• እንኳን በደኅና መጡ !

“ለግቢ ጉባኤ ትምህርቴ የመደበኛው ትምህርቴን ያህል ትኩረት ስሰጠው ነበር፡፡” (ዲ/ን ፕ/ር እንግዳ አበበ)

ክፍል አንድ                                              በእንዳለ ደምስስ ዲ/ን ፕ/ር እንግዳ አበበ በ፲፱፻፹፯ ዓ.ም ከኮልፌ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ፲፪ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ፬ ነጥብ በማምጣት በ፲፱፻፹፰-፲፱፻፺፬ ዓ.ም በጅማ ዩኒቨርስቲ የሕክምና ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡ በሰባት ዓመታት የሕክምና ትምህርት ቆይታቸው ከትምህርት ክፍሉ እና ከአጠቃላይ የዩኒቨርሲቲው ተመራቂዎች በከፍተኛ ማዕረግ የሜዳልያ ተሸላሚ በመሆን […]

“ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ፣ ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኵሉ” (ድጓ ዘአስተርእዮ ማርያም)

በእንዳለ ደምስስ አስተርእዮ ቃሉ አስተርአየ፤ ታየ፣ ተገለጠ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ቃል ሲሆን መታየት፣ መገለጥ ማለት ነው። ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ፣ ከነፍሷ ነፍስን ነሥቶ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማሕፀኗ አድሮ የተወለደበት (በሥጋ የተገለጠበት)፣ አንድነት፣ ሦስትነቱም የተገለጠበት ወቅት በመሆኑ ከልደት በዓል እስከ ጥር መጨረሻ ዘመነ አስተርእዮ በመባል ይታወቃል። የእመቤታችን ቅድስት […]

ቃና ዘገሊላ

እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ በጥምቀት በዓል ማግስት ጥር ፲፪ ቀን የቃና ዘገሊላ በዓል ይከበራል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቃና ዘገሊላ በተደረገ ሠርግ ቤት ያደረገውን ተአምር በማሰብ በዓልን ታደርጋለች፡፡ በዓሉ ቃና ዘገሊላ የሚል ስያሜ ያገኘው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከገሊላ ክፍል ቃና በተባለችው ቦታ በፈፀመው ተአምር መነሻነት ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቃና […]

ማስታወቂያ

Nothing Found

Sorry, no posts matched your criteria

መልእክትዎን ይላኩልን