• እንኳን በደኅና መጡ !

ማኅበረ ቅዱሳን የድጋፍ ማሰባሰቢያ የዕጣ ትኬት ማዘጋጀቱ ተገለጸ

ማኅበረ ቅዱሳን የተቋማዊ ለውጥ ትግበራን ተግባራዊ በማድረግ አገልግሎቱን እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን ይህን ተከትሎ በተከለሰው የግቢ ጉባኤያት ሥርዓተ ትምህርት መሠረት በግቢ ጉባኤያት (በዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች) ለሚማሩ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች በሃይማኖት እና በሥነ ምግባር አንጾ ለማውጣት ለሚተገብራቸው የመምህራን ማፍራት፣ የመመማሪያ መጻሕፍት ዝግጅት፣ እንዲሁም የቨርቹዋል ሥልጠና ማእከል ማቋቋሚያ የሚውል የድጋፍ ማሰባበሰቢያ የዕጣ ትኬት አዘጋጅቷል፡፡ የዕጣ ትኬቱንም ከሐምሌ 01 ቀን […]

በደረጃ ሁለት ተተኪ አመራርነት ሥልጠና የወሰዱ ሠልጣኞች ተመረቁ

በማኅበረ ቅዱሳን የደቡብ ማእከላት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙና ከተለያዩ ግቢ ጉባኤያት ለተወጣጡ ፸፮ አገልጋዮች የደረጃ ሁለት ተተኪ አመራርነት ሥልጠና በመስጠት አስመረቀ፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን በሥራ አስፈጻሚነት የሚመሩትን አባላት አቅም ለመገንባትና የማኅበሩን እንዲሁም የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት በሚገባ የተረዱ፤ መንፈሳዊ ሕይወታቸውም የተስተካከለና አርአያ ሆነው ግቢ ጉባኤን ሊመሩ የሚችሉ የአመራር አባላትን ለማፍራት ታስቦ በክረምት ወቅት በተለያዩ […]

የተተኪ አመራርና መምህራን ሥልጠና በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ

ማኅበረ ቅዱሳን በስድስት ማስተባበሪያዎችና በዐሥራ አንድ ሥልጠና ማእከላት የደረጃ ሁለት ተተኪ አመራርና መምህራን ሥልጠና በመስጠት ላይ እንደሚገኝ በማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ማስተባበሪያ የተቋማዊ ልማት አገልግሎት ዋና ክፍል አስተባባሪ ሓጋዚ አብርሃ ገለጹ፡፡ የደረጃ ሁለት ተተኪ አመራርነት ሥልጠናው በመሐል ማእከላት፡- በአዲስ አበባ፣ በአዳማ (በአፋን ኦሮሞ) ፤ በደቡብ ማስተባበሪያ፡- በወላታና ሐዋሳ፤ በምሥራቅ ማስተባበሪያ፡- ድሬዳዋ፤ በሰሜን ምሥራቅ ማስተባበሪያ፡- […]

ማስታወቂያ

Nothing Found

Sorry, no posts matched your criteria

መልእክትዎን ይላኩልን