የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠርና አጠቃቀሙ
ዲ/ን ኃ/ኢየሱስ ቢያ
የዘመን አቆጣጠር ማለት፡- ዓመታትን፤ ወራትን፣ ሳምንታትን፣ ዕለታትን፤ ደቂቃንና ድቁቅ ሰዓታትን በየሥፍራቸው የሚገልጽ፤ የሚተነትን፤ የሚለካ የቤተ ክርስቲያን የቁጥር ትምህርት ነው፡፡
እነዚህ ሁሉ ተመርምረው ተመዝነው ተቆጥረው ሲያበቁ ምድብና ቀመር ተሰጥቶአቸው የሚገኙበትን ውሳኔና ድንጋጌ የሚያሰማ የዘመን አቆጣጠር ሐሳበ ዘመን ይባላል፡፡
ዓመታታ፣ ወራት፣ ሳምንታት፣ ዕለታትና ሰዓታት የሚለኩት /የሚቆጠሩት በሰባቱ መሰፈሪያና በሰባቱ አዕዋዳት ነው፤ እነሱም፡-
1. ሰባቱ መስፈርታት
– ሳድሲት
– ኃምሲት
– ራብዒት
– ሣልሲት
– ካልዒት
– ኬክሮስ
– ዕለት ይባላሉ
2. ሰባቱ አዕዋዳት
– ዐውደ ዕለት፡- ከእሑድ እስከ ቅዳሜ ያሉት ሰባቱ ዕለታት ናቸው፤ አውራህን ለማስገኘት በዚህ ሲመላለሱ ይኖራሉ፡፡
– ዐውደ ወርኅ፡- በፀሐይ 30 ዕለታት በጨረቃ 29/30 ዕለታት ናቸው ዓመታትን ለማስገኘት በዚህ ሲመላለሱ ይኖራሉ፡፡
– ዐውደ ዓመት፡- በፀሐይ ቀን አቆጣጠር 365 ቀን ከ15 ኬክሮስ፡፡ በጨረቃ ቀን አቆጣጠር 354 ቀን ከ22 ኬኬሮስ ነው፡፡ እነዚህ 3ቱ በዕለት ሲቆጠሩ አራቱ በዓመት ይቆጠራሉ፡፡ ዘመናትን ለማስገኘት በዚህ ሲመላለሱ ይኖራሉ፡፡
– ዐውደ ፀሐይ፡- 28 ዓመት ነው በዚህ ዕለትና ወንጌላዊ ይገናኙበታል፡፡
– ዐውደ አበቅቴ፡- 19 ዓመት ነው በዚህ ፀሐይና ጨረቃ ይገናኙበታል፡፡
– ዐውደ ማኅተም፡- 76 ዓመት ነው በዚህ አበቅቴና ወንጌላዊ ይገናኙበታል፡፡
– ዐውደ ቀመር፡- 532 ዓመት ነው በዚህ ዕለትና ወንጌላዊ አበቅቴም ይገናኙበታል፡፡
የዘመናት/የጊዜያት ክፍልና መጠን
1 ዓመት በፀሐይ 365 ቀን ከ15 ኬክሮስ፣ በጨረቃ 354 ቀን ከ22 ኬኬሮስ ነው፡፡ 1 ወር በፀሐይ 30 ዕለታት አሉት በጨረቃ 29/30 ዕለታት አሉት፡፡ ዕለት 24 ሰዓት ነው፤ ቀን 12 ሰዓት ነው ፤ ሰዓት 60 ደቂቃ ነው ፤ ደቂቃ 60 ካልዒት ነው ፤ካልዒት 1 ቅጽበት ነው፡፡ ኬክሮስ ማለት የክፍል ዕለት ሳምንት ነው /የዕለት 1/60ኛው ወይም 1/24ኛ ሰዓት ነው/ 1 ዕለት 24 ሰዓት ወይም 60 ኬክሮስ ማለት ነው፡፡
ክፍለ ዓመት /የዓመት ክፍሎች/
1. መፀው፡- ከመስከረም 26 እስከ ታኅሳስ 25 ቀናት ድረስ ያለው ክፍለ ዓመት መጸው ይባላል፡፡ በዚህ ክፍለ ዓመት ሌሊቱ ረጅም ቀኑ አጭር ነው፡፡
2. በጋ፡- ከታኅሳስ 26 እስከ መጋቢት 25 ቀናት ድረስ ያለው ክፍለ ዓመት በጋ ይባላል፡፡ በዚህ ክፍለ ዓመት የቀኑና የሌሊቱ ርዝመት እኩል ነው፡፡
3. ፀደይ፡- ከመጋቢት 26 እስከ ሰኔ 25 ቀናት ድረስ ያለው ፀደይ ይባላል፡፡ በዚህ ክፍለ ዓመት ቀኑ ይረዝማል ሌሊቱ ያጥራል፡፡
4. ክረምት፡- ከሰኔ 26 እስከ መስከረም 25 ቀናት ድረስ ያለው ክረምት ይባላል፡፡ በዚህ ከፍለ ዓመት የቀኑና የሌሊቱ ርዝመት እኩል ነው፡፡
በአራቱ ወንጌላውያን መካከል የዘመናት አከፋፈል /ርክክብ/
1. ማቴዎስ ዘመኑን ከምሽቱ በ 1ሰዓት ጀምሮ በዓመቱ ከሌሊቱ በ6 ሰዓት ይፈጽማል፡፡
2. ማርቆስ ዘመኑን ከሌሊቱ በሰባት ሰዓት ጀምሮ በዓመቱ ከጠዋቱ በ12 ሰዓት ይፈጽማል፡፡
3. ሉቃስ ዘመኑን ከጠዋቱ በ1 ሰዓት ጀምሮ በዓመቱ በቀትር በ6 ሰዓት ይፈጽማል፡፡
4. ዮሐንስ ዘመኑን ከቀኑ በሰባት ሰዓት ጀምሮ በዓመቱ ከቀትር በኋላ በ12 ሰዓት ይፈጽማል፡፡
የየወራቱ ሌሊትና ቀን ስፍረ ሰዓት
1. የመስከረም ወር ሌሊቱ 12 ሰዓት መዐልቱ 12 ሰዓት ነው፡፡
2. የጥቅምት ወር ሌሊቱ 13 ሰዓት መዐልቱ 11 ሰዓት ነው፡፡
3. የኅዳር ወር ሌሊቱ 14 ሰዓት መዐልቱ 10 ሰዓት ነው፡፡
4. የታኅሣሥ ወር ሌሊቱ 15 ሰዓት መዐልቱ 9 ሰዓት ነው፡፡
5. የጥር ወር ሌሊቱ 14 ሰዓት መዐልቱ 10 ሰዓት ነው፡፡
6. የየካቲት ወር ሌሊቱ 13 ሰዓት መዐልቱ 11 ሰዓት ነው፡፡
7. የመጋቢት ወር ሌሊቱ 12 ሰዓት መዐልቱ 12 ሰዓት ነው፡፡
8. የሚያዝያ ወር ሌሊቱ 11 ሰዓት መዐልቱ 13 ሰዓት ነው፡፡
9. የግንቦት ወር ሌሊቱ 10 ሰዓት መዐልቱ 14 ሰዓት ነው፡፡
10. የሰኔ ወር ሌሊቱ 19 ሰዓት መዐልቱ 15 ሰዓት ነው፡፡
11. የሐምሌ ወር ሌሊቱ 10 ሰዓት መዐልቱ 14 ሰዓት ነው፡፡
12. የነሐሴ ወር ሌሊቱ 11 ሰዓት መዐልቱ 13 ሰዓት ነው፡፡
የበዓላትና የአጽዋማት ኢየዐርግና ኢይወረድ
1. ጾመ ነነዌ ከጥር 17 ቀን በታች ከየካቲት 21 ቀን በላይ አይውልም
2. ዐቢይ ጾም ከየካቲት 1 ቀን በታች ከመጋቢት 5 ቀን በላይ አይውልም
3. ደብረ ዘይት ከየካቲት 28 ቀን በታች ከሚያዝያ 2 ቀን በላይ አይውልም፡፡
4. በዓለ ሆሣዕና ከመጋቢት 19 ቀን በታች ከሚያዝያ 23 ቀን በላይ አይውልም፡፡
5. በዓለ ስቅለት ከመጋቢት 24 ቀን በታች ከሚያዝያ 28 ቀን በላይ አይውልም፡፡
6. በዓለ ትንሣኤ ከመጋቢት 26 ቀን በታች ከሚያዝያ 3ዐ ቀን በላይ አይውልም፡፡
7. ርክበ ካህናት ከሚያዝያ 20 ቀን በታች ከግንቦት 24 ቀን በላይ አይውልም፡፡
8. በዓለ ዕርገት ከግንቦት 5 ቀን በታች ከሰኔ 19 ቀን በላይ አይውልም፡፡
9. ጾመ ሐዋርያት ከግንቦት 16 ቀን በታች ከሰኔ 20 ቀን በላይ አይውልም፡፡
10. ጾመ ድኅነት ከግንቦት 18 ቀን በታች ከሰኔ 22 ቀን በላይ አይውልም፡፡
ሁለት ዓይነት የተውሳክ አቆጣጠር አለ
1. የዕለት ተውሳክ በቅዳሜ ይጀምራል፡፡
የቅዳሜ ተውሳክ 8፤ የእሑድ ተውሳክ 7፤ የሰኞ ተውሳክ 6፤ የማክሰኞ ተውሳክ 5፤ የረቡዕ ተውሳክ 4፤ የሐሙስ ተውሳክ 3፤ የዓርብ ተውሳክ 2
2. የአጽዋማትና የበዓላት ተውሳክ
የነነዌ ተውሳክ 0፤ የዐቢይ ጾም ተውሳክ 14፤ የደብረ ዘይት ተውሳክ 1፤ የሆሣዕና ተውሳክ 2፤ የስቅለት ተውሳክ 7፤ የትንሣኤ ተውሳክ 9፤ የርክበ ካህናት ተውሳክ 3፤ የዕርገት ተውሳክ 18፤ የጰራቅሊጦስ 28፤ የጾመ ሐዋርየት ተውሳክ 29፤ የጾመ ድኅነት ተውሳክ 1
በዓላትና አጽዋማት የሚውሉበት ቀን
– ጾመ ነነዌ
– ዐብይ ጾም
– ጾመ ሐዋርያት
ሰኞ
– ደብረ ዘይት
– ሆሣዕና
– ትንሣኤ
– ጰራቅሊጦስ
እሑድ
– ስቅለት
ዓርብ
– ርክበ ካህናት
– ጾመ ድኅነት
ረቡዕ
– ዕርገት
ሐሙስ ቀን ይሆናል፡፡
ይቀጥላል