• እንኳን በደኅና መጡ !

ዜናዎች፣ ወቅታዊ ክንውኖች እና ልዩ ልዩ ይዘቶች

ነቢዩ ሳሙኤል

ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ወገን ከሆኑት ከአባቱ ሕልቅና እና ከእናቱ ሐና የተወለደው  ሳሙኤል የእግዚአብሔር ነቢይ እንደሆነ ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠቅሳሉ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስም እንዲህ ተጽፏል፤ ‹‹ሕልቅናና ሐናም ማልደው ተነሥተው ለእግዚአብሔር ሰግደው ሄዱ፤ወደ ቤታችውም ወደ አርማቴም ደረሱ፤ ሕልቅናም ሚስቱን ሐናን ዐወቃት፤ እግዚአብሔርም አሰባት፤ ፀነሰችም፡፡ የመውለጃዋም ወራት በደረሰ ጊዜ ሐና ወንድ ልጅ ወለደች፤ እርስዋም ‹‹ከሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ለምኜዋለሁ›› ስትል ስሙን ‹ሳሙኤል› ብላ ጠራችው፡፡›› (፩ኛሳሙ.፩፥፲፱-፳)

‹‹ቀድሱ ጾመ ወስብኩ ምሕላ፤ ጾምን ለዩ! ምሕላንም ዐውጁ›› (ኢዮ.፩፥፲፬)

የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተገልጦ ፍርሃትና ሥጋታቸው የተወገደላቸው ቅዱሳን ሐዋርያት ለወንጌል አገልግሎት ከመሠማራታቸው በፊትና ሕገ ወንጌልን ከማስተማራቸው አስቀድሞ አገልግሎታቸው እንዲቃና፣ መንፈስ ቅዱስ እንዳይለያቸውና የመንፈስ ቅዱስን ምሪትና ኃይል ለመቀበል ሱባኤ ያዙ፤ ሀብተ መንፈስ ቅዱስም በአገልግሎታቸው እንደሚበዛ ሲያረጋግጡ ቅዱሱን ወንጌል የሚያገለግሉበትን ክፍለ ዓለም ዕጣ በመጣጣል ዕጣው ወደ ደረሳቸው የአገልግሎት ቦታ መሰማራታቸውን የቤተ ክርስቲያን የታሪክ መዛግብትና ሊቃውንት አባቶቻችን ያስረዳሉ::

‹‹እነሆ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ›› (ሉቃ.፳፬፥፵፱)

የሰላም አምላክ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚያርግበት ጊዜ ቅዱሳን ሐዋርያትን ‹‹እነሆ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይልን እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ›› በማለት ከነገራቸው በኋላ እንዳረገ ቅዱሱ መጽሐፍ ይገልጻል፡፡ (ሉቃ.፳፬፥፵፱) በዕርገቱ ዕለትም ለሐዋርያቱ በገባላቸው ቃል መሠረት ተሰብስበው በአንድነት ሳሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዐረገ በዐሥረኛው ቀን በተነሣ በሃምሳኛው ዕለት ጧት በሦስት ሰዓት እንደ ዐውሎ ነፋስ ያለ ድምፅ ድንገት ከሰማይ መጣና የነበሩበትን ቤት ሞላው፡፡ ከዚያም እንደ እሳት የተከፋፈሉ የእሳት ላንቃዎች በሁሉም ላይ ተቀመጡባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ሁሉም መንፈስ ቅዱስን ተሞሉ፤ መንፈስ ቅዱስም ባደላቸው መጠን በየሀገሩ ቋንቋዎች ሁሉ መናገር ጀመሩ። (ሐዋ.፪፥፩-፬) ጌታችን መንፈስ ቅዱስን ለሐዋርያት የላከበት ይህ ዐቢይ ‹‹በዓል ጰራቅሊጦስ›› በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ይከበራል፡

ቅድስት አመተ ክርስቶስ

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁ? የዓመቱ የትምህርት ወቅት አልቆ የፈተና ጊዜ በመድረሱ ለመፈተን ዝግጅት ላይ የሆናችሁም ሆነ የተፈትናችሁ በጥሩ ውጤት ወደ ቀጣዩ ክፍል እንደምትዘዋወሩ መልካም ምኞታችን ነው! ልጆች! በምድረ በዳና በተራራ በዋሻና በምድር ጉድጓድ ተቅበዘበዙ››  በማለት እንደገለጸው ዓለምን ንቀው በበረሃ በተጋድሎ ሕይወት የኖሩ ብዙ አባቶችና እናቶች አሉ፡: ለዛሬ የኑሯቸውን ፍሬ ተመልክተን፣ በእምነት እንመስላቸው፣ በምግባር እንከተላቸው ዘንድ ምሳሌ ከሚሆኑን ከቅዱሳን እናቶቻችን መካከል አንዷ ስለሆነችው ስለ ቅድስት አመተ ክርስቶስ ታሪክ በጥቂቱ ልንነግራችሁ ወደድን። መልካም ንባብ!

ደቂቅ አገባብ

የተወደዳችሁ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? የእግዚአብሔር አምላካችን ስም የተመሰገነ ይሁን! ባለፈው የትምህርታችን ክፍለ ጊዜ ‹‹ዐቢይ አገባብ›› በሚል ርእስ አስተምረናችሁ ነበር፡፡ በዚህ ሳምንት ደግሞ ለሰጠናችሁ መልመጃ ምላሽና ስለ ‹‹ደቂቅ አገባብ›› እንመለከታለን፤ በጥሞና ተከታተሉን!

ዕርገት

አምላካችን እግዚአብሔር ምሉዕ በኩለሄ (ሁሉን የሞላና በሁሉም ቦታ የሚኖር) በመሆኑ በባሕርይው መውጣት መውረድ የለበትም::‹ወረደ፣ ተወለደ› ሲባል ፍጽም ሰው መሆኑን የትሕትና ሥራ መፈጸሙን ከመናገር ውጪ ከዙፋኑ ተለየ ማለት እንዳልሆነ ሁሉ ዐረገ ወጣ ሲባልም  ከሰማያዊዉ ዙፋኑ ተለይቶ ነበር ማለት አይደለም::በምድር ላይ ሊሠራ ያለውን ሁሉ መፈጸሙን ያመለክታል እንጂ::ጌታችን በዕርገቱ ምክንያት ከቤተ ክርስቲያን የተለየበት ጊዜ የለም።ነገር ግን ዕርገቱ በሥጋው የተደረገውን ዕርገቱን ያመለክታል።ይህም ዕርገት ቅዱስ ሥጋው በምድር የስበት ቁጥጥር የማይዘው ለመሆኑ አስረጅ ነዉ።አምላካዊ ሥልጣኑንም ያሳያል።

ጥንተ ስደት

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት እናቱ እመቤታችን ድንግል ማርያም፣ ከአረጋዊ ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ወደ ግብፅ የተሰደደበት ዕለት ግንቦት ፳፬ በቅድስት ቤተ ክርስተያናችን ይከበራል፡፡ ጌታችንም በአረጋዊ ዮሴፍ በትር ብዙ አስደናቂ ተአምራትን አድርጓል፡፡ ዳግመኛም እመቤታችንና የተወደደ ልጇን መድኃኒዓለምን በእጆቹ ሥራ ይመግባቸው የነበረና እነርሱንም ከኄሮድስ ለማዳን ብዙ ሰማዕትንት የተቀበለ ጻድቁና የ፹፫ ዓመቱ አረጋዊ ዮሴፍ ግብፅ የገባበትና ቅዳሴ ቤቱ የከበረበት ዕለት ነው፡፡

በዓለ ደብረ ምጥማቅ

የክርስተያን ወገን ሁሉ አምላክን የወለደች እመቤታችንም ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ በስሟ በተሠራች ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ በብርሃን መርከብ ተቀምጣ ፊቷ በግልጥ ስለመታየቱ ታላቅ በዓልን ያደርጋሉ፡፡

ቅዱሰ ኤጲፋንዮስ

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች እንዴት አላችሁ? ትምህርት እንዴት ነው? የዓመቱ የትምህርት ወቅት እየተገባደደ የፈተና ጊዜ እየደረሰ ነው፡፡ተፈትናችሁ በጥሩ ውጤት ወደ ቀጣዩ ክፍል ለመዘዋወር እየበረታችሁ ነውን? ልጆች! ‹‹የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሯችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ። የኑሯቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው›› እንደተባልነው የኑሯቸውን ፍሬ ተመልክተን በእምነት እንመስላቸው፣ በምግባር እንከተላቸው ዘንድ ምሳሌ ከሚሆኑን ከቅዱሳን አባቶቻችን አንዱ ስለሆነው ስለቅዱስ ኤጲፋንዮስ ታሪክ በጥቂቱ ልንነግራችሁ ወደድን፤ መልካም ንባብ!

በፌስቡክ የትስስር ገጽ ያግኙን

ስለ ማኅበረ ቅዱሳን መሰረታዊ መረጃዎች

ስያሜ

ማኅበረ ቅዱሳን እግዚአብሔር ያከበራቸው የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት በአጠቃላይ የቅዱሳን ገድል፣ ትሩፋትና አማላጅነት የሚዘከርበት በመሆኑ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን›› የሚል ስያሜውን አግኝቷል፡፡

የማኅበሩ ርእይ

ቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ የመሪነት ሚናዋን ስትወጣ ማየት

ተልእኮ

ለቤተ ክርስቲያን ተልእኮ መሳካት እና ለሕልውናዋ የሚተጋ፣ የተደራጀ ፣ ምሉዕ ኦርቶዶክሳዊ፤ ርቱዕ ዘመናዊ፤ ሁለገብ መሪ ትውልድ ማፍራት እና ማሰማራት

እሴቶች

  • መንፈሳዊነት

    ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
  • አገልጋይነት

    የማኅበሩ አባላት አገልግሎትን የክርስቲያናዊ ሕይወታቸው መገለጫ አድርገው በመቀበል በበጎ ፈቃድ ሰማያዊውን ክብርና ጸጋ በመሻት፣ ምድራዊ ክብርና ውዳሴ ከንቱን ሳይፈልጉ፣ በትሕትና እና በክርስቲያናዊ ፍቅር በታማኝነት ያገለግላሉ::
  • የሐሳብ መሪነት

    ማኅበሩ ለቤተ ክርስቲያን ዘላቂ አገልግሎት የሚያስፈልጉ፣ ኦርቶዶክሳዊ እሳቤን የተከተሉና ዘመኑን የዋጁ የመሪነት ሐሳቦችን በማፍለቅ ከሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ጋር በመመካከር ይሠራል::
  • ተባባሪነት

    ማኅበሩ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሁሉም የቤተ ክርስትያን አካላት የወል ተግባር ነው ብሎ ያምናል:: በመሆኑም እንደየጉዳዩ አግባብነት ካላቸው ባለ ድርሻ እና አጋር አካላት ጋር በመግባባት፣ በመመካከር እና በቅንነት ለተልእኮ አንድነት ብዝኃ ጸጋን በማክበር አብሮ ይሠራል::
  • ሙያ አክባሪነት

    የማኅበሩ አባላት ባላቸው ልዩ ልዩ ሙያ /ዕውቀት/ ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል የተሰባሰቡ በመሆናቸው፣ በማኅበሩ አሠራሮች ሁሉ ከኦርቶዶክሳዊው ትምህርተ ሃይማኖት ጋር በማይጋጩ በእውነተኛ መረጃ ለሚደገፉ ሙያዊ ምክረ ሐሳቦች ተገቢውን ክብርና ቅድሚያ ይሰጣል:: በቤተ ክርስቲያንም ለመንፈሳዊ እና ለዘመናዊው (አስኳላ) ሙያ ተገቢው ክብር እንዲሰጥ ይሠራል::
  • ምክንያታዊ ሞጋችነት

    ማኅበሩ በእውነተኛ መረጃ ላይ ተመሥርቶ ቤተ ክርስቲያንን ከውስጥም ሆነ ከውጭ የሚፈትኑ አስተሳሰቦችን፣ አሠራሮችን፣ ልማዶችን እና ትርክቶችን በግልጽና በመንፈሳዊ ጥብዓት እና በእውነት እንዲሞገቱና መፍትሔ ላይ እንዲደረስ ይሠራል::
  • ተጠያቂነት

    የማኅበሩ አገልግሎት ግብ ሰማያዊ ዋጋ ማግኘት ስለሆነ ኀላፊነትን በአግባቡ አለመወጣት በእግዚአብሔር እና በሰዎች ዘንድ የሚያስጠይቅ በመሆኑ በየትኛውም እርከን ላይ ያለ አባል እና አመራር በማኅበሩ አሠራር መሠረት በተሰጠው ኀላፊነት ተጠያቂ ይሆናል፡፡

ዓላማዎች

  • የቤተ ክርስቲያን ተቋማዊ አስተዳደር፣ የአሠራር ሥርዐትና አስተሳሰብ፣ በቴክኖሎጂ እና በልዩ ልዩ መንገዶች በመደገፍ ዘመኑን ለዋጀ ጠንካራ አገልግሎት ማብቃት፤
  • የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ሙሉ ሰብእናን የሚገነባ ሥርዐተ ትምህርት በማስተማር ዘመኑን የዋጁ ምሉዕ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር የሚያገለግሉ እንዲሁም በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ በፖለቲካዊ እና በሀገር አስተዳደር ጉዳዮች መሪ/ንቁ ተሳታፊ አገልጋዮችን ማፍራት እና ማሠማራት፤
  • የተተኪውን ትውልድ ምንጭ ለማጎልበት የሰ/ት/ቤቶችን አቅም በማጠናከር የሕጻናት እና የወጣቶችን የተተኪነት ሚና ማሳደግ፤
  • ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነትን በተግባር የሚገልጽ ቤተሰብ እና አንድነቱን የጠበቀ ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰብ በመገንባት የተደራጀ እና የተናበበ አገልግሎት መስጠት፤
  • በተደራጀ እና ተደራሹን ማእከል ባደረገ መንገድ ስብከተ ወንጌልንና ሐዋርያዊ ተልእኮን ዘርፈ ብዙ በሆኑ መንገዶች በመላው ዓለም ማስፋፋት፤
  • በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚነዙትን የርእዮተ ዓለም፣ የሐሰት ትርክቶች እና የአጽራረ ቤተ ክርስቲያንን እንቅስቃሴ ጥናት እና ምርምር ላይ ተመርኩዞ መሞገት እና የተሳሳቱትን በማረም፣ በጠንካራ የዕቅበተ እምነት አገልግሎት የቤተ ክርስቲያንን ሕልውና ማስጠበቅ፤
  • በተመረጡ ገዳማት እና አብነት ትምህርት ቤቶች የልኅቀት ማእከል እና የተለየ ክርስቲያናዊ ተልእኮ የሚፈጽሙ እንዲሆኑ የሚያስችል ሁለገብ የአእምሮ ልማት ድጋፍ ማድረግ፤
  • ማኅበሩ ዘመኑን የዋጀ ተቋማዊ የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት ተልእኮውን ማሳካት የሚችልበት አቅም መፍጥር ( በአመራር፣ በሰው ኃይል፣ በመንፈሳዊነት፣ በግንኙነት፣ በዕውቀት፣በልማት፣ በፋይናንስ፣ በቴክኖሎጂ)፤
  • ዓለም አቀፍ ግንኙነትና የትብብር አገልግሎትን መርሕ ያደረገ የኦርቶዶክሳውያን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎ ማሳደግ፣

አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ
የሸዋ ሊቀ ጳጳስ ፲፱፻፴፪-፲፱፻፹፪ዓ.ም.

የማኅበሩ ህንጻ