• እንኳን በደኅና መጡ !

ዜናዎች፣ ወቅታዊ ክንውኖች እና ልዩ ልዩ ይዘቶች

ደብረ ዘይት፡- ዳግም ምጽአት

በመዋዕለ ስብከቱ ስለ ዳግም ምጽአቱና ምልክቶቹ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ በዝርዝር በደቀ መዛምርቱ በኩል አሳውቆናል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ በወንጌሉ እንዲህ ይገልጸዋል፡፡…

የምሕረት ቤት

የፍቅር ባለቤት፣ የምሕረት ጌታ፣ የዓለሙ ሁሉ መድኃኒት፣ የሰው ልጆች ቤዛ ጌታችን በተወለደባት በኢየሩሳሌም ከተማ በቤተ መቅደሱ አቅራቢያ የምትገኝ በዕብራይስጥ ቋንቋ “ቤተ ሳይዳ” በአማርኛው ደግሞ “የምሕረት ቤት” የተባለች የመጠመቂያ ቦታ ነበረች፡፡

መፃጒዕ

ለሠላሳ ስምንት ዓመታት ያህል በደዌ ዳኛ፣ በአልጋ ቁራኛ ተይዞ የኖረ መፃጉዕን በአልጋው ተኝቶ ሳለ ደዌው እንደጠናበት ፈውስ እንደዘገየበት አይቶ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቀርቦ “ባድንህ ፈቃድህ ነውን?” አለው።ቅዱስ ጳውሎስ “የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል…” ብሎ የመሰከረለት ጌታችን ፈውስን በመጠባበቅ ላይ የነበረውን ይህን ሰው አይቶ ፈቃዱን እያወቀ ግን ፍቀድልኝና ላድንህ አለው።

‹‹ነገን ዛሬ እንሥራ››

ውድ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? ባለፉት ሁለት ክፍሎች ‹‹ነገን ዛሬ እንሥራ›› በሚል ርእስ ጽሑፍ አድርሰናችኋል፡፡ አንብባችሁ ቁም ነገር እንዳገኛችሁ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ አሁን ደግሞ ክፍል ሦስትን ይዘንላችሁ ቀርበናል፤ መልካም ንባብ!

ምኵራብ፡- የዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት

“ቦአ ኢየሱስ ምኵራበ አይሁድ ወመሐረ ቃለ ሃይማኖት፤ ወይቤሎሙ ምጽዋተ አበድር እመሥዋዕት፤ አነ ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት ወአቡሃ ለምሕረት፤ እግዚኣ ውእቱ ለሰንበት ወልደ እጓለ እመሕያው፤ ጌታችን ኢየሱስ ወደ አይሁድ ምኵራብ ገባ፤ የሃይማኖት ቃልን አስተማረ፤ ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን እወዳለሁ፤ የሰንበት ጌታዋ የምሕረት አባቷም እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም የሰንበት ጌታዋ ነው።” (ጾመ ድጓ)

የእግዚአብሔር ባሕርያት

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁልን!  እንኳን ለታላቁ ዐቢይ ጾም አደረሳችሁ! በዚህ ጊዜ ግን ልጆች ከሰባት ዓመት ጀምሮ መጾም እንደሚጀመር እናስታውሳችሁ! መልካም! አሁን ለዛሬ ወዳዘጋጀንላችሁ ትምህርት እናምራ፡፡ ባለፈው “ሀልዎተ እግዚአብሔር” በሚል ርእስ ተምረን ነበር፤ ዛሬ ደግሞ የእግዚአብሔር ባሕርያት ምን እንደሆኑ እንማራለን!-

‹‹ነገን ዛሬ እንሥራ!››

ውድ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? ባለፈው ሳምንት ‹‹ነገን ዛሬ እንሥራ›› በሚል ርእስ ባቀረብንላችሁ ጽሑፍ ቤተ ክርስቲያን ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዴት እየተላለፈች ወደ እኛ  እንደደረሰችና እኛም እንዴት ከአባቶቻችንና እናቶቻችን እንደተረከብናት በጥቂቱ የዳሰስንበትን ክፍል አድርሰናችኋል፡፡ በዚህ በክፍል ሁለት ደግሞ ከክፍል አንድ የቀጠለውንና “ቤተ ክርስቲያንን እኛስ እንዴት ለቀጣዩ ትውልድ እናስተላልፋት?፡ የሚለውን ክፍል ይዘንላችሁ ቀርበናል፤ መልካም ንባብ!

‹‹ዕለት ዕለት የሚያሳስበኝ የቤተ ክርስቲያን ነገር ነው›› (፪ኛ ቆሮ.፲፩፥፳፰)

ታላቁ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ይህን ቃል የተናገረው ለቆሮንቶስ ሰዎች በላከው መልእክቱ ነው፡፡ ዕለት ዕለት ጽኑ የሆኑ መከራዎች ያጋጠሙት ቢሆንም ያ ሁሉ ሳያሳስበው፣ ሳይከብደውና ሳያስጨንቀው በመዓልትም በሌሊትም ዕረፍት የሚነሣው የቤተ ክርስቲያን ነገር ነበር፡፡ የተጠራው ለቤተ ክርስቲያን እንዲያስብና እንዲያገለግል በመሆኑ ቅዱስ ጳውሎስ የደረሱበትን ችግሮች ሁሉ ገለጸላቸው፡፡

ቅድስት፡ የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት

የቅድስና ባለቤት የሆነው እርሱ እግዚአብሔር አምላክ ነው። እቀደስ አይል ቅዱስ፣ እባረክ አይል ቡሩክ ነው። በእርሱ የባሕርይ ቅድስና እኛን በአርአያውና በአምሳሉ ፈጥሮ ቡሩክ ሆኖ ባረከን፣ ቅዱስ ሆኖ ቀደሰን፣ሕያው ሆኖ ሕያዋን አደረገን። የጸጋ ቅድስናንም ከእርሱ አገኘን።

የምን አለበት መዘዝ!

“በምን አለበት” ሰበብ ከእግዚአብሔር ሕግና ትእዛዝ ልንወጣ አይገባም፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “እንደ ርግብ የዋህ፣ እንደ እባብ ልባሞች (ብልጦች) ሁኑ” ያለው ያልተገባ የዋህነት ስለሚጎዳ ነው፤ ብዙ የዋሃን በየዋህነት ሃይማኖታቸውን የለቀቁ አሉ፡፡ እኛን ግን እግዚአብሔር አምላካችን በሃይማኖትና በምግባር ያጽናን፡፡

በፌስቡክ የትስስር ገጽ ያግኙን

ስለ ማኅበረ ቅዱሳን መሰረታዊ መረጃዎች

ስያሜ

ማኅበረ ቅዱሳን እግዚአብሔር ያከበራቸው የነቢያት፣ የሐዋርያት፣ የጻድቃንና የሰማዕታት በአጠቃላይ የቅዱሳን ገድል፣ ትሩፋትና አማላጅነት የሚዘከርበት በመሆኑ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን›› የሚል ስያሜውን አግኝቷል፡፡

የማኅበሩ ርእይ

ቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ የመሪነት ሚናዋን ስትወጣ ማየት

ተልእኮ

ለቤተ ክርስቲያን ተልእኮ መሳካት እና ለሕልውናዋ የሚተጋ፣ የተደራጀ ፣ ምሉዕ ኦርቶዶክሳዊ፤ ርቱዕ ዘመናዊ፤ ሁለገብ መሪ ትውልድ ማፍራት እና ማሰማራት

እሴቶች

  • መንፈሳዊነት

    ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
  • አገልጋይነት

    የማኅበሩ አባላት አገልግሎትን የክርስቲያናዊ ሕይወታቸው መገለጫ አድርገው በመቀበል በበጎ ፈቃድ ሰማያዊውን ክብርና ጸጋ በመሻት፣ ምድራዊ ክብርና ውዳሴ ከንቱን ሳይፈልጉ፣ በትሕትና እና በክርስቲያናዊ ፍቅር በታማኝነት ያገለግላሉ::
  • የሐሳብ መሪነት

    ማኅበሩ ለቤተ ክርስቲያን ዘላቂ አገልግሎት የሚያስፈልጉ፣ ኦርቶዶክሳዊ እሳቤን የተከተሉና ዘመኑን የዋጁ የመሪነት ሐሳቦችን በማፍለቅ ከሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ጋር በመመካከር ይሠራል::
  • ተባባሪነት

    ማኅበሩ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሁሉም የቤተ ክርስትያን አካላት የወል ተግባር ነው ብሎ ያምናል:: በመሆኑም እንደየጉዳዩ አግባብነት ካላቸው ባለ ድርሻ እና አጋር አካላት ጋር በመግባባት፣ በመመካከር እና በቅንነት ለተልእኮ አንድነት ብዝኃ ጸጋን በማክበር አብሮ ይሠራል::
  • ሙያ አክባሪነት

    የማኅበሩ አባላት ባላቸው ልዩ ልዩ ሙያ /ዕውቀት/ ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገል የተሰባሰቡ በመሆናቸው፣ በማኅበሩ አሠራሮች ሁሉ ከኦርቶዶክሳዊው ትምህርተ ሃይማኖት ጋር በማይጋጩ በእውነተኛ መረጃ ለሚደገፉ ሙያዊ ምክረ ሐሳቦች ተገቢውን ክብርና ቅድሚያ ይሰጣል:: በቤተ ክርስቲያንም ለመንፈሳዊ እና ለዘመናዊው (አስኳላ) ሙያ ተገቢው ክብር እንዲሰጥ ይሠራል::
  • ምክንያታዊ ሞጋችነት

    ማኅበሩ በእውነተኛ መረጃ ላይ ተመሥርቶ ቤተ ክርስቲያንን ከውስጥም ሆነ ከውጭ የሚፈትኑ አስተሳሰቦችን፣ አሠራሮችን፣ ልማዶችን እና ትርክቶችን በግልጽና በመንፈሳዊ ጥብዓት እና በእውነት እንዲሞገቱና መፍትሔ ላይ እንዲደረስ ይሠራል::
  • ተጠያቂነት

    የማኅበሩ አገልግሎት ግብ ሰማያዊ ዋጋ ማግኘት ስለሆነ ኀላፊነትን በአግባቡ አለመወጣት በእግዚአብሔር እና በሰዎች ዘንድ የሚያስጠይቅ በመሆኑ በየትኛውም እርከን ላይ ያለ አባል እና አመራር በማኅበሩ አሠራር መሠረት በተሰጠው ኀላፊነት ተጠያቂ ይሆናል፡፡

ዓላማዎች

  • የቤተ ክርስቲያን ተቋማዊ አስተዳደር፣ የአሠራር ሥርዐትና አስተሳሰብ፣ በቴክኖሎጂ እና በልዩ ልዩ መንገዶች በመደገፍ ዘመኑን ለዋጀ ጠንካራ አገልግሎት ማብቃት፤
  • የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን ሙሉ ሰብእናን የሚገነባ ሥርዐተ ትምህርት በማስተማር ዘመኑን የዋጁ ምሉዕ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር የሚያገለግሉ እንዲሁም በማኅበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ በፖለቲካዊ እና በሀገር አስተዳደር ጉዳዮች መሪ/ንቁ ተሳታፊ አገልጋዮችን ማፍራት እና ማሠማራት፤
  • የተተኪውን ትውልድ ምንጭ ለማጎልበት የሰ/ት/ቤቶችን አቅም በማጠናከር የሕጻናት እና የወጣቶችን የተተኪነት ሚና ማሳደግ፤
  • ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊነትን በተግባር የሚገልጽ ቤተሰብ እና አንድነቱን የጠበቀ ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰብ በመገንባት የተደራጀ እና የተናበበ አገልግሎት መስጠት፤
  • በተደራጀ እና ተደራሹን ማእከል ባደረገ መንገድ ስብከተ ወንጌልንና ሐዋርያዊ ተልእኮን ዘርፈ ብዙ በሆኑ መንገዶች በመላው ዓለም ማስፋፋት፤
  • በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚነዙትን የርእዮተ ዓለም፣ የሐሰት ትርክቶች እና የአጽራረ ቤተ ክርስቲያንን እንቅስቃሴ ጥናት እና ምርምር ላይ ተመርኩዞ መሞገት እና የተሳሳቱትን በማረም፣ በጠንካራ የዕቅበተ እምነት አገልግሎት የቤተ ክርስቲያንን ሕልውና ማስጠበቅ፤
  • በተመረጡ ገዳማት እና አብነት ትምህርት ቤቶች የልኅቀት ማእከል እና የተለየ ክርስቲያናዊ ተልእኮ የሚፈጽሙ እንዲሆኑ የሚያስችል ሁለገብ የአእምሮ ልማት ድጋፍ ማድረግ፤
  • ማኅበሩ ዘመኑን የዋጀ ተቋማዊ የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት ተልእኮውን ማሳካት የሚችልበት አቅም መፍጥር ( በአመራር፣ በሰው ኃይል፣ በመንፈሳዊነት፣ በግንኙነት፣ በዕውቀት፣በልማት፣ በፋይናንስ፣ በቴክኖሎጂ)፤
  • ዓለም አቀፍ ግንኙነትና የትብብር አገልግሎትን መርሕ ያደረገ የኦርቶዶክሳውያን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎ ማሳደግ፣

አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ
የሸዋ ሊቀ ጳጳስ ፲፱፻፴፪-፲፱፻፹፪ዓ.ም.

የማኅበሩ ህንጻ