የሰው ሰውነት ክፍሎች
ነሐሴ 23 ቀን 2005 ዓ.ም.
በመ/ርት ኖኀሚን ዋቅጅራ
ባለፈው ግእዝን ይማሩ አምዳችን ላይ የግእዝ ቁጥሮችን አጻጻፍና የንባብ ስያሜአቸውን ማቅረባችን የሚታወስ ነው፡፡ ዛሬ ደግሞ የሰውነት ክፍሎችን ማቅረባችንን እንቀጥላለን፡፡
የሰውነት ክፍሎች፣ ከአንገት በላይ የአካል ክፍሎች፣ /ክፍላተ አካላት ዘላዕለ ክሳድ/
የአንገት በላይ የአካል ክፍሎች ማለት ከእራስ ፀጉራችን ጀምሮ እስከ አንገታችን ድረስ ያሉትን የአካል ክፍሎች ያካተተ /የያዘ/ ክፍል ማለት ነው፡፡ እነዚህንም የአካል ክፍሎች ከዚህ በመቀጠል እንመለከታለን፡፡
ሰብእ – ሰው
– ሰብእ ዘተፈጥረ እምነ ሠለስቱ ባሕርየተ ነፍስ ምስለ አርባዕቱ ባሕርያተ ሥጋ ውእቱ
ሰው የተፈጠረው ከሦስቱ ባሕርያተ ነፍስ እና ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋ ነው፡፡
– ሠለስቱ ባሕርያተ ነፍስ ብሂል
ሦስቱ ባሕርያተ ነፍስ ማለት
፩. ሕያዊት – ሕዋሳትን የምታንቀሳቅስ ሕይወት ያላት
፪. ለባዊት – ልብ የምታደርግ /የምታስብ/
፫. ነባቢት – የምትናገር
አርባዕቱ ባሕርያተ ሥጋ ብሂል
አራቱ የሥጋ ባሕርያት ማለት
- ነፋስ – የነፋስነት ባሕርይ – አፍ – አፍ
- እሳት – የእሳትነት ባሕርይ – ስን – ጥርስ
- ማይ – የውኃነት ባሕርይ – ልሳን – ምላስ
- መሬት – የመሬትነት ባሕርይ – ቃል – ቃል
- ድማሕ /ናላ/ – መሀል ራስ /አናት/ – ዕዝን – ጆሮ
- ናላ – አናት – መልታህ – ጉንጭ
- ስእርት – የራስ ፀጉር – አንፍ – አፍንጫ
- ጽፍሮ – ሹርባ – ከንፈር – ከንፈር
- ድንጉዝ – ጥቅል ሥራ – ሕልቅ – አገጭ
- ድምድማ – የተበጠረ ጎፈሬ – ጽሕም – ጢም
- ሲበት – ሽበት – ክሳድ – አንገት
- ገጽ – ፊት – ምጉንጳ – የዐይን ሽፋን
- ፍጽም – ግንባር – ዓይን – ዐይን
- ከዋላ – ኋላ የድምጽ ክፍላት
- ቅርንብ – ቅንድብ – ፋጻ – ፍጨት
- ዕዝን – ጆሮ – ጒሕና – ጎርናና /ወፍራም/ ድምጽ
- መልታህ – ጉንጭ – ቃና – የዜማ ድምጽ, እስትንፋስ – ትንፋሽ