• እንኳን በደኅና መጡ !

በጊዜው ሁሉ ጸልዩ(ፊል.፬.፮)

ክፍል ሁለት በእንዳለ ደምስስ ጸሎት ጸለየ፣ ለመነ ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ቃል ሲሆን መለመን፣ ማመስገን፣ በንጽሕና በእግዚአብሔር ፊት መቆም፣ ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ማለት እንደሆነ ቅዱሳት መጻሕፍት ያስረዳሉ፡፡ “ጸሎትስ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር የሚናገርባት ናት” (ፍትሐ. ነገ. አንቀጽ ፲፬) እንዲል፡፡ አዳም አባታችን ተግቶ በመጸለዩ ዲያብሎስ ሊፈትነው በቀረበ ጊዜ ድል ነስቶታል፣ ሔዋን ግን ሥራ ፈትታ፣ እግሯን ዘርግታ በመቀመጧ […]

“የሰላም መንገድ” (መዝ.፲፬፥፮)

በመ/ር ኃይለ ሚካኤል ብርሃኑ ሰላም ማለት ጸጥታ፣ ዕረፍት፣ እርጋታ፣ እርካታ ማለት ሲሆን የእርስ በእርስ ስምምነት፣ በአንድነት አብሮ መኖር፣ መቻልና የዕረፍት ስሜት እንደሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ያስረዳል፡፡ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ክፉዎች የሰላምን መንገድ የማያውቁ መሆናቸውን “ደምን ለማፍሰስ እግራቸው ፈጣን ነው፣ ጥፋትና ጉስቁልና በመንገዳቸው አለ፣ የሰላምን መንገድ አላወቁአትምና እግዚአብሔርን መፍራት በዓይናቸው ፊት የለም” (መዝ.፲፬፥፮) ሲል […]

“የጽድቅንም ጥሩር ልበሱ”/ኤፌ.፮.፲፬/

ክፍል አንድ በእንዳለ ደምስስ መንፈሳዊ ሰው ርስት መንግሥተ ሰማያትን ይወርስ ዘንድ፣ ራስን ለእግዚአብሔር ማስገዛት፣ ትእዛዙንም መፈጸም ይጠበቅበታል፡፡ ከኃጢአት ወደ ጽድቅ ለመሸጋገርም አንድ ክርስቲያን መንፈሳዊ የተጋድሎ መሣሪያዎችን ይዞ መገኘት ይገባዋል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን ክርስቲያኖች በጻፈው መልእክቱ “እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ታጥቃችሁ ቁሙ፣ የጽድቅንም ጥሩር ልበሱ” እንዲል/ኤፌ.፮.፲፬/፡፡ ሃይማኖትን፣ መልካም ምግባርን፣ ፍቅርን፣ የንስሓ ሕይወትን፣ ወዘተ የያዘ ሰው ራሱን […]

ማስታወቂያ

Nothing Found

Sorry, no posts matched your criteria

መልእክትዎን ይላኩልን