የማኅበረ ቅዱሳን አመሠራረት
ስለ ማኅበረ ቅዱሳን አመሠራረት ስናነሣ ዘመኑ የኮምዩኒዝም ርዕዮተ ዓለምና አስተሳሰብ የሰፈነበት፤ ስመ እግዚአብሔርን መጥራት አስቸጋሪ የሆነበትና ወደ ቤተ እግዚአብሔር መሔድ እንደ ኋላ ቀርነት የሚቆጠርበት ዘመን ነበር ፲፱፻፸፯ ዓ.ም፡፡ በተለይም በየከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በሚገኙ ተማሪዎች ዘንድ ቃለ እግዚአብሔርን በግልጽ መነጋገርም ሆነ መስማት የማይታሰብበት ወቅት ነበር፡፡ ቀደም ባሉት ጊዜያት በተለይም በንጉሠ ነገሥት ዐፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት በዩኒቨርሲቲና ኮሌጆች እንዲያስተምሩ ከምዕራባውያኑ ሀገሮች መጥተው የነበሩ ሚሲዮናውያን የኑፋቄ ትምህርታቸውን ያሠራጩ የነበረውም በእነዚሁ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ነበር፡፡ በዚህም መሠረት ያ ዘመን ትውልዱ በየአቅጣጫው በሚሲዮናውያኑ የኑፋቄ ትምህርት እንዲሁም በኮምዩኒዝም ርዕዮተ ዓለምና አስተሳሰብ እየተነጠቀ ከኦርቶዶከሳዊት ተዋሕዶ እምነት የኮበለለበት ዘመን ነበር፡፡ (ለዝርዝሩ ሊንኩን ይጫኑ)፡፡ brocher pdf final
Leave a Reply
Want to join the discussion?Feel free to contribute!