የ፳፻፲፫ መስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ 

የ፳፻፲፫ መስቀል ደመራ በዓል የኮሮና በሽታ ወረርሽኝን ለመከላከል የሃይማኖት አባቶችን ጨምሮ አምስት ሺህ ተሳታፊዎች ብቻ  በተገኙበት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ተከብሯል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ማቲያስ፣ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ ዲፕሎማቶችና ሌሎች የማኅበረሰብ ክፍሎች ታድመዋል።

የደመራ በዓል ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች የተከናወኑ ሲሆን ዝማሬዎችም ቀርቧል።