መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
ተዝካረ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጻድቅ
አባታችን ተክለ ሃይማኖት ሕይወታቸዉን ሙሉ ለእግዚአብሔር በመስጠት፣ እንደ በሬ ተጠምደው፣ እንደገበሬ ታጥቀው ይህንን ዓለም ንቀው በጾም በጸሎት ተወስነው በብሕትውና ከመኖራቸው በተጨማሪ እንደቅዱሳን ሐዋርያት ወንጌልን በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ የሰበኩ፣ በጌታችን በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ድውያነ ሥጋን በተአምራት፣ ድውያነ ነፍስን በትምህርት የፈወሱ ሐዋርያ ናቸው፡፡
ብፁዕ ሥራ አስኪያጁ የአንድነት ኑሮውን አበረታቱ
‹‹የአንድነት ኑሮው ዓላማና ተልእኮ ከመላው የኢትዮጵያ ክፍሎች የተውጣጡ በልዩ ልዩ ቋንቋዎች ማስተማር የሚችሉ ሰባክያነ ወንጌልን በማሠልጠን ወንጌልን ማዳረስና የአብነት ትምህርት በማስተማር በአገልጋይ ካህን እጦት ምክንያት የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናት አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ነው፤››
‹‹ትርጓሜ ያሐዩ›› በሚል ኃይለ ቃል የውይይት መርሐ ግብር ተካሔደ
በዕለቱ የጎንደር መንበረ መንግሥት መድኀኔ ዓለም የአራቱ ጉባኤያት ምስክር ጉባኤ ቤት መምህርና የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪ ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ በአንድምታ ትርጕም ያዘጋጇቸው ትንቢተ ኢሳይያስ፣ ሃይማኖተ አበውና ድርሳነ ቄርሎስ ወጰላድዮስ ምስለ ተረፈ ቄርሎስ ተመርቀዋል፡፡
ክብረ ድንግል ማርያም
‹‹በእግዚአብሔር፣ በመላእክትና በሰው ፊት የከበረ ሰው መታሰቢያው ለዘለዓለም ነው፡፡ በቤቱ በቅጥሩ የማይጠፋ የዘለዓለም ስምን ይቀበላልና›› /ኢሳ.፶፭፥፫/፡፡ ይህንን ታላቅ በረከት እንደሚሰጣቸው የተናገረው የማይዋሸው ቅዱስ እግዚአብሔር ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ወልድ እናት ከድንግል ማርያም የበለጠ በሰውና በእግዚአብሔር ዘንድ የከበረ ማንን ልንጠራ እንችላለን? እንደ እርሷስ ሊታሰብ፣ ሊከበርም የሚችል በቅድስና ሕይወት ያለፈ ማን ይኖራል?
ቤተ ክርስቲያናችን ፳፰ ቤቶቿን አስመለሰች
አስመላሽ ኰሚቴው ባደረገው ያለሰለሰ ጥረት በሦስት ክፍለ ከተሞች ማለትም በልደታ ፲፰፤ በየካ ፭ እና በቂርቆስ ፭ በድምሩ ፳፰ ቤቶች ነሐሴ ፲፱ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም ለባለንብረቷ ለቤተ ክርስቲያን መመለሳቸው ተረጋግጧል፡፡
ዘመነ ክረምት ክፍል ሦስት
‹‹ለነፍሳችሁ በምትበሉት ወይም ለሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፡፡ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ ይበልጣልና፡፡ ቍራዎችን ተመልከቱ፤ አይዘሩም፤ አያጭዱምም፡፡ ዕቃ ቤትም ወይም ጎተራ የላቸውም፤ እግዚአብሔርም ይመግባቸዋል፡፡ እናንተ ከወፎች ትበልጡ የለምን? … የእናንተም አባት ይህ እንዲያስፈልጋችሁ ያውቃል:: ዳሩ ግን መንግሥቱን ፈልጉ፤ ይህም ኹሉ ይጨመርላችኋል፡፡››
ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ማወቅ የችግሮች መፍትሔ መኾኑን ብፁዕ ሥራ አስኪያጁ ገለጡ
‹‹ኹሉም ሕዝበ ክርስቲያን ክርስቲያናዊ መብትና ግዴታውን ዐውቆ እናት ቤተ ክርስቲያንን በፍቅር በማገልገል መንፈሳዊ አደራውን ሊወጣ ይገባል››
በዓለ ፍልሰታና ሻደይ
ከነሐሴ ፲፮ እስከ ነሐሴ ፳፩ ቀን ድረስ የሚከበረው ይህ በዓል በዋግ ኽምራ ‹‹ሻደይ››፣ በላስታ ‹‹አሸንድዬ››፣ በትግራይ ‹‹አሸንዳ››፣ በቆቦ አካባቢ ‹‹ሶለል››፣ በአክሱም አካባቢ ደግሞ ‹‹ዓይነ ዋሪ›› እየተባለ ይጠራል።
‹‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦትም›› /መዝ.፻፴፩፥፰/
ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በትንቢቱ «ተንሥእ እግዚኦ ውስተ ዕረፍትከ አንተ ወታቦተ መቅድስከ፤ አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦትም» /መዝ.፻፴፩፥፰/ በማለት አስቀድሞ የክርስቶስን ትንሣኤ ከገለጸ በኋላ ቀጥሎ የመቅደሱ ታቦት እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ከሞት እንደምትነሣ ተናግሯል /ማቴ.፭፥፴፭፤ ገላ.፬፥፳፮፤ ዕብ. ፲፪፥፳፪፤ ራእ.፫፥፲፪/፡፡
አስደናቂው የድንግል ማርያም ሞትና ትንሣኤ
መንፈስ ቅዱስ በድንግልና ፀንሳ በድንግልና መውለዷን በትንቢት እንዳናገረ ትንሣኤዋንም በትንቢት ሲያናግር ኖሯልና ይህ ታላቅ ምሥጢር በቅዱስ ዳዊት አንደበት ‹‹ተንሥእ እግዚኦ ውስተ ዕረፍትከ አንተ ወታቦተ መቅደስከ፤ አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦትም›› ተብሎ ተገልጿል /መዝ.፻፴፩፥፰/፡፡