2006 ዓ.ም. ከሌሊቱ 12፡30 ወደ አሰግድመኝ ቅድስት ማርያም ገዳም ለመጓዝ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በር ላይ እና ላም በረት አካባቢ ከሚገኘው መናኸሪያ በር ተገናኝተናል፡፡
ንቡረ ዕድን በረድእነት እያገለገሏቸው የሚገኙት ታናሽ ወንድማቸውን ቀሲስ እንግዳወርቅ መልሴ ድርሳናትንና ገድላትን እንዲያነቡ አዘዟቸውና እያደመጥን በየመሐሉ አቡነ ዘበሰማያት እየተሰጠን እየጸለይን ደብረ ብርሃን ከተማ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም ቤት ደረስን፡፡
መምሬ ጥላዬ በአስግድመኝ ማርያም አካባቢ ተወላጅና ለረጅም ዘመናት ታቦቷን በማገልገል የሚታወቁ የእድሜ ባለጸጋ አባት ናቸው፡፡ ስለ አሰግድመኝ ማርያም የሚያውቁትን እንዲነግሩን ጠየቅናቸው፡፡
ወንበሮ ኪዳነ ምሕረት በአንድ አቅራቢያ የሚገኙ አድባራት በመሆናቸው አንድ ላይ አገልግሎት ይሰጥባቸው ነበር፡፡ በተለይ በወንበሮ ኪዳነ ምሕረት በርካታ የአብነት ተማሪዎችና መሪ ጌቶች ይገኙ ነበር፡፡ በዚህ ሥፍራም የንባብና የዜማ ትምህርት ሲሰጥበት የቆየ ሲሆን ዛሬም የአገልጋዮቹ ቁጥር ቢቀንስም አገልግሎት እየተሰጠበት ነው፡፡ ድሮ አባቶች አሰግድመኝ ቅድስት ማርያም ቀድሰው እዚያው መክፈልት አይቀምሱም ነበር፡፡ ለቦታው ካላቸው አክብሮት የተነሣ በገዳሙ ዙሪያ ምግብ ስለማይበላ ከቅደሴ መልስ ወንበሮ ኪዳነ ምሕረት እየሄዱ ነበር ምግብ የሚቀምሱት፡፡”
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የግንቦቱ ርክበ ካህናት ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ግንቦት 5 ቀን 2006 ዓ.ም. በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በጸሎት ተጀምሯል፡፡ ግንቦት 6 ቀን 2006 ዓ.ም. በቅዱስ ፓትርያርኩ የመክፈቻ መልእክት ጉባኤው ቀጥሏል፡፡