መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
በዓለ ደብረ ታቦር
በታቦር ተራራ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ዕለት ነሐሴ ፲፫ ”በዓለ ደብረ ታቦር‘ የከበረ በዓል ነው፡፡ ኦርቶዶክሳዊት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም በድምቀት ታከብረዋለች፡፡ ደብረ ታቦርም የቤተ ክርስቲያን አምሳል ነች፤ ከብሉይና ከሐዲስ በውስጧ ሰብስባለችና።
‹‹ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው›› (መዝ.፻፳፯፥፫)
ከፍጥረታት ሁሉ የሰው ልጅ በቅድስት ሥላሴ አርአያና አምሳል የተፈጠረ ክቡር ፍጥረት ነው፤ የፍጥረት ሁሉ መፈጠር ትርጉም ያገኘው የሰው ልጅ ሲፈጠር ነው፤ እግዚአብሔር ፍጥረታትን በአርምሞ የፈጠራቸው፣ በመናገር የፈጠራቸው እና ካለሞኖር ወደ መኖር በማምጣት ፈጠራቸው፤ አዳምን (የሰው ልጅን) ሲፈጥር ግን በሦስቱም ግብር ነው፤ በማሰብ ‹‹…ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር›› ብሎ በመናገር፣ ከዚያም ከምድር አፈር (ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋ ከውኃ፣ ከመሬት፣ ከነፋስ እና ከእሳት) በማበጀት በኋላም የሕይወትን እስትንፋስ እፍ በማለት ፈጥሮታል፤ (ዘፍ.፩፥፳፮)ሰው ክቡር ፍጥረት ነው መባሉ ለዚህ ነው፡፡
ፅንሰታ ለማርያም
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እናት ቅድስት ሐና የተወለደችው በቤተ ልሔም ይሁዳ ውስጥ ነው፡፡ ኢያቄም የሚባል ሰው አግብታ ትኖር ነበር፡፡ ሁለቱም በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ነበሩ፡፡ ሆኖም ግን ሐና መካን ስለነበረች ልጅ መውለድ አልቻሉም፡፡ በዚህም ለበርካታ ዓመት ሲያዝኑና አምላካቸውን ሲማጸኑ ኖሩ፡፡ በዚህም መካከል ስዕለትን ተሳሉ፤ ፈጣሪ ልጅ ቢሰጣቸው ለቤተ ክርስቲያን አገልጋይ እንደሚሰጡም ቃል ገቡ፡፡
ጾመ ፍልሰታ ለማርያም
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት ናችሁ? የክረምቱን ወቅት ምን ቁም ነገር እየሠራችሁበት ነው? ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ መንፈሳዊ ትምህርት እየተማራችሁ እንደሆነ ተስፋ እናደርጋለን፤ ልጆች! ለዛሬ የምንማረው ስለ ፍልሰታ ጾም ነው፤
ለሲኖዶሳዊ ልዕልና መከበር የምእመናን ድርሻ ከፍተኛ ነው!
በሀገር አቀፍ ደረጃ የፖለቲካ ተሰሚነት እና ውክልና እንዳይኖራት፣ እጅግ ብዙ ችግር እንዲከባት ተሠርቷል፤ አሁንም እየተሠራ ይገኛል፡፡ ይህንም ለማድረግ የተቻለው በተቀናጀ ስልት ሲሆን ሲኖዶሱ ክብሩ ልዕልናው እንዳይጠበቅ በማድረግ፣ የመሪነት ሚናውን እንዳይወጣ፣ የተጠራበትን ሰማያዊ ተልእኮውን እንዳያሳካ፣ በመከፋፈል እና በራሱ ውስጣዊ አጀንዳ እንዲጠለፍና፣ ውሳኔው መሬት እንዳይነካ በማድረግ ነው፡፡ ከምንም በላይ መሪና ተመሪ እንዳይገናኙ፣ ሲኖዶሱ በምእመናን ዘንድ ተቀባይነት እንዲያጣ አድርጎታል፡
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል
መልአኩ ዑራኤል “አፍህን ክፈት፤ እኔም የማጠጣህን ጠጣ” … ብሎ አእምሮ ለብዎውን ገልጦለታል። (ዕዝ.ሱት. ፲፫፥፴፰) የዚህን ተአምር መታሰቢያ ሐምሌ ፳፪ በየዓመቱ ቤተ ክርስቲያናችን ታከብራለች።
“ልጄ ሆይ ከእንግዲህ አባቴ ነህ!”
መኮንኑ አፈረና ጽኑ ሥቃይ ሊያሠቃያቸው ወድዶ እንደ ክረምት ነጎድጓድ ድምፅ ወደ ሚያስተጋባው የፈላ ውኃ እንዲጥሏቸው አዘዘ፤ ያን ጊዜ እናቱ ፈራች፤ ሕፃኑ ግን ለእናቱ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እንዲህም አላት፤ “እናቴ ሆይ አትፍሪ! ጨክኝ፤ አናንያ አዛርያ ሚሳኤልን ያዳነ አምላክ እኛንም ያድነናል” አላት። እናቱ ቀና ብላ ብትመለከት ለቅዱሳን ሰማዕታት የተዘጋጁትን የብርሃን ማደርያቸውን ተመለከተች፤ ደስም ተሰኝታ እንዲህ አለች፤ “ልጄ ሆይ ከእንግዲህ አባቴ ነህ፤ እኔም ልጅህ ነኝ፤ አንተን የወለድኩባት ቀን የተባረከች ናት፡፡”
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት የተሰጠ መግለጫ
ቅዱስ ኤፍሬም
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁ? ወርኃ ክረምትን እንዴት እያሳለፋችሁ ነው? ዘመናዊ ትምህርት ተጠናቆ አሁን ዕረፍት ላይ እንደመሆናችሁ መጠን ጊዜያችሁን በተገቢው መንገድ እየተጠቀማችሁበት እንደሆነ ተስፋ እናደርጋለን! በጥሩ ውጤት ከክፍል ክፍል እንደተዘዋወራችሁም ተስፋ አለን፡:ልጆች! ዛሬ የምንነግራችሁ የቅዱስ ኤፍሬምን ታሪክ ነው፡፡
ለሲኖዶሳዊ ልዕልና መከበር የምእመናን ድርሻ አስፈላጊ ነው!
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ቤተ ክርስቲያን የመልካም አስተዳደር ችግሮች እና የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና አለመከበር እንዲሁም በርካታ ምእመናን በቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ጉዳዮች ባይታዋር የሆኑበት፣ ቤተ ክርስቲያንን ለካህናቱና ጳጳሳቱ ብቻ እየተው የመጡበት ሁኔታ ይታያል፡፡
ቅድስት ቤተ ክርስትያንን ፖለቲከኞች፣ አማሳኞች፣ ምንደኞች አገልጋዮች እንዲሁም የውስጥም ሆነ የውጭ ጠላቶቿ አጀንዳ ሲያደርጓት፣ ባልዋለችበት ሲያውሏት፣ የማይገልጻትን ጥላሸት ሲቀቧት፣ ታሪኳን ሲሰርዙ፣ ሲደልዙ፣ የፕሮፖጋንዳ ሰለባ ሲያደርጓት፣ በባሰ ሁኔታ ኵላዊትነቷን፣ ዓለማቀፋዊነቷን ወደ ጎን በማለት በርካሽ የጎሳ ከረጢት ሊከቷት ሲሞክሩ እያዩ ዝም ማለታቸው ነው፡