መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
መራሕያን ምድብ ተውላጠ ስሞች /Pronoun/
ነሐሴ 1 ቀን 2006 ዓ.ም.
በመ/ር ደሴ ቀለብ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፊሎሎጂ መምህር
መራሕያን ማለት “መሪዎች” ማለት ሲሆን በግእዝ ቋንቋ አስር /10/ የሚሆኑ ተውላጠ ስሞች /መራሕያን/ አሉ፡፡ እነርሱም፡-
አነ …………………..እኔ
አንተ…………………. አንተ
አንቲ ………………… አንቺ
ውእቱ ………………. እርሱ
ይእቲ ………………. እርሷ
ንሕነ ………………… እኛ
አንትሙ………………. እናንተ /ለቅርብ ወንዶች/
አንትን ………………. እናንተ /ለቅርብ ሴቶች/
ወእቶሙ ……………… እነዚያ /ለወንዶች/
ውእቶን …………….. እነዚያ /ለሴቶች/
ለአብነት ተማሪዎች የአልባሳትና የንጽሕና መጠበቂያ ድጋፍ በመደረግ ላይ ነው
ሐምሌ 28 ቀን 2006 ዓ.ም.
እንዳለ ደምስስ
በ150 አብነት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለሚገኙ ለ10 ሺህ የአብነት ትምህርት ተማሪዎች ለማዳረስ ሥርጭቱ ይቀጥላል፡፡
“ያለኝ አንድ የተቀደደ ሱሪና አንድ ሸሚዝ ብቻ ነበር ፤ ቅያሪ ስለሌለኝ በመጨነቅ ላይ ሳለሁ በመድረሳችሁ እግዚአብሔር ይስጥልኝ” ከአብነት ተማሪዎች አንዱ::
በማኅበረ ቅዱሳን የቅዱሳት መካናት ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዋና ክፍል አስተባባሪነት “ሁለት ልብሶች ያሉት” በሚል መሪ ቃል ከምእመናን አልባሳትና ቁሳቁሶችን በማሰባሰብ በየአኅጉረ ስብከቱ ለሚገኙ የአብነት ትምህርት ተማሪዎች የአልባሳትና የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡
ቅዱስ ፓትርያርኩ ጾመ ፍለሰታን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ
ሐምሌ 28 ቀን 2006 ዓ.ም.
ዲ/ን ፍቃዱ ዓለሙ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት በየዓመቱ ከነሐሴ 1 እስከ 16 የሚጾመው የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ጾም ዘንድሮም የፊታችን ሐሙስ ይጀምራል፡፡
ከጠረፋማ አካባቢዎችና ከግቢ ጉባኤያት ለተውጣጡ ተተኪ መምህራን ሥልጠና እየተሰጠ ነው
ሐምሌ 17 ቀን 2006 ዓ.ም.
እንዳለ ደምስስ
የአውሮፓ ማእከል ጠቅላላ ጉባኤ ተደረገ
ሐምሌ 17 ቀን 2006 ዓ.ም.
በአውሮፓ ማእከል ሚድያና ቴክኖሎጂ ክፍል
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን አውሮፓ ማእከል 14ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ከሐምሌ 11 እስከ 14 ቀን 2006 ዓ.ም. በኢጣልያ ዋና ማእከል ሮሜ ማእከል አካሄደ፡፡
“መላእክት ሁሉ ረቂቃን አይደሉምን የዘላለም ሕይወትን ይወርሱ ዘንድ ላላቸው ለአገልግሎት ይላኩ የለምን” ዕብ.1፡14
ሐምሌ 17 ቀን 2006 ዓ.ም.
መላእክት እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን የሰማይንም ሠራዊት ፈጠረ በሚለው አንቀጽ እንደተጠቀሰው፤በመጀመሪያው ቀን በዕለተ እሑድ በእግዚአብሔር ቃል ተፈጥረዋል፡፡ እግዚአብሔር አፈጣጠሩ ድንቅ ነውና መላእክትን እንደ እሳትና ነፋስ የማይዳሰሱ የማይታዩ አድርጎ ፈጥሯቸው ያመሰግኑታል፡፡ ዘፍ.1፡1 መዝ.108፡4፣ ዕብ.1፡12
እግዚአብሔር የፈጠራቸው 20 ዓለማት ሲኖሩ ሦስቱ፤ ኢዮር፣ ራማ፣ ኤረር የመላእክት ከተሞች ናቸው፡፡
የጎንደር መካነ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን
ሐምሌ 16 ቀን 2006 ዓ.ም.
እንዳለ ደምስስ
ክፍል ሁለት
ጥምቀት
በጎንደር ጥምቀትን አስመልክቶ ታቦታት ከመንበራቸው ወጥተው ወደ ጥምቀተ ባሕር የሚወርዱበትና የሚመለሱበት ሦስት ዓይነት ሥርዓት ይገኛሉ፡፡ እነዚህም እየተፈጸሙ እስከ ዛሬ ድረስ ደርሰዋል፡፡
ሊቁ አለቃ ወልደ ሰንበት ተገኝ አረፉ
ሐምሌ 15 ቀን 2006 ዓ.ም.
እንዳለ ደምስስ
ማኅበረ ቅዱሳን ከ40,000 በላይ የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎችን አስመረቀ
ሐምሌ 15 ቀን 2006 ዓ.ም.
እንዳለ ደምስስ
ማኅበረ ቅዱሳን በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ከ40,000 በላይ የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎችን አስመረቀ ፡፡
ክረምት
ሐምሌ 15 ቀን 2006 ዓ.ም.
ካለፈው የቀጠለ
ከሐምሌ 19 እስከ ነሐሴ 21 ቀን ድረስ ያለው መካከለኛ ክረምት በመባል ይታወቃል፡፡ የክረምት ኃይልና ብርታት እንዲሁም ክረምትን ጥግ አድርገው የሚከሰቱ የተፈጥሮ ኃይላት ዑደት ያጸናበታል፡፡\ የዕለቱ ቁጥርም 33 ዕለት ነው፡፡ በዚህ ጊዜ መብረቅ፣ ነጎድጓድ ባሕርና አፍላግ ይሰለጥናሉ፡፡
መብረቅ የአምላክን ፈጣንነት፣ ነጎድጓድ የግርማውን አስፈሪነት፣ ባሕር የምሕረቱን ብዛት የሚያመለክቱ የእግዚአብሔር ባሕርይ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ በዚህ ወቅት ጥልቆቹ የውኃ ቦታዎች መጠናቸው ያድጋል፣ የወንዞች ሙላት ይጨምራል፣ ምንጮች ይመነጫሉ፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድም “ዘይመይጦ ለመብረቅ ወያጸንኦ ለነጎድጓድ ዘርዋነ ያስተጋብዕ ወያበርህ ለመሃይምናን” /ድጓ ዘክረምት/ መብረቅን የሚመልሰው፣ ነጎድጓድን የሚያበረታው የተበታተኑትን ይሰበስባል፣ ለሚያምኑባትም ዕውቀትን ያድላል በማለት ብርሃንን ከምዕራብ ወደምሥራቅ እንደሚመልሰው ሁሉ መብረቅንም ካልነበረበት በጋ ወደሚኖርበት ክረምት የሚያመጣውና መገኛውን ደመና የሚፈጥርለት እርሱ ብቻ መሆኑን ያስረዳል፡፡