መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::




‹‹እኔ ሰላማዊ ነኝ!›› (መዝ.፻፲፱፥፯)
ሰላም “ፍጹም ጤና፣ ዕረፍት፣ ዕርቅ፣ ፍቅር፣ አንድነት” ነው፡፡ (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላት ገጽ ፰፻፷፮) አንድ ሰው ሰላም አለው ሲባል ጤነኛ እና ለሰዎች ፍቅር ያለው ኅብረትን አንድነትን የሚወድ ማለት ነው፡፡ ሰላም ለሰዎች ሁሉ አስፈላጊና መሠረታዊ ከሆኑ ነገሮችም አንዱ ነው፤ ማንኛውንም ነገር ለማከናወን ቅድሚያ ሰላም መሆን አስፈላጊ ነው፤ በሕይወታችን ደስተኛ ሆነን ለመኖር፣ አእምሮአችንን ከጭንቀት ነጻ ለማድረግ፣ ለሰዎች መልካም ነገርን ለማሰብ እኛም ደስተኛ እና ጤነኛ ለመሆን ሰላማዊ መሆን አለብን፡፡ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ለሮሜ ምእመናን በላከው መልእክቱ እንዲህ ይመክረናል፤ ‹‹…ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ…፡፡›› (ሮሜ ፲፪፥፲፰) ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ለመኖር እኛ የሰላም ሰዎች ነገሮችን በትዕግሥት የምናልፍ፣ ለሰዎች መልካም የምናስብ ልንሆን ይገባል፡፡
‹‹እነርሱ በእምነት የእሳት ኀይልን አጠፉ›› (ዕብራውያን ፲፩፥፩)
ለብዙዎቻችን እሳትን የሚያጠፋው ውኃ ብቻ ይመስለናል፡፡ ለእግዚአብሔር የታመኑ ቅዱሳን ሰማዕታት የእሳትን ኃይል በትዕግሥታቸው እንዳጠፉትና ጸሎታቸውም ለእኛ በአማላጅነታቸው ለምንታመን ምእመናን ሁልጊዜም እንደሚያስፈልገን ፈልፈለ ማኅሌት የቤተ ክርስቲያናችን ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ምስክር ሆኖ ያስተምረናል፤ አጥፍኡ ኃይለ እሳት በትዕግሥቶሙ፤ ይብጽሐነ ወትረ ጸሎቶሙ፤በትዕግሥታቸው የእሳትን ኃይል አጠፉ፤ ጸሎታቸው ዘወትር ይድረሰን” እንዲል፤ (ድጓ ዘታኅሣሥ ፪)
አማናዊ ብርሃን
እውነተኛው ብርሃን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰዎችን ከገቡበት የኃጢአት ባርነትና የጨለማ ዓለም ለማውጣት ወደዚህች ምድር እንደመጣ፣ መከራን ተቀብሎ፣ በመስቀል ተስቅሎ፣ ሞቶ፣ ተነሥቶ ነጻ እንዳወጣን ቅዱሳኑ ነቢያት ሰብከዋል፡፡ ምሥጢረ ሥጋዌውን ነገረ ድኅነትን በሚገባ አስተምረዋል፡፡
ተስፋ መቁረጥ የኅሊና ሞት!
አበው ኅሊናን ‹‹እግዚአብሔር በሰው ልጅ ውስጥ ያስቀመጠው እውነተኛ ዳኛ ነው›› በማለትም ይገልጡታል፡፡ ዛሬ በዚህ መልእክታችን ማስገንዘብ የፈለግነው ስለ ኅሊና ምንነት በጥልቀት መመልከት ሳይሆን ተስፋ መቁረጥ ስለሚያመጣብን የኅሊና ሞት ነው፡፡
የፍቅር ምርኮዎች
ፍጹም በሆነ ልዩ የልብ ስሜትና ኃይል ከራስ በላይ ለሌላ የሚኖር ደስ የሚያሰኝ መንፈስ፣ በሥቃይ ውስጥ የሚገኝ፣ እጅግ አስደናቂ ተፈጥሮ “ፍቅር ነው!” ፍቅር ሁለመናውን ይሰጣል፤ እንደራሱ ይወዳል፤ ለወደደው ያስባል፤ ይንገላታል፤ ይሠቃያል፤ ይሞታል፡፡
በአታ ለእግዝእትነ ውስተ ቤተ መቅደስ
ከደጋጎቹ ቅዱሳን አባቷና እናቷ ኢያቄምና ሐና የተወለደችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ቀን የከበረ ነው፡፡ በበጎ ምክር በእግዚአብሐርም ፈቃድ ይህ ሆነ፤ በዚያን ጊዜ ኢያቄምና ሐና “….ሆዷ ዘመድ ሳይወድ አፏ እህል ሳይለምድ ወስደን እንስጥ” ብለው በመማከር መባዕም ጨምረው ወደ ቤተ መቅደስ ሄዱ፡፡
ተዝካረ ልደቱ ለኤልያስ ነቢይ
ቅዱሳት መጻሕፍት ነቢዩ ኤልያስ የተወለደው በታኅሣሥ ፩ ቀን ከነገደ ሌዊ እንደሆነ ይገልጻሉ፤ የአባቱ ስም ኢያስንዩ የእናቱ ስም ቶና ይባላሉ፡፡ በተቀደሰች የልደት ቀኑም አባቱ ብርሃን የለበሱ አራት ሰዎች ሲሰግዱለትና ሕፃናት በሚጠቀልሉበት ጨርቅ ፈንታ በእሳት ሲጠቅልሉት ተመልክቷል፡፡
ሥዕለ አድኅኖ
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁ? እንኳን ለጾመ ነቢያት (የገና ጾም) አደረሳችሁ! ይህ ጾም የሚጾመው አባቶቻችንን ነቢያት እግዚአብሔር በሰጠን ተስፋ በገባልን ቃል ኪዳን መሠረት ከሰማያት ወርዶ እንዲያድነን “አቤቱ ውረድ፤ ተወለድ፤ አድነን” እያሉ የጾሙት ጾም ነው፤ እኛ ደግሞ ከሰማያት ወርዶ፣ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ አድኖናል እያልን ውለታውን እያስታወስን እንጾመዋለን፡፡ ከሰባቱ የዐዋጅ አጽዋማት አንዱ ስለሆነ እኛም እንደ አቅማችን ልንጾመው ይገባል! መልካም!
ትምህርታችሁንም በርትታችሁ ተማሩ! የመንፈቀ ዓመቱ ፈተናም እየተቃረበ ነው፤ በደንብ በማጥናት ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ አለባችሁ! በሰንበት ቤተ ክርስቲያን በመሄድ መማርን፣ማገልገልንም እንዳትረሱ።
ባለፈው ትምህርታችን ስለ ሥዕለ አድኅኖ በተማርነው ትምህርት ሥዕለ አድኅኖ እንዴት መሣል እንዳለበት በመጠኑ ተምረናል፡፡ ዛሬ ደግሞ ሥዕለ አድኅኖ ሲሣል የምንጠቀማቸው ቀለማት (ከለር) ምን ዓይነት መሆን እንዳበቸውና ምክንያቱን የተወሰኑትን ለአብነት እንመለከታለን፡፡
ትሩፋን
ቅዱሱ መጽሐፍ ትሩፋን ከጦርነት፣ ከስደት፣ ከምርኮ የተረፉትን ሰዎች እንደሚያመልክት ይነግረናል፡፡ “ትሩፍ” ጥሬ ቃሉ “የቀረ፣ የተረፈ፣ ቀሪ፣ ትርፍ” የሚል ትርጓሜ አለው፡፡ (መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፣ ገጽ ፱፻፫) ናቡከደነፆር እስራኤልን ወደ ባቢሎን ማርኮ ከወሰዳቸው ከሰባ ዘመን በኋላ በባቢሎን የቀሩት ከተማረኩት ሽማግሎች ትሩፋን ይባላሉ። በንጉሡ ዘመነ መንግሥት ከኢየሩሳሌም ተማርከው ሰባ ዘመን በፋርስ በባቢሎን የሚኖሩ የእስራኤል ሕዝብ ትሩፋነ ባቢሎን እንደሆኑም መጽሐፍ ያስረዳናል። (ዕዝራ ፪፥፩)
የቤተ ክርስቲያን መሪ ዕቅድ
ውድ አንባብያን! እንደምን ከረማችሁ? አሜን! የአምላካችን የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን! ከወራት በፊት ‹‹የቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ካርታ›› በሚል ርእስ የተወሰኑ ጉዳዮችን በተከታታይ አቅርበንላችሁ ነበር፡፡ ዛሬም ከቤተ ክርስቲያናችን አዲሱ የዐሥር ዓመት መሪ ዕቅድ ከዚያው ጋር የተገናኘ ሐሳብ አቅርበንላችኋል፡፡