ሀገሬ!

የካቲት ፳፤፳፻፲፮ ዓመተ ምሕረት

የወለድሽኝ ክብርት እናቴ

ነሽና መገኛ የማንነቴ

አሳዳጊዬ ማርና ወተቴ

መልካሟ ልጅነቴ

በአንቺ ነው መኖሬ

የምወድሽ ሀገሬ

ፊደላትን ቆጥሬ

ሃይማኖትን ተምሬ

ያፈራሁብሽ ፍሬ!

ነውና የዘወትር ጸሎቴ

እንዳይለየኝ ከአንዲቷ ቤቴ

ቅድስት ቤተ ክርስቲያኔ

ሰላም የሆንሽው ለእኔ!

ፍቅርንም ሰጠሽኝ

ስኖር በብቸኝነት

መከታ ሆነሽኝ

ስማቅቅ በድህነት

ሕይወቴ ሊሆን አንዲያ ልጅሽ

ተወልዷልና ከኅቱም ድንግልናሽ

የአምላክ ማደሪያ ከሆነው ማኅፀንሽ

እመቤቴ ሆይ፥ ቤዛዬ ልበልሽ!

ለነፍሴ የሆነልኝ ድኅነት

ስማጸነው ሁል ጊዜ ሳልታክት

ካራቀኝ ከአምላኬ በኃጢአት

ጠላቴን ላሸንፈው የቻልኩት

ስለሆንሽኝ ነው ብርታት

ኃይል ጽንዕ ሰጥተሽኝ በልኬት

ሥጋዬን ገትቼ እንድኖር በትጋት

ጌታዬን እንዳስብ በክብር በስብሐት!