• እንኳን በደኅና መጡ !

ዜናዎች፣ ወቅታዊ ክንውኖች እና ልዩ ልዩ ይዘቶች

‹‹ታመመ፤ ሞተ፤ ተቀበረ፤ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ›› (የዘወትር ጸሎት)

ጌታ ሰው በመሆኑ የሰውን ልጅ ከኃጢአት፣ ከሞት እና ከሰይጣን ባርነት ነጻ አወጣው። እነዚህ ድል የተነሡትም ፍጹም እስከ መስቀል ሞት በደረሰ መታዘዝ፣ ቅዱስ በሆነ ሕማሙ፣ አዳኝ በሆነ ሞቱና፣ በትንሣኤው ኃይል ነበር።

‹‹እባክህ አሁን አድነን!››

ግሩም አምላክ በትሕትና ከተገለጠባቸው ዕለታት አንዱ የሆነው ድንቅ ቀን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ‹‹ሆሣዕና›› በመባል ይታወቃል፡፡ ሆሣዕና መተርጉማነ አበው በአንድምታቸው ‹‹ ሆሣዕና በአርያም በሰማይ ያለ መድኃኒት›› ብለው ተርጉመውልናል፤

‹‹ነገን ዛሬ እንሥራ››

ተወዳጆች እንደምን ሰነበታችሁ? በዚህ ርእስ ባለፉት ተከታታይ አራት ክፍሎች ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ክብረ ክህነት ጽሑፎችን አቅርበንላችኋል፡፡ በዚህም “ክብረ ክህነት ትናንት እንዴት ነበር? ዛሬስ ምን ሁኔታ ላይ ነው?” የሚሉ ጉዳዮችን በጥቂቱ ለማየት ሞክረናል፡፡ በዚህ በክፍል አምስት ደግሞ የነገዋን ቤተ ክርስቲያን የተሻለች ለማድረግ “ክብረ ክህነት ነገ ምን መሆን አለበት” የሚለውን ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡

ምሥጢረ ሥላሴ

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁልን? የዐቢይ ጾምን ከጀመርን እነሆ ሰባተኛው ሳምንት ደረስን! በፍቅር አስጀምሮና አበርትቶ ለዚህ ያደረሰን እግዚአብሔር ይመስገን!… ልጆች!ባለፈው “ሥነ ፍጥረት” በሚል ርእስ ተምረን ነበር፤ ዛሬ ደግሞ ምሥጢረ ሥላሴን ስለምንማር ተከታተሉን!

መጽሔተ ተልእኮ ዘማኅበረ ቅዱሳን

መጽሔተ ተልእኮ ዘማኅበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃና መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ሕዝብ ግንኙነትና ትብብር አገልግሎት ማስተባበሪያ የተዘጋጀ ነው፡፡ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መጽሔቱን ያንብቡ!

መምህር ሆይ!

መሆንህን አውቆ እውነተኛ
ገሰገሰ ወዳንተ በሌሊት ሳይተኛ
ቅዱስ ቃልህንም ሲሰማ ፈወሰው
የታወረ ኅሊናውን አብርቶ አቀናው
ጥያቄውን እንዲያቀርብ አበረታታኸው
ስለ ዳግም ውልደትም አስተማርከው

መልካም አገልግሎት

መንፈሳዊ ሕይወት ከሚገለጽበት ዋነኛና ተቀዳሚ ተግባራት ከሆኑት መካከል መልካም አገልግሎት አንዱ ነው፡፡ አገልግሎትን መልካም የሚያደርገውን ተግዳሮቶቹን ለይቶ ማወቅ ደግሞ ከማንኛውም መንፈሳዊ አገልጋይ ይጠበቃል፡፡ ይህም የእምነታችን፣ የሃይማኖታችን፣ የመንፈሳዊ ዕውቀታችንና ክርስቲያናዊ ተግባራችን መለኪያ ነው፡፡

‹‹ጌታውን ያስደሰተው አገልጋይ ታማኝና ቸር አገልጋይ ነው›› ቅዱስ ያሬድ

ከማንም አስቀድሞ አገልግሎት ለአምላካችን እግዚአብሔር ይገባል፤ በጥንተ ተፈጥሮ በመጀመሪያው ቀን የተፈጠሩት መላእክት ፈጣሪያቸውን ዘወትር ያለማቋረጥ ‹‹ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ›› እያሉ እንደሚያመሰግኑት ሊቁ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በመጽሐፈ አክሲማሮስ ገልጾልናል፡፡በዕለተ ዓርብ ሰው ሲፈጠር እንደ መላእክቱ የፈጠረውን ጌታውን እንዲያመሰግን፣ እንዲያገለግል እንዲሁም ስሙን እንዲቀድስና ክቡርን እንዲወርስ በመሆኑም የቀደመ ሰው አዳምም አምላኩን እያመሰገነና በገነትም በጸሎት እየተጋ ኖሯል፡፡

‹‹ነገን ዛሬ እንሥራ››

ክህነት በዘመናችን በብዙ ተግዳሮቶች ውስጥ ያለ፣ ልዩ ትኩረትን የሚሻ ዐቢይ ጉዳይ ነው፡፡ ያልተማሩ ከድንቁርናቸው፣ ሥርዓት አልበኞቹም ከክፉ መንገዳቸው እንዲላቀቁ፣ በቆሬ መንገድ የቆሙ ከመንገዳቸው እንዲመለሱ የሚያደርግም ኃይል ነው፡፡

ሥነ ፍጥረት

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁልን? ዐቢይ ጾምን እንዴት እያሳለፋችሁ ነው? ባለፈው ትምህርታችን ዕድሜው ከሰባት ዓመት በላይ የሆነ ማንኛውም ክርስቲያን ጾምን መጾም እንዳለበት በተማርነው መሠረት እንደ ዓቅማችሁ እየጾማችሁ እንደሆነ ተስፋችን እሙን ነው! መልካም! አሁን ለዛሬ ወዳዘጋጀንላችሁ ትምህርት እናምራ፡፡ ባለፈው “የእግዚአብሔር ባሕርያት” በሚል ርእስ ተምረን ነበር፤ ዛሬ ደግሞ እግዚአብሔር ስለፈጠራቸው ፍጥረታት እንማራለን!

በፌስቡክ የትስስር ገጽ ያግኙን

ስለ ማኅበረ ቅዱሳን መሰረታዊ መረጃዎች

ስያሜ

ማኅበረ ቅዱሳን እግዚአብሔር ያከበራቸው የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት በአጠቃላይ የቅዱሳን ገድል፣ ትሩፋትና አማላጅነት የሚዘከርበት በመሆኑ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን›› የሚል ስያሜውን አግኝቷል፡፡

የማኅበሩ ርእይ

ቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ የመሪነት ሚናዋን ስትወጣ ማየት

ተልእኮ

ለቤተ ክርስቲያን ተልእኮ መሳካት እና ለሕልውናዋ የሚተጋ፣ የተደራጀ ፣ ምሉዕ ኦርቶዶክሳዊ፤ ርቱዕ ዘመናዊ፤ ሁለገብ መሪ ትውልድ ማፍራት እና ማሰማራት

እሴቶች

  • መንፈሳዊነት

    ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
  • አገልጋይነት

    የማኅበሩ አባላት አገልግሎትን የክርስቲያናዊ ሕይወታቸው መገለጫ አድርገው በመቀበል በበጎ ፈቃድ ሰማያዊውን ክብርና ጸጋ በመሻት፣ ምድራዊ ክብርና ውዳሴ ከንቱን ሳይፈልጉ፣ በትሕትና እና በክርስቲያናዊ ፍቅር በታማኝነት ያገለግላሉ::
  • የሐሳብ መሪነት

    ማኅበሩ ለቤተ ክርስቲያን ዘላቂ አገልግሎት የሚያስፈልጉ፣ ኦርቶዶክሳዊ እሳቤን የተከተሉና ዘመኑን የዋጁ የመሪነት ሐሳቦችን በማፍለቅ ከሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ጋር በመመካከር ይሠራል::
  • ተባባሪነት

    ማኅበሩ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሁሉም የቤተ ክርስትያን አካላት የወል ተግባር ነው ብሎ ያምናል:: በመሆኑም እንደየጉዳዩ አግባብነት ካላቸው ባለ ድርሻ እና አጋር አካላት ጋር በመግባባት፣ በመመካከር እና በቅንነት ለተልእኮ አንድነት ብዝኃ ጸጋን በማክበር አብሮ ይሠራል::
  • ሙያ አክባሪነት

    የማኅበሩ አባላት ባላቸው ልዩ ልዩ ሙያ /ዕውቀት/ ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል የተሰባሰቡ በመሆናቸው፣ በማኅበሩ አሠራሮች ሁሉ ከኦርቶዶክሳዊው ትምህርተ ሃይማኖት ጋር በማይጋጩ በእውነተኛ መረጃ ለሚደገፉ ሙያዊ ምክረ ሐሳቦች ተገቢውን ክብርና ቅድሚያ ይሰጣል:: በቤተ ክርስቲያንም ለመንፈሳዊ እና ለዘመናዊው (አስኳላ) ሙያ ተገቢው ክብር እንዲሰጥ ይሠራል::
  • ምክንያታዊ ሞጋችነት

    ማኅበሩ በእውነተኛ መረጃ ላይ ተመሥርቶ ቤተ ክርስቲያንን ከውስጥም ሆነ ከውጭ የሚፈትኑ አስተሳሰቦችን፣ አሠራሮችን፣ ልማዶችን እና ትርክቶችን በግልጽና በመንፈሳዊ ጥብዓት እና በእውነት እንዲሞገቱና መፍትሔ ላይ እንዲደረስ ይሠራል::
  • ተጠያቂነት

    የማኅበሩ አገልግሎት ግብ ሰማያዊ ዋጋ ማግኘት ስለሆነ ኀላፊነትን በአግባቡ አለመወጣት በእግዚአብሔር እና በሰዎች ዘንድ የሚያስጠይቅ በመሆኑ በየትኛውም እርከን ላይ ያለ አባል እና አመራር በማኅበሩ አሠራር መሠረት በተሰጠው ኀላፊነት ተጠያቂ ይሆናል፡፡

ዓላማዎች

  • የቤተ ክርስቲያን ተቋማዊ አስተዳደር፣ የአሠራር ሥርዐትና አስተሳሰብ፣ በቴክኖሎጂ እና በልዩ ልዩ መንገዶች በመደገፍ ዘመኑን ለዋጀ ጠንካራ አገልግሎት ማብቃት፤
  • የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ሙሉ ሰብእናን የሚገነባ ሥርዐተ ትምህርት በማስተማር ዘመኑን የዋጁ ምሉዕ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር የሚያገለግሉ እንዲሁም በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ በፖለቲካዊ እና በሀገር አስተዳደር ጉዳዮች መሪ/ንቁ ተሳታፊ አገልጋዮችን ማፍራት እና ማሠማራት፤
  • የተተኪውን ትውልድ ምንጭ ለማጎልበት የሰ/ት/ቤቶችን አቅም በማጠናከር የሕጻናት እና የወጣቶችን የተተኪነት ሚና ማሳደግ፤
  • ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነትን በተግባር የሚገልጽ ቤተሰብ እና አንድነቱን የጠበቀ ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰብ በመገንባት የተደራጀ እና የተናበበ አገልግሎት መስጠት፤
  • በተደራጀ እና ተደራሹን ማእከል ባደረገ መንገድ ስብከተ ወንጌልንና ሐዋርያዊ ተልእኮን ዘርፈ ብዙ በሆኑ መንገዶች በመላው ዓለም ማስፋፋት፤
  • በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚነዙትን የርእዮተ ዓለም፣ የሐሰት ትርክቶች እና የአጽራረ ቤተ ክርስቲያንን እንቅስቃሴ ጥናት እና ምርምር ላይ ተመርኩዞ መሞገት እና የተሳሳቱትን በማረም፣ በጠንካራ የዕቅበተ እምነት አገልግሎት የቤተ ክርስቲያንን ሕልውና ማስጠበቅ፤
  • በተመረጡ ገዳማት እና አብነት ትምህርት ቤቶች የልኅቀት ማእከል እና የተለየ ክርስቲያናዊ ተልእኮ የሚፈጽሙ እንዲሆኑ የሚያስችል ሁለገብ የአእምሮ ልማት ድጋፍ ማድረግ፤
  • ማኅበሩ ዘመኑን የዋጀ ተቋማዊ የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት ተልእኮውን ማሳካት የሚችልበት አቅም መፍጥር ( በአመራር፣ በሰው ኃይል፣ በመንፈሳዊነት፣ በግንኙነት፣ በዕውቀት፣በልማት፣ በፋይናንስ፣ በቴክኖሎጂ)፤
  • ዓለም አቀፍ ግንኙነትና የትብብር አገልግሎትን መርሕ ያደረገ የኦርቶዶክሳውያን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎ ማሳደግ፣

አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ
የሸዋ ሊቀ ጳጳስ ፲፱፻፴፪-፲፱፻፹፪ዓ.ም.

የማኅበሩ ህንጻ