• እንኳን በደኅና መጡ !

“ባሕር አየች፣ ሸሸችም” (መዝ. ፻፲፫፥፫)

በዲ/ን አሻግሬ አምጤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከገሊላ ተነሥቶ ወደ ዮርዳኖስ ሄዶ፣ በዮሐንስ እጅ በተጠመቀ ጊዜ ባሕር ሸሸች፣ ዮረዳስም ወደ ኋላ ተመልሷል፡፡ ጌታችን ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ የወረደው በጥምቀቱ ክብር ሊያገኝበት፣ የጎደለው ነገር ኖሮ ሊመላበት ሳይሆን እኛም ከውኃ እና ከመንፈስ ቅዱስ ተወልደን ልጅነትን እንድናገኝ፣ በኃጢአት ምክንያት ጎድሎብን የነበረው እንዲሞላልን፣ አጥተነው የነበረው ልጅነት እንዲመለስልን ነው፡፡ ሊቁ ቅዱስ […]

ጾመ ጋድ(ገሃድ)

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ካሏት ሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት መካከል አንዱ ጾመ ጋድ(ገሃድ) ነው፡፡ ገሃድ ማለት ለውጥ(ምትክ) ወይም ልዋጭ፤ እንዲሁም ግልጥ፣ ተገላጭ በማለት ይተረጎማል፡፡ ይህንንም ደስታ ተክለ ወልድ በመዝገበ ቃላት መጽሐፋቸው ጋድ(ገሃድ) እንዲህ ይተረጉሙታል፡- “ገና፣ የጥምቀት ከተራ (የልደትና የጥምቀት ዋዜማ) እንደ ዐርብ ረቡዕ እና ፍልሰታ፣ እንደ ሑዳዴ የሚጾም፡፡ ትርጓሜው የሚገለጥ፣ ተገላጭ፣ ግልጥ ማለት ነው፡፡ ጌታችን እንደ ሰውነቱ […]

በዓለ ግዝረት

እግዚአብሔር የግዝረት ሥርዓትን ለአበ ብዙኀን አብርሃም የሰጠው የቃል ኪዳን ምልክት ነው። እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፡- “አንተ ደግሞ ቃል ኪዳኔን ትጠብቃለህ፤ አንተ፣ ከአንተም በኋላ ዘርህ በትውልዳቸው፡፡ በእኔና በአንተ መካከል፣ ከአንተም በኋላ በዘርህ መካከል የምትጠብቋት ቃል ኪዳኔ ይህች ናት፤ ከእናንተ ወንድ ሁሉ ይገረዝ፡፡ የሰውነታችሁን ቊልፈት ትገረዛላችሁ፤ በእኔና በእናንተ መካከል ላለውም ቃል ኪዳን ምልክት ይሆናል” በማለት ቃል ኪዳንን አኖረ፡፡ […]

ማስታወቂያ

Nothing Found

Sorry, no posts matched your criteria

መልእክትዎን ይላኩልን