• እንኳን በደኅና መጡ !

ጾመ ፍልሰታ ለማርያም

እንኳን ለፍልሰታ ለማርያም ጾም በሰላም አደረሳችሁ! ጾመ ፍልሰታ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከደነገገቻቸው ሰባቱ የዐዋጅ አጽዋማት አንዱ ነው፡፡ ይህንንም ጾም ከነሐሴ ፩-፲፮ ቀን ድረስ ለሁለት ሱባኤ ከሰባት ዓመት ሕፃናት ጀምሮ ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ የሚጾሙትና በናፍቆት የሚጠበቅ ጾም ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያትን አብነት አድርጋ የምትጾመው ጾም እንደመሆኑ ምእመናን በየገዳማቱና አድባራት በመገኘት ራሳቸውን ለእግዚአብሔር በማስገዛት በሱባኤ በጾም፣ በጸሎት፣ በስግደትና […]

መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ

መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፤ በሀገራችን በኢትዮጵያና በመላው ዓለም የምትገኙ ሕዝበ ክርስቲያን በሙሉ፡- የክብር ባለቤት እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ሰባት ዓ.ም የቅድስት ድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ! ‹‹ታዓብዮ ነፍስየ ለእግዚአብሔር፤ ነፍሴ እግዚአብሔርን እጅግ ታከብረዋለች›› (ሉቃ. ፩÷፵፮)፤ ይህንን ዐረፍተ ነገር የተናገረችው ማኅደረ መንፈስ ቅዱስ የሆነችው ቅድስት ድንግል […]

“እናቴ ሆይ ገድላችን እንፈጽም ዘንድ ጨክኝ በርቺ አትጠራጠሪ”

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደም ላይ ተመሥርታለችና ዙሪያዋን በከበቧት ስፍር ቁጥር በሌላቸው ቅዱሳን መላእክት፣ ቅዱሳን ጻድቃን ሰማዕታት ተጋድሎና ጸሎት የታጠረች ናት፡፡ “እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ፤ በተራራ ላይ የተሠራች ከተማ መሰወር አይቻላትም” (ማቴ. ፭፥፲፬) እንዲል መጽሐፍ ቅዱስ ቅዱሳንን በብርሃን ይመስላቸዋል፤ ቅዱሳን ወንጌልን በመስበክ ዓለምን አጣፍጠዋታልና፡፡ ቤተ ክርስቲያን ለእነዚህ ዓለምን ድል ለነሱ ቅዱሳን ከዓመት […]

ማስታወቂያ

Nothing Found

Sorry, no posts matched your criteria

መልእክትዎን ይላኩልን