• እንኳን በደኅና መጡ !

“ለንስሓ የሚገባ ፍሬ አድርጉ።” (ማቴ. ፫፥፰)

በደሳለኝ ብርሃኑ ክፍል አንድ ንስሓ “ነስሐ” ከሚለው የግዕዝ ግሥ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ማዘን፣ መጸጸት፣ የኖርኩበት የኃጢአት ሕይወት ይበቃኛል ማለት፣ በደለኛነትን አምኖ ኃጢአትን ለካህን መናዘዝ ማለት ነው። ንስሓ እግዚአብሔርን መፈለግ ነው። ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት “ለይትፌሣሕ ልብ ዘየኀሦ ለእግዚአብሔር፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው” (መዝ. ፻፭፥፫) በማለት እንደተናገረው። ቅዱስ ዳዊት በዚህ ብቻ አያበቃም የአምላኩን ገጸ ምሕረት […]

“ታማኝአገልጋይማነው?” (ማቴ. ፳፬፥፵፭)

በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት የዐቢይ ጾም ስድስተኛው ሳምንት ገብር ኄር ይባላል፡፡ ሰያሜውንም የሰጠው ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ነው፡፡ ከአምስቱ መጻሕፍቶቹ አንዱ በሆነው ጾመ ድጓ በተባለው መጽሐፍ የዐቢይ ጾም ሳምንታት ስያሜዎች ከነሥርዓተ ማኅሌቱ አዘጋጅቷል፡፡ በዚህም መሠረት በስድስተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ከዋዜማው ቅዳሜ ጀምሮ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሚዘመረው ዝማሬ፣ የሚሰበከው ስብከት፣ የሚሰጠው ትምህርት ገብር ኄር ወይም […]

ደብረ ዘይት (የዐቢይ ጾም አምስተኛ ሳምንት)

ደብረ ዘይት የቃሉን ፍቺ ስንመለከት “ደብር” ተራራ ማለት ሲሆን “ዘይት” የሚለው ቃል ደግሞ ወይራ ማለት ነው። ስለዚህ ደብረ ዘይት በወይራ ዛፍ የተሸፈነ ተራራ ማለት ነው።  ይህ የደብረ ዘይት ተራራ ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ በደብረ ቄድሮን ሸለቆ ብቻ አለ። ከታች ጌቴ ሴማኒ የተባለው የአትክልት ስፍራ ሲገኝ የጸሎተ ሐሙስ ማታ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተያዘበትና በኋላም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ሥጋዋ ረፈበት በዚህ ተራራ […]

ማስታወቂያ

Nothing Found

Sorry, no posts matched your criteria

መልእክትዎን ይላኩልን