ንዑስ አንቀጽና ቅጽሎች

መምህር በትረማርያም አበባው

ሚያዚያ ፮ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም

የተወደዳችሁ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? የእግዚአብሔር አምላካችን ስም የተመሰገነ ይሁን! በተከታታይ በሦስት ክፍል የግሥ ዝርዝር ርባታን እንዳቀረብንላችሁ ይታወቃል፤ በዚህ የትምህርት ክፍለ ጊዜያችን ደግሞ በተማራችሁት መሠረት ላቀረብንላችሁ የመልመጃ ጥያቄዎች ምላሻቸውን እንዲሁም ንዑስ አንቀጽና ቅጽሎችበሚል ርእስ የዛሬውን ትምህርት ይዘንላችሁ ቀርበናል፤ በጥሞና ተከታተሉን!     

የመልመጃ ጥያቄዎች፦

የሚከተሉትን ቃላት የአማርኛ ትርጒማቸውን ጻፉ!

፩) ሠመርናሃ (ሠምረ፤ወደደ)

፪) ፈጠረኒ (ፈጠረ፤ፈጠረ)

፫) ኀረይኩክሙ (ኀረየ፤መረጠ)

፬) ነአኵተከ (አእኮተ፤አመሰገነ)

፭) መሐርኩከ (መሐረ፤ይቅር አለ)

የጥያቄዎች መልሶች

፩) ወደድናት

፪) ፈጠረኝ

፫) መረጥኳችሁ

፬) እናመሰግንሃለን

፭) ይቅር አልኩህ

ንዑስ አንቀጽና ቅጽሎች

የስምንቱ ሠራዊት የየራሳቸው የሆነ ንዑስ አንቀጽ አላቸው። በተጨማሪ የቆመ፣ የሤመ፣ የነደ፣ የገብረን ቤት የመሰሉ ግሦች ንዑስ አንቀጻቸው እንዴት እንደሆነ እንመለከታለን።

ግእዝ አማርኛ
ቀቲል/ቀቲሎት መግደል
ቀድሶ/ቀድሶት ማመስገን
ተንብሎ/ተንብሎት መለመን
ክሂል/ክሂሎት መቻል
ጦምሮ/ጦምሮት መጻፍ
ሴስዮ/ሴስዮት መመገብ
ባርኮ/ባርኮት ማመስገን
ማሕርኮ/ማሕርኮት መማረክ
ሠይም/ሠይሞት መሾም
ቀዊም/ቀዊሞት መቆም
ገቢር/ገቢሮት መሥራት
ነዲድ/ነዲዶት መንደድ

በግሥ አወራረድ ከንዑስ አንቀጽ ጀምሮ የሚገሠሠው ሣልስ ውስጠ ዘ ነው። ቅጽል ማለት ስለ አንድ ነገር ተጨማሪ ገላጭ ነገርን የሚያመለክት ሲሆን ብዙ ጊዜ በግእዝ ቋንቋ ቅጽል የሚሆኑ ሣልስ ውስጠዘ፣ ሳድስ ውስጠ ዘ፣ ግልጸ ዘ፣ መድበል፣ ባዕድ ቅጽል፣ መስም ቅጽል እና ዘሮች ደግሞ ዘርፍ ይዘው ከሆነ ነው። ስለዚህ መጀመሪያ ሣልስ ቅጽሎችን በስምንቱ አርእስተ ግሥ እንመልከት፦

            ሣልስ ውስጠዘ

ተ.ቁ. ግእዝ አማርኛ ፆታ
ቀታሊ ገዳይ ወንድ
ቀታልያን ገዳዮች ብዙ ወንዶች
ቀታሊት ገዳይ ሴት
ቀታልያት ገዳዮች ብዙ ሴቶች
ቀዳሲ አመስጋኝ ወንድ
  ቀዳስያን አመስጋኞች ብዙ ወንዶች
  ቀዳሲት አመስጋኝ ሴት
  ቀዳስያት አመስጋኞች ብዙ ሴቶች
ተንባሊ ለማኝ ወንድ
  ተንባልያን ለማኞች ብዙ ወንዶች
  ተንባሊት ለማኝ ሴት
  ተንባልያት ለማኞች ብዙ ሴቶች
ባራኪ አመስጋኝ ወንድ
  ባራክያን አመስጋኞች ብዙ ወንዶች
  ባራኪት አመስጋኝ ሴት
  ባራክያት አመስጋኞች ብዙ ሴቶች
ማሕራኪ ማራኪ ወንድ
  ማሕራክያን ማራኪዎች ብዙ ወንዶች
  ማሕራኪት ማራኪ ሴት
  ማሕራክያት ማራኪዎች ብዙ ሴቶች
ሴሳዪ መጋቢ ወንድ
  ሴሳይያን መጋቢዎች ብዙ ወንዶች
  ሴሳዪት መጋቢ ሴት
  ሴሳይያት መጋቢዎች ብዙ ሴቶች
ከሃሊ ቻይ ወንድ
  ከሃልያን ቻዮች ብዙ ወንዶች
  ከሃሊት ቻይ ሴት
  ከሃልያት ቻዮች ብዙ ሴቶች
ጦማሪ ጸሐፊ ወንድ
  ጦማርያን ጸሐፍያን ብዙ ወንዶች
  ጦማሪት ጸሐፊት ሴት
  ጦማርያት ጸሐፊዎች ብዙ ሴቶች
ቀዋሚ ቋሚ ወንድ
  ቀዋምያን ቋሚዎች ብዙ ወንዶች
  ቀዋሚት ቋሚ ሴት
  ቀዋምያት ቋሚዎች ብዙ ሴቶች
ሠያሚ ሿሚ ወንድ
  ሠያምያን ሿሚዎች ብዙ ወንዶች
  ሠያሚት ሿሚ ሴት
  ሠያምያት ሻሚዎች ብዙ ሴቶች
፲፪ ገባሪ ሠሪ ወንድ
  ገባርያን ሠሪዎች ብዙ ወንዶች
  ገባሪት ሠሪ ሴት
  ገባርያት ሠሪዎች ብዙ ሴቶች

ሣልስ ቅጽል በሦስት ይተረጎማል ለምሳሌ ቀዳሲ ብሎ ያመሰገነ፣ የሚያመሰግን፣ አመስጋኝ ተብሎ ይተረጎማል ማለት ነው። ሌላውም እንዲሁ ነው። በአምስቱ አእማድ ይገኛል። ለምሳሌ ተቀታሊ የተገደለ የሚገደል፣ ተገዳይ ይባላል። አቅታሊ ደግሞ የሚያስገድል አስገዳይ ያስገደለ ይባላል። አስተቃታሊ ደግሞ የሚያገዳድል፣ ያገዳደለ፣ አገዳዳይ ይባላል። ተቃታሊ ደግሞ ተገዳዳይ፣ የሚገዳደል፣ የተገዳደለ ተብሎ ይተረጎማል። በስምንቱም አርእስት እንዲሁ እያለ ይዘልቃል።                

ሳድስ ውስጠዘ

ከሣልስ ቅጽል ቀጥሎ የሚገሠሠው ደግሞ ሳድስ ውስጠዘ ነው። እርሱንም ከስምንቱ አርእስት ቀጥለን እንመለከታለን።

ተ.ቁ. ግእዝ አማርኛ ፆታ
ቅቱል የተገደለ ወንድ
ቅቱላን የተገደሉ ብዙ ወንዶች
ቅትልት የተገደለች ሴት
ቅቱላት የተገደሉ ብዙ ሴቶች
ቅዱስ የተመሰገነ ወንድ
  ቅዱሳን የተመሰገኑ ብዙ ወንዶች
  ቅድስት የተመሰገነች ሴት
  ቅዱሳት የተመሰገኑ ብዙ ሴቶች
ትንቡል የተለመነ ወንድ
  ትንቡላን የተለመኑ ብዙ ወንዶች
  ትንብልት የተለመነች ሴት
  ትንቡላት የተለመኑ ብዙ ሴቶች
ቡሩክ የተመሰገነ ወንድ
  ቡሩካን የተመሰገኑ ብዙ ወንዶች
  ቡርክት የተመሰገነች ሴት
  ቡሩካት የተመሰገኑ ብዙ ሴቶች
ምሕሩክ የተማረከ ወንድ
  ምሕሩካን የተማረኩ ብዙ ወንዶች
  ምሕርክት የተማረከች ሴት
  ምሕሩካት የተማረኩ ብዙ ሴቶች
ሲሱይ የመገበ ወንድ
  ሲሱያን የመገቡ ብዙ ወንዶች
  ሲሲት የመገበች ሴት
  ሲሱያት የመገቡ ብዙ ሴቶች
ክሁል የቻለ ወንድ
  ክሁላን የቻሉ ብዙ ወንዶች
  ክህልት የቻለች ሴት
  ክሁላት የቻሉ ብዙ ሴቶች
ጡሙር የጻፈ ወንድ
  ጡሙራን የጻፉ ብዙ ወንዶች
  ጡምርት የጻፈች ሴት
  ጡሙራት የጻፉ ብዙ ሴቶች
ቅውም የቆመ ወንድ
  ቅውማን የቆሙ ብዙ ወንዶች
  ቅውምት የቆመች ሴት
  ቅውማት የቆሙ ብዙ ሴቶች
ሥዩም የተሾመ ወንድ
  ሥዩማን የተሾሙ ብዙ ወንዶች
  ሥይምት የተሾመች ሴት
  ሥዩማት የተሾሙ ብዙ ሴቶች
፲፪ ግቡር የተሠራ ወንድ
  ግቡራን የተሠሩ ብዙ ወንዶች
  ግብርት የተሠራች ሴት
  ግቡራት የተሠሩ ብዙ ሴቶች

ሳድስ ውስጠ ዘ አንዱ ብቻ በ፲፭ ይተረጎማል። ለምሳሌ ቅዱስ ያለውን ብቻ ብንወስድ ያመሰገነ፣ የተመሰገነ፣ ያስመሰገነ፣ የተመሰጋገነ፣ ያመሰጋገነ፣ አመስጋኝ፣ ተመስጋኝ፣ አስመስጋኝ፣ ተመሰጋጋኝ፣ አመሰጋጋኝ፣ የሚያመሰግን፣ የሚመሰገን፣ የሚያስመሰግን፣ የሚያመሰጋግን፣ የሚመሰጋገን ተብሎ ይተረጎማል። ሌላውም እንዲሁ እያለ ይቀጥላል።

መድበል

መድበል የሚባለው ትርጉሙ የብዙ ሴቶች ወይም የብዙ ወንዶች ውስጠዘ ጋር ይመሳሰላል። ይህም ማለት ምሳሌ ቀደስት ብንል ቅዱሳን እና ቅድስት ከሚለው ጋር በትርጉም ተመሳሳይ ነው ማለታችን ነው። በስምንቱ መራሕያን እንደሚከተለው ይቀርባል።

ግእዝ አማርኛ
ቀተልት የገደሉ
ቀደስት ያመሰገኑ
ተንበልት የለመኑ
ባረክት ያመሰገኑ
ማሕረክት የማረኩ
ሴሰይት የመገቡ
ከሀልት የቻሉ
ጦመርት የጻፉ
ቀወምት የቆሙ
ሠየምት የሾሙ
ገበርት የሠሩ

ቅዱሳን፣ ቀደስት እና ቅዱሳት የሚሉት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው። በ፲፭ም ይተረጎማሉ። የሌሎችም እንዲሁ ምሳሌ ሥዩማን፣ ሥዩማት እና ሠየምት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው። የቀደስትን ሙሉ ትርጉም ለመጻፍ ያህል፦ያመሰገኑ፣ የተመሰገኑ፣ ያስመሰገኑ፣ የተመሰጋገኑ፣ ያመሰጋገኑ፣ አመስጋኞች፣ ተመስጋኞች፣ አስመስጋኞች፣ ተመሰጋጋኞች፣ አመሰጋጋኞች፣ የሚያመሰግኑ፣ የሚመሰገኑ፣ የሚያስመሰግኑ፣ የሚያመሰጋግኑ፣ የሚመሰጋገኑ ተብሎ ይተረጎማል።

 ባዕድ ሳድስ ቅጽል

ባዕድ ቅጽል ከመነሻው ባዕድ ፊደል ን ጨምሮ የሚገሠሥ ሲሆን በስምንቱ አርእስት እንደሚከተለው ይቀርባል። ትርጉሙ እንደ ሳድስ ውስጠ ዘው በ፲፭ ይተረጎማል። ለምሳሌ የቀተለን ብናይ

መቅትል፣መስተቅትል፣መስተቃትል ቅቱል ካለው ጋር ተመሳሳይ ትርጉም አለው።

መቅትላን፣መስተቅትላልን፣መስተቃትላን የሚለው ደግሞ ቅቱላን ካለው ጋር ተመሳሳይ ትርጉም አለው።

መቅትልት፣መስተቅልት፣መስተቃትልት ያለው ደግሞ ከ ቅትልት ጋር ተመሳሳይ ትርጉም አለው።

መቅትላት፣መስተቅትላት መስተቃትላት ያለው ደግሞ ቅቱላት ካለው ጋር ተመሳሳይ ትርጉም አለው። ቀሪዎችን አርእስት ቀጥለን እንመልከት።

መቀድስ፣መስተቀድስ፣መስተቃድስ

መቀድሳን፣መስተቀድሳን፣መስተቃድሳን

መቀድስት፣መስተቀድስት፣መስተቃድስት

መቀድሳት፣መስተቀድሳት፣መስተቃድሳት

መተንብል፣መስተተንብል፣መስተተናብል

መተንብላን፣መስተተንብላን፣መስተተናብላን

መተንብልት፣መስተተንብልት፣መስተተናብልት

መተንብላት፣መስተተንብላት፣መስተተናብላት

መባርክ፣መስተባርክ

መባርካን፣መስተባርካን

መባርክት፣መስተባርክት

መባርካት፣መስተባርካት

መማሕርክ፣መስተማሕርክ፣መስተማሓርክ

መማሕርካን፣መስተማሕርካን፣መስተማሓርካን

መማሕርክት፣መስተማሕርክት፣መስተማሓርክት

መማሕርካት፣መስተማሕርካት፣መስተማሓርካት።

መሴስይ፣መስተሴስይ፣መስተሴያስይ፣መስተስያስይ፣መስተሲያስይ፣መስተሰያስይ

መሴስያን፣መስተሴስያን፣መስተሴያስያን፣መስተስያስያን ፣መስተሲያስያን፣መስተሰያስያን

መሴስይት፣መስተሴስይት፣መስተሴያስይት፣መስተስያስይት፣መስተሰያስይት፣መስተሲያስይት

መሴስያት፣መስተሴስያት፣መስተሴያስያት፣መስተሲያስያት፣መስተሰያስያት፣መስተስያስያት።

መክህል፣መስተክህል፣መስተካህል

መክህላን፣መስተክህላን፣መስተካህላን

መክህልት፣መስተክህልት፣መስተካህልት

መክህላት፣መስተክህላት፣መስተካህላት

መጦምር፣መስተጦምር፣መስጡዋምር፣መስተጠዋምር፣መስተጥዋምር

መጦምራን፣መስተጦምራን፣መስተጡዋምራን፣መስተጠዋምራን፣መስተጥዋምራን

መጦምርት፣መስተጦምርት፣መስተጡዋምርት፣መስተጠዋምርት፣መስተጥዋምርት

መጦምራት፣መስተጦምራት፣መስተጡዋምራት፣መስተጠዋምራት፣መስተጥዋምራት።

መቀውም፣መስተቀውም፣መስተቃውም

መቀውማን፣መስተቀውማን፣መስተቃውማን

መቀውምት፣መስተቀውምት፣መስተቃውምት

መቀውማት፣መስተቀውማት፣መስተቃውማት

መሠይም፣መስተሠይም፣መስተሣይም

መሠይማን፣መስተሠይማን፣መስተሣይማን

መሠይምት፣መስተሠይምት፣መስተሣይምት

መሠይማት፣መስተሠይማት፣መስተሣይማት

መግብር፣መስተግብር፣መስተጋብር

መግብራን፣መስተግብራን፣መስተጋብራን

መግብርት፣መስተግብርት፣መስተጋብርት

መግብራት፣መስተግብራት፣መስተጋብራት

በትርጉም ከዚህ ጋር የሚመሳሰል ባዕድ ሣልስ ቅጽል የሚባልም አለ። ይኽውም መድረሻውን ሣልስ አድርጎ ከመነሻው ባዕድ የሚጨምር ነው። ለምሳሌ የቀተለን ብቻ ብንመለከት።

‹መቅተሊ፣መስተቅተሊ፣መስተቃትሊ› ልክ እንደ ቅቱል ይተረጎማል።

‹መቅተልያን፣መስተቅተልያን፣መስተቃትልያን› እንደ ቅቱላን ይተረጎማል።

‹መቅተሊት፣መስተቅተሊት፣መስተቃትሊት› እንደ ቅትልት ይተረጎማል።

‹መቅተልያት፣መስተቅተልያት፣መስተቃትልያት› እንደ ቅቱላት ይተረጎማል።

የመልመጃ ጥያቄዎች

፩) ለሚከተሉት ቃላት ሣልስ ውስጠ ዘ አውጡ!

ሀ) ጸሐፈ-ጻፈ

ለ) ሠዐለ-ሣለ

ሐ) ኖለወ-ጠበቀ

፪) ለሚከተሉት ቃላት ንዑስ አንቀጽ አውጡ!

ሀ) አርመመ-ዝም አለ

ለ) ነጸረ-አየ

ሐ) አእመረ-አወቀ

፫) ለሚከተሉት ቃላት ሳድስ ውስጠ ዘ አውጡ!

ሀ) ሠምረ-ወደደ

ለ) ከብረ-ከበረ

ሐ) አፍቀረ-ወደደ

መ) ፈጠረ-ፈጠረ

፬) ለሚከተሉት ቃላት ባዕድ ቅጽል አውጡ!

ሀ) ወደሰ-አመሰገነ

ለ) ናዘዘ-አረጋጋ

፭) ለሚከተሉት ቃላት  መድበል አውጡ!

ሀ) ጸሐፈ

ለ) ኖመ

ሐ) መርሐ