• እንኳን በደኅና መጡ !

በለቅሶ የሚዘሩ በደስታ ይሰበስባሉ (መዝ.፩፻፳፭:፭)

በመምህር ፍቃዱ ሳህሌ ክፍል አንድ                                       ይህ የቅዱስ ደዊት መዝሙር የመዓርግ መዝሙሮች ከሚባሉት መካከል የሚመደብ ነው፡፡ እስራኤላውያን በእግረ ሥጋ ወደ ኢየሩሳሌም፣ በእግረ ሕሊና/ነፍስ/ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር ሲወጡ ይዘምሯቸው ስለነበር ይህን ስያሜ አግኝተዋል፡፡ “አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ” ተብሎ በቅዱስ መጽሐፍ እንደተገለጠው በዚህ ኃይለ ቃል ውስጥ የምናገኛቸው ቁም ነገሮች እግዚአብሔር በምናውቀውና በምንረዳው በዕለት ተዕለት ተግባራቸው ምሳሌነት ገልጦልናል፡፡ ዛሬም […]

‘‘እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ ትእዛዜ ይህች ናት’’(ማቴ. ፲፭፥፲፪)

በመ/ር ኃይለ ሚካኤል ብርሃኑ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ የወይን ሐረግ ስለመሆኑና አምነው የተከተሉት ሁሉ ደግሞ ቅርንጫፎች እንደሆኑ በብዙ ምሳሌ ካስረዳ በኋላ ከላይ በርዕስ የተነሣንበትን ቃል ተናግሯል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን ቃል በቃል ስንመለከተው “እኔ እንደወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ የእኔ ትእዛዜ ይህች ናት፣ ስለ ወዳጆቹ ሕይወቱን አሳልፎ የሚሰጥ ሰው ያለ እንደሆነ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም፤ እናንተስ […]

“አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦትም” (መዝ. ፻፴፩፥፰)

በመምህር ሳሙኤል ተስፋዬ እግዚአብሔር አምላካችን አምስት ሺሕ አምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም “ከልጅ ልጅህ ተወልጄ ስደትህን በስደቴ፣ ሞትህን በሞቴ አጥፍቼ፤ የቀደመ ክብርህን መልሼ ያጣኸውን ርስት፣ ገነትን (መንግሥተ ሰማያትን) አወርስለሁ” በማለት ለአባታችን አዳም የገባው ቃል ኪዳን ፍጻሜው በደረሰ ጊዜ ለእግዚአብሔር ወልድ ማደሪያነት የተመረጠች፣ ለአዳም እና ለዘሩ መዳን ምክንያት የኾነች “የልጅ ልጅ” የተባለችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች፡፡ ፲፭ ዓመት ሲኾናት በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት የእግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ማደሪያ ኾነች (ገላ. ፬፥፬)፡፡ ልጇን በወለደች ወቅት “የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት አለ?”  የሚለውን የሰብአ ሰገልን ዜና […]

ማስታወቂያ

Nothing Found

Sorry, no posts matched your criteria

መልእክትዎን ይላኩልን