ቃና

በመዝሙርና ሥነ ጥበባት ክፍል

  • በገሊላ ከተማ…ልዩ ስሟ ቃና

ልብን ደስ የሚያሰኝ ተሰማባት ዜና

ጵርስቅላን ሊድር ዶኪማስ ደግሷል

ፍሪዳውን አርዶ…

…የወይን ጠጁንም በጋኖቹ ጥሏል

ከቤተ ዘመዱ!…

  • …ድንግል ማርያምን በሰርጉ ላይ ጠራ

ድንግል ማርያምን እናቱን ሲጠራ…

…ልጇን መለየቱ አይገባምና…

…ብሎ አሳሰባት… ኢየሱስ ክርስቶስ…

….ደቀመዛሙርቱ ይምጡልኝ አደራ

  • ሰርገኛው በደስታ በዳሱ ታድሟል

ጵርስቅላን ሊወስድ ዮስጦስ ተገኝቷል

የተጠራች እናት ከልጇ ጋር ሁና…

…ደቀ መዛሙርቱን ከኋላ አስከትላ

ዶኪማስ ቤት መጣች ከናዝሬት ገሊላ

  • አገልጋዮች ታጥቀው ጠጅ እያሳለፉ

ደስታቸው ተሟጦ በድንገት ተከፉ

ርኅርኅተ ልቡና…

  • …መከፋታቸውን ከፊታቸው አይታ

የወይን ጠጅ አልቋል… ስትል አሳሰበች…

…ለአማናዊው መጠጥ ለሠራዊት ጌታ

አላት ለእናቱ…

  • …“እንኳን ለወይኑ ጠጅ!… ገና የአዳም ዘር…

…በሕይወት እንዲኖር…

…ሥጋየን ይበላል ደሜንም ይጠጣል”

ልጅ!.. ሲሆን ለእናቱ እንዲህ ይታዘዛል፡፡

አሳላፊዎችን ጠርታ ስታዝዝ በቃሉ

እያለች ከኢየሱስ ትእዛዝ ተቀበሉ

የድንጋዩ ጋኖች በውኃ ተሞሉ

  • ውኃውም ተቀድቶ ሲሞላ በጋኑ

ጋኖቹም በሙሉ የወይን ጠጅ ሆኑ

አሳዳሪው ቀምሶ ወይኑን አደነቀ

ቀድሞ የጠጣውን መናኛውን ናቀ

ዶኪማስ በሰርጉ…

…እናት እና ልጇን በአንድ ስለጠራ…

…ጎዶሎውን ሞላ

በጌታ ተባርከው…

  • …ከብረዋል ሙሽሮች ዮስጦስ ጵርስቅላ

የቃና ሰርግ ቤት ጌታውን ወደደ

ጵርስቅላ ፀንሳ ከዮስጦስ አብራክ ሙሴ ተወለደ

የኢትዮጵያ ጳጳስ ሚናስ ተወለደ፡፡