መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
‹‹ነገን ዛሬ እንሥራ››
ተወዳጆች! እንዴት ሰነበታችሁ? በክፍል ሰባት እና ስምንት “ምንኩስና ዛሬ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እያጋጠመው ያለውን ተግዳሮት” አንስተን የተወሰኑ ችግሮችን ለማቅረብ ሞክረን ነበር፤ክብረ ምንኩስና ነገ ምን መሆን አለበት? እንዴትስ የተሻለ እናድርገው? የሚለውን በዚህ በክፍል ዘጠኝ ይዘንላችሁ ቀርበናል፤ መልካም ንባብ!
‹‹ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል›› (ሐዋ.፭፥፳፱)
መንፈስ ቅዱስ ያደረባቸው ቅዱሳን ሐዋርያት ይህንን ቃል የተናገሩት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዓለም ለይቶ የጠራቸው፣ የመረጣቸው በመሆናቸው ነው። በዓለም እየተዘዋወሩ ቅዱስ ቃሉን በሚያስተምሩበት በስሙ ተአምራት በሚያደርጉበት ጊዜ ፈተና ነበረባቸው፤ እንቅፋት ያጋጥማቸው ነበረ። ብዙዎች በምቀኝነትና በቅናት እየተነሣሡ እንዳያስተምሩ ይከለክሏቸው ነበረ፤ ይናገሯቸውም ነበረ። በዚህ ሰዓት ነበር ቅዱሳን ሐዋርያት ‹‹ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባናል›› በማለት ያስተማሩት፤ እግዚአብሔር እንዲያስተምሩ አዟቸው ነበርና። (ሐዋ.፭፥፳፱)
‹‹በዚያን ጊዜ ይጾማሉ›› (ማቴ.፱፥፲፮)
‹‹ሚዜዎች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወስድበት ወራት ይመጣል፤ በዚያን ጊዜም ይጾማሉ›› (ማቴ.፱፥፲፴-፲፮)
‹‹ይፈኑ ለክሙ ጰራቅሊጦስሃ፤ አጽናኝ መንፈስ ይልክላችኋል›› (ዮሐ.፲፬፥፲፮)
የቤዛነት ሥራውን ከፈጸመ በኋላ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር ሲያርግ ለሐዋርያት የሰጣቸው ተስፋ አጽናኝና የእውነት መንፈስ የሆነውን መንፈስ ቅዱስን አብ እንደሚልክላቸው፣ እርሱም አጽናኝ የሆነ ጰራቅሊጦስ እንደሆነ ለዘለዓለሙም ከእነርሱ ጋር እንደሚሆን ነግሯቸው ነበር፡፡ ጌታችን እንደተናገረውም በሰጣቸው ተስፋ መሠረት ባረገ በዐሥረኛው ቀን በተነሣ ደግሞ በሃምሳኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ልኮላቸዋል፡፡
ምሥጢረ ቊርባን
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁልን! በዓለ ሃምሳ ተብሎ የሚታወቀውን ወቅት እንዴት አሳለፋችሁት? እንኳን ለብርሃነ ዕርገቱ እንዲሁም ደግሞ ለበዓለ ጰራቅሊጦስ አደረሳችሁ! አሁን ደግሞ በተለምዶ የሰኔ ጾም እየተባለ የሚታወቀው ጾመ ሐዋርያት ሰኔ ፲፯ (ዐሥራ ሰባት) ቀን ይጀምራል፡፡ ከወዲሁ እንኳን አደረሳችሁ እንላለን!
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! በሰንበት (በዕረፍት ጊዜያችሁ ሄዳችሁ) ቤተ ክርስቲያን በመሄድ ማስቀደስ እንደሚገባ፣ መጾም መጸለይ እንዳለብን መዘንጋት የለብንም! በዘመናዊ ትምህርታችሁም ሁለተኛውን መንፈቀ ዓመት ጨርሳችሁ የማጠቃለያ ፈተና የተፈተናችሁ አላችሁ! እንዲሁም ደግሞ እየተፈተናችሁም ያላችሁ ትኖራለችሁና በርትታችሁ ማጥናት ሥሩ! መልካም! አሁን ለዛሬ ወዳዘጋጀንላችሁ ትምህርት እናምራ፤ ባለፈው ምሥጢረ ጥምቀትን ተምረን ነበር፤ ዛሬ ደግሞ የምሥጢረ ቊርባንን ትምህርት እንማራለን፤!
ርኅሩኁና የይቅርታ መልአክ
የርኅራኄ መዝገብ፣ ትሑት፣ ታዛዥና ለዘለዓለም ፈጣሪውን አመስጋኝ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ጌታ በሚያደርገው ቸርነት ላይ ለሰው አንድ ወገን የሚሆን መልአክ ነው፡፡ (ሄኖ.፮፥፭፣፲፪፥፭፣፲፥፲፪)
ማኅቶት!
ለጨለመው ሕይወት ሆኖለት ማኅቶት፣
በብርሃኑ ጸዳል ሰውሮት ከጽልመት ፡፡
የክህነትን ሥልጣን፣ ሥጋውና ደሙን ፣ የንስሐን መንገድ፣
በፍቅሩ ለግሶ መዳንን ለሚወድ፡፡
ያናገረው ትንቢት የሰጠው ምሳሌ፣ በአማን ተፈጽሞ፣
በይባቤ መልአክ በዕልልታው ደግሞ፣
እያለ ከፍ ከፍ ረቆ ያይደለ! እያዩት በርቀት፣
ዐረገ ወደ ላይ ወደ ክቡር መንበሩ ሰማየ ሰማያት፡፡
‹‹ነገን ዛሬ እንሥራ››
ተወዳጆች! እንዴት ሰነበታችሁ? እንኳን ለብርሃነ ዕርገቱ በሰላም አደረሳችሁ! በክፍል ስድስት ክብረ ምንኩስና ትናንት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የነበረውን ክብርና ሞገስ ያስገኘውን የቅድስና ፍሬና ያሳረፈውን አሻራ፣ በክፍል ሰባት ደግሞ ምንኩስና ዛሬ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እያጋጠመው ያለውን ተግዳሮት አንሥተን የተወሰኑ ችግሮችን ለማቅረብ ሞክረን ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ክፍል ስምንትን አቅርበንላችኋልና ተከታተሉን!
ምሥጢረ ጥምቀት
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁልን? በዓለ ሃምሳ ተብሎ የሚታወቀውን ወቅት እንዴት እያሳለፋችሁት ነው? መቼም ልጆች! ጾም የለም ብላችሁ ጸሎት ተግቶ ከመጸለይ፣ ቤተ ክርስተያን በሰንበት በዕረፍት ጊዜያችሁ ሄዶ ማስቀደስን እንደማትዘነጉ ተስፋ እናደርጋለን!
በዘመናዊ ትምህርታችሁም ሁለተኛው የመንፈቀ ዓመት እየተገባደደ በመሆኑ ለማጠቃለያ ፈተና የምትዘጋጁበት ወቅት በመሆኑ በርትታችሁ አጥኑ፤ መልካም! አሁን ለዛሬ ወዳዘጋጀንላችሁ ትምህርት እናምራ! ባለፈው የትምህርት ክፍለ ጊዜያችን ‹‹ምሥጢረ ጥምቀትን›› ተምረን ነበር፤ ዛሬ ደግሞ ምሥጢረ ጥምቀትን ቀጣይ ክፍለ ትምህርት እንማራለን፤ ተከታተሉን!
ከቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ