ዝርዝር ርባታ
መምህር በትረማርያም አበባው
የካቲት ፳፰ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም
ውድ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? የእግዚአብሔር አምላካችን ስም የተመሰገነ ይሁን! ባለፈው የትምህርታችን ክፍለ ጊዜ የ ‹‹ሀ፣ አ፣ ወ እና የ›› የሚያመጡት የርባታ ለውጥ በግሥ ርባታ አስተምረናችሁ ነበር፡፡ በዚህ ሳምንት ደግሞ ለሰጠናችሁ መልመጃ ምላሽና ስለ ዝርዝር ርባታ እንመለከታለን፤ በጥሞና ተከታተሉን!
የመልመጃ ጥያቄዎች
የሚከተሉትን ግሦች ከካልአይ እስከ ትእዛዝ አንቀጽ አርቡ!
፩) ፈረየ፤አፈራ
፪) ወለደ፤ወለደ
፫) ሰወረ፤ሸሸገ
የጥያቄዎች መልስ
፩) ፈረየ አፈራ
ይፈሪ፤ያፈራል
ይፍረይ፤ያፈራ ዘንድ
ይፍረይ፤ያፍራ
፪) ወለደ፤ወለደ
ይወልድ፤ይወልዳል
ይለድ፤ይወልድ ዘንድ
ይለድ፤ይውለድ
፫) ሰወረ፤ሸሸገ
ይሴውር፤ይሸሽጋል
ይሰውር፤ይሸሽግ ዘንድ
ይሰውር፤ይሸሽግ
ዝርዝር ርባታ
ባለቤትንና ተሳቢን በአንድ ላይ የሚያሳውቅ ርባታ ዝርዝር ርባታ ይባላል። ይህንንም ሙሉውን ክፍል ‹‹አፍቀረ፤ወደደ›› በሚለው ቃል መነሻነት እንመለከተዋለን።
ውእቱ አፍቀረ፤ እርሱ ወደደ
ያፈቅር፤ይወዳል ያፍቅር፤ይወድ ዘንድ ያፍቅር፤ይውደድ ውእቶሙ አፍቀሩ፤ እነርሱ ወደዱ ያፈቅሩ፤ይወዳሉ ያፍቅሩ፤ይወዱ ዘንድ ያፍቅሩ፤ይውደዱ ይእቲ አፍቀረት፤ እርሷ ወደደች ታፈቅር፤ትወዳለች ታፍቅር፤ትወድ ዘንድ ታፍቅር፤ትውደድ ውእቶን አፍቀራ፤ እነርሱ ወደዱ ያፈቅራ፤ይወዳሉ ያፍቅራ፤ይወዱ ዘንድ ያፍቅራ፤ይውደዱ አንተ አፍቀርከ፤አንተ ወደድክ ታፈቅር፤ትወዳለህ ታፍቅር፤ትወድ ዘንድ አፍቅር፤ውደድ |
አንትሙ አፍቀርክሙ፤ እናንተ ወደዳችሁ
ታፈቅሩ፤ትወዳላችሁ ታፍቅሩ፤ትወዱ ዘንድ አፍቅሩ፤ውደዱ አንቲ አፍቀርኪ፤አንቺ ወደድሽ ታፈቅሪ፤ትወጃለሽ ታፍቅሪ፤ትወጂ ዘንድ አፍቅሪ፤ውደጂ አንትን አፍቀርክን፤እናንተ ወደዳችሁ ታፈቅራ፤ትወዳላችሁ ታፍቅራ፤ትወዱ ዘንድ አፍቅራ፤ውደዱ አነ አፍቀርኩ፤ እኔ ወደድኩ አፈቅር፤እወዳለሁ አፍቅር፤እወድ ዘንድ አፍቅር፤ልውደድ ንሕነ አፍቀርነ፤እኛ ወደድን ናፈቅር፤እንወዳለን ናፍቅር፤እንወድ ዘንድ ናፍቅር፤እንውደድ |
ከዚህ በላይ ያሉት ግሦች ዝርዝር ባለቤትን ብቻ እንጂ ተሳቢውን አያሳውቁም ስለሆነም ‹‹ንኡስ ርባታ›› ይባላል። ዝርዝር ርባታን በዐሥር ክፍል እንደሚከተለው እናቀርባለን።
ውእቱ ውእቱን ሲወድ፦
አፍቀሮ/አፍቀራሁ፤ወደደው ያፈቅሮ/ያፈቅራሁ፤ይወደዋል ያፍቅሮ/ያፍቅራሁ፤ይወደው ዘንድ ያፍቅሮ/ያፍቅራሁ፤ይውደደው ውእቱ ውእቶሙን ሲወድ፦ አፍቀሮሙ/አፍቀራሆሙ፤ወደዳቸው ያፈቅሮሙ/ያፈቅራሆሙ፤ይወዳቸዋል ያፍቅሮሙ/ያፍቅራሆሙ፤ይወዳቸው ዘንድ ያፍቅሮሙ/ያፍቅራሆሙ፤ይውደዳቸው። ውእቱ ይእቲን ሲወድ፦ አፍቀራ/አፍቀራሃ፤ወደዳት ያፈቅራ/ያፈቅራሃ፤ይወዳታል ያፍቅራ/ያፍቅራሃ፤ይወዳት ዘንድ ያፍቅራ/ያፍቅራሃ፤ይውደዳት ውእቱ ውእቶንን ሲወድ፦ አፍቀሮን/አፍቀራሆን፤ወደዳቸው ያፈቅሮን/ያፈቅራሆን፤ይወዳቸዋል ያፍቅሮን/ያፍቅራሆን፤ይወዳቸው ዘንድ ያፍቅሮን/ያፍቅራሆን፤ይውደዳቸው ውእቱ አንተን ሲወድ፦ አፍቀረከ/አፍቀራከ፤ወደደህ ያፈቅረከ/ያፈቅራከ፤ይወድሀል ያፍቅርከ/ያፍቅራከ፤ይወድህ ዘንድ ያፍቅርከ/ያፍቅራከ፤ይውደድህ ውእቱ አንትሙን ሲወድ፦ አፍቀረክሙ/አፍቀራክሙ፤ወደዳችሁ ያፈቅረክሙ/ያፈቅራክሙ፤ይወዳችኋል ያፍቅርክሙ/ያፍቅራክሙ፤ይወዳችሁ ዘንድ ያፍቅርክሙ/ያፍቅራክሙ፤ይውደዳችሁ ውእቶሙ አንተን ሲወዱ፦ አፍቀሩከ፤ወደዱህ ያፈቅሩከ፤ይወዱሃል ያፍቅሩከ፤ይወዱህ ዘንድ ያፍቅሩከ፤ይውደዱህ ውእቶሙ አንትሙን ሲወዱ፦ አፍቀሩክሙ፤ወደዷችሁ ያፈቅሩክሙ፤ይወዷችኋል ያፍቅሩክሙ፤ይወዷችሁ ዘንድ ያፍቅሩክሙ፤ይወደዷችሁ ውእቶሙ አንቲን ሲወዱ፦ አፍቀሩኪ፤ወደዱሽ ያፈቅሩኪ፤ይወዱሻል ያፍቅሩኪ፤ይወዱሽ ዘንድ ያፍቅሩኪ፤ይውደዱሽ ውእቶሙ አንትንን ሲወዱ፦ አፍቀሩክን፤ወደዷችሁ ያፈቅሩክን፤ይወዷችኋል ያፍቅሩክን፤ይወዷችሁ ዘንድ ያፍቅሩክን፤ይውደዷችሁ |
ውእቱ አንቲን ሲወድ፦
አፍቀረኪ/አፍቀራኪ፤ወደደሽ ያፈቅረኪ/ያፈቅራኪ፤ይወድሻል ያፍቅርኪ/ያፍቅራኪ፤ይወድሽ ዘንድ ያፍቅርኪ/ያፍቅራኪ፤ይውደድሽ ውእቱ አንትንን ሲወድ፦ አፍቀረክን/አፍቀራክን፤ወደዳችሁ ያፈቅረክን/ያፈቅራክን፤ይወዳችኋል ያፍቅርክን/ያፍቅራክን፤ይወዳችሁ ዘንድ ያፍቅርክን/ያፍቅራክን፤ይውደዳችሁ ውእቱ አነን ሲወድ፦ አፍቀረኒ/አፍቀራኒ፤ወደደኝ ያፈቅረኒ/ያፈቅራኒ፤ይወደኛል ያፍቅረኒ/ያፍቅራኒ፤ይወደኝ ዘንድ ያፍቅረኒ/ያፍቅራኒ፤ይውደደኝ ውእቱ ንሕነን ሲወድ፦ አፍቀረነ/አፍቀራነ፤ወደደን ያፈቅረነ/ያፈቅራነ፤ይወደናል ያፍቅረነ/ያፍቅራነ፤ይወደን ዘንድ ያፍቅረነ/ያፍቅራነ፤ይውደደን ውእቶሙ ውእቱን ሲወዱ፦ አፍቀርዎ፤ወደዱት ያፈቅርዎ፤ይወዱታል ያፍቅርዎ፤ይወዱት ዘንድ ያፍቅርዎ፤ይውደዱት ውእቶሙ ውእቶሙን ሲወዱ፦ አፍቀርዎሙ፤ወደዷቸው ያፈቅርዎሙ፤ይወዷቸዋል ያፍቅርዎሙ፤ይወዷቸው ዘንድ ያፍቅርዎሙ፤ይውደዷቸው ውእቶሙ ይእቲን ሲወዱ፦ አፍቀርዋ፤ወደዷት ያፈቅርዋ፤ይወዷታል ያፍቅርዋ፤ይወዷት ዘንድ ያፍቅርዋ፤ይውደዷት ውእቶሙ ውእቶንን ሲወዱ፦ አፍቀርዎን፤ወደዷቸው ያፈቅርዎን፤ይወዷቸዋል ያፍቅርዎን፤ይወዷቸው ዘንድ ያፍቅርዎን፤ይውደዷቸው ውእቶሙ አነን ሲወዱ፦ አፍቀሩኒ፤ወደዱኝ ያፈቅሩኒ፤ይወዱኛል ያፍቅሩኒ፤ይወዱኝ ዘንድ ያፍቅሩኒ፤ይውደዱኝ ውእቶሙ ንሕነን ሲወዱ፡- አፍቀሩነ፤ወደዱን ያፈቅሩነ፤ይወዱናል ያፍቅሩነ፤ይወዱን ዘንድ ያፍቅሩነ፤ይውደዱን |
ውድ አንባብያን! ከላይ የተመለከትናቸውን የግሥ ርባታዎች እንደተረዳችሁ ተስፋ እንናደርጋለን፤ የቀሩትን ዝርዝር ርባታዎች ደግሞ በሚቀጥለው የትምህርት ክፍለ ጊዜያችን ይዘንላችሁ እንቀርባለን፡፡
ይቆየን!