New Search

If you are not happy with the results below please do another search

1 search result for:

1

‹‹ኑ ምሳ ብሉ›› (ዮሐ.፳፩፥፲፪)

ይህን ኃይለ ቃል የተናገረው ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ቃሉን  ደግሞ የሚበላ ፈልገው ዓሣ ለማጥመድ ሌሊቱን ሲደክሙ ለነበሩ ግን የሚፈልጉትን ሳያገኙ በረኀብ ዝለው በፍለጋ ደክመው ለነበሩ ለቅዱሳን ሐዋርያት ነው፡፡ ሞትን በሞቱ ገድሎ፣ በትንሣኤው ትንሣኤያችንን አብሥሮ፣ ሞትን ድል አድርጎ ከተነሣ በኋላ ለቅዱሳን ሐዋርያት በጥብርያዶስ ባሕር ዳርቻ ተገለጠላቸው፤ ይህ ከትንሣኤው በኋላ ሲገለጥላቸው ሦስተኛው ጊዜ ነው፡፡ መጀመሪያ ሲገለጥላቸው አይሁድን ፈርተው በፍርሃት ተሸብበው በራቸውን ዘግተው በተስፋ መቁረጥ ውስጥ በነበሩ ጊዜ በዝግ ቤት ገብቶ ፍርሃትን አስወገደላቸው ተስፋቸውን ቀጠለላቸው፤ ለተረበሸው ልባቸው ‹‹ሰላም ለእናንተ ይሁን›› በማለት ሰላምን ሰጣቸው አረጋጋቸው፡፡ (ሉቃ.፳፬፥፴፮፣ዮሐ.፳፥፲፱)