• እንኳን በደኅና መጡ !

ቅዱስ ቂርቆስ ወቅድስት ኢየሉጣ

                                                             በቀሲስ ኃይለ ሚካኤል ብርሃኑ      በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ አምልኮ ሐምሌ ፲፱ ቀን የሚከበረው ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ቅድስት ኢየሉጣን እና ልጁዋን ቅዱስ ቂርቆስን ከፈላ ውኃ የታደገበት(ያዳነበት) የሚታሰብበት በዓል ነው፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ፡- ”ይትአየን መልአከ እግዚአብሔር አውዶሙ ለእለ ይፈርህዎ ወያድኅኖሙ ጣዕሙ ወታእምሩ ከመ ኄር እግዚአብሔር፤ የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል […]

ቅድስት ሥላሴ

የሁሉ ፈጣሪ የዓለም ገዢ አምላካችን እግዚአብሔር ለስሙ ክብር ይግባውና በሐምሌ ፯ ቀን ወደ ጻድቁ አብርሃም ቤት በመግባት በአንድነትና በሦስትነት ክብሩ ተገለጠለት፡፡ በዚህች በከበረችም ቀን አብርሃም በደጃፉ ሆኖ ዓይኖቹን አንሥቶ ሲመለከት ሦስት አረጋውያንን አየ፤ ሮጦ ሄዶም ተቀበላቸው፡፡ ‹‹ውኃ እናምጣላችሁ፤ እግራችሁን እንጠባችሁ፡፡ ከዛፉም ሥር ዕረፉ፤ እንጀራም እናምጣላችሁና ብሉ፤ ከዚያም በባሪያችሁ ዘንድ ከአረፋችሁ በኋላ፥ ወደ አሰባችሁት ትሄዳላችሁ›› አላቸው፡፡ ‹‹እንደምታየን ሽማግሌዎች […]

“የጻድቅ መታሰቢያ ለዘለዓለም ይኖራል”(መዝ.፻፳፮፥፮)

ሐምሌ አምስት ቀን በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከሚከበሩ በዓላት ውስጥ የክቡራን የዐበይት አባቶቻችን የቅዱስ ጴጥሮስና የቅዱስ ጳውሎስ የሰማዕትነታቸው መታሰቢያ ዕለት ነው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ አሣ አጥማጅ ነበር፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን አኢየሱስ ክርስቶስ ከመረጣቸው ፲፪ቱ ሐዋርያት መካከል አንዱ ነው፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅዱስ ጴጥሮስ በፊት ወንድሙ እንዲርያስን የጠራው ሲሆን ለሐዋርያነት ከተመረጠበት ጊዜ አንስቶ ከጌታችን እግር ሥር እየተከተለ በዋለበት […]

ማስታወቂያ

Nothing Found

Sorry, no posts matched your criteria

መልእክትዎን ይላኩልን