በእሾህ መካከል የበቀለች ጽጌሬዳ

የውበት ልኬት በእርሷ እንደሆነ እስኪሰማኝ ድረስ ማረከችኝ፡፡ የምድር ጌጥ በመሆኗም ብዙዎች ተደነቁባት፤ ውበቷን በቃላት መግለጽ እስኪያቅታቸው ድረስ ተገረሙባት፡፡ ተፈጥሮዋና ውስጠቷ ዕፁብ የሆነው ጽጌሬዳ በማይነገረው ድንቅ ፍጥረቷ የተማረኩ ብዙኃኑ ሊቀርቧት፣ሊነኳት ወይም ሊያበላሿት አልያም ሊቀጥፏት ይከጅላሉ፡፡…

አማናዊቷ መቅደስ!

የገሃነም ደጆች የማይችሏት ምን ቢጥሩ፣

እንዳትፈርስ አነጻት በይቅርታና በፍቅሩ፡፡

መሰብሰቢያ እንድትሆን ለአምልኮ መፈጸሚያ፣

ሕንጻዋንም ሲመሠርት በምድር ላይ መጀመሪያ፡፡

በተአምራት በእናቱ ስም  በሦስት አዕባን አቆመ፣

የአማናዊቷን መቅደስ ምሳሌዋን በራሷ ስም ሰየመ፡፡

በጴጥሮስ ዐለትነት በገባው ቃል እንደሚሠራት፣

መቅደሱን በእናቱ ስም በፊሊጵሲዩስ አቆማት፡፡

ከቅዱሳኑ ከምርጦቹ ከድንግል ከተቋሙ፣

የሚዘከሩበት ወዳጆቹ የሚጠራበትን  ቅዱስ ስሙ፣

ይድረሰው ግናይ ውዳሴ ለሰጠን መሥርቶ በደሙ!

ማኅቶት!

ለጨለመው ሕይወት ሆኖለት ማኅቶት፣
በብርሃኑ ጸዳል ሰውሮት ከጽልመት ፡፡
የክህነትን ሥልጣን፣ ሥጋውና ደሙን ፣ የንስሐን መንገድ፣
በፍቅሩ ለግሶ መዳንን ለሚወድ፡፡

ያናገረው ትንቢት የሰጠው ምሳሌ፣ በአማን ተፈጽሞ፣
በይባቤ መልአክ በዕልልታው ደግሞ፣
እያለ ከፍ ከፍ ረቆ ያይደለ! እያዩት በርቀት፣
ዐረገ ወደ ላይ ወደ ክቡር መንበሩ ሰማየ ሰማያት፡፡

ጣፋጯ ፍሬ

ዘለዓለማዊ ሕይወትን የማገኝብሽ ባለ መልካሟ መዓዛ ፍሬ የአምላኬ ስጦታ ነሽ፤ በገነት ፈጥሮ ቢያሳየኝ ሳላውቅሽ መቅረቴና ልመገብሽ ባለመቻሌ እጅጉን ኀዘን ይሰማኝ ነበር፡፡ ፈጣሪ በአንቺ ሕይወትን ሊሰጠኝ ጣፋጭ አድርጎ ቢፈጥርሽ ሳላውቅሽ ያልታዘዝኩትን ፍሬ በልቼ መራራ ሞትን በራሴ አመጣሁ፡፡ አሁን ግን አወኩሽ! የሕይወቴ ጣፋጯ ፍሬ በአንቺ ነፍሴ ተፈውሳለችና፡፡

በመቅረዝ ላይ የተቀመጠች መብራት

ከመቅረዜ ላይ አድርጌ ለኮስኳት፡፡ እርሷም ቦገግ ብላ አበራችልኝ፡፡ ከመብራቷ የሚወጣውን ብርሃን ስመለከት ውስጤ ሰላም ይሰማኛል፤ ተስፋም አገኛለሁ፤ በጨለማ ውስጥ መብራት ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ በጭንቅ፣ በመረበሽ እና በሁከት ተወጥሮ ለሚጨነቅ አእምሮዬ ወገግ ብላ እንደምታበራ ብርሃኔ ሆነችኝ፡፡…

መምህር ሆይ!

መሆንህን አውቆ እውነተኛ
ገሰገሰ ወዳንተ በሌሊት ሳይተኛ
ቅዱስ ቃልህንም ሲሰማ ፈወሰው
የታወረ ኅሊናውን አብርቶ አቀናው
ጥያቄውን እንዲያቀርብ አበረታታኸው
ስለ ዳግም ውልደትም አስተማርከው

ሀገሬ!

በአንቺ ነው መኖሬ

የምወድሽ ሀገሬ

ፊደላትን ቆጥሬ

ሃይማኖትን ተምሬ

ያፈራሁብሽ ፍሬ!

ወልድ ተወለደልን!

ኧረ ይህች ቀን ምንኛ ድንቅ ናት!

በዓይን የማይታየው የተገለጠባት

የማይዳሰሰው በአካል የተገኘባት

አንድ አምላክ ፈጣሪ የተወለደባት

እርሱ ነው ተስፋችን የዓለም መድኃኒት

የሆነው ቤዛ ለሁሉ ፍጥረት!

ወልድ ተወለደልን መድኃኒዓለም

በከብቶች በረት በቤተ ልሔም!

ብርሃንህን ላክልን!

ድቅድቁ ጨለማ ተጋርዶ ከፊቴ
ሰላም ቢያሳጣኝ ካለሁበት ቤቴ
ነፍሴን ካስጨነቃት ጥንቱ ጠላቴ
በእስራቱ ኖርኩኝ ጸንቶ ፍርሃቴ
ከልጅነት ጸጋ ለይቶኝ ከአባቴ

በጸሎትህ ጠብቅ!

ከቅዱሳን አበው የሆነ ውልደትህ
የጸሎታቸው መልስ ለእናት ለአባትህ
ክብርህ እጅግ በዛ ተወደደ ሥራህ

ፍጥረት ያስደሰተ የውልደትህ ዜና
ገና ሕፃን ሳለህ የጀመርክ ምሥጋና፡፡
ጽድቅን ተጎናጽፈህ ወንጌል ተጫምተሃል
በጉብዝናህ ወራት መስቀሉን ሽተሃል፡፡

እንደ ጠዋት ጤዛ በምትረግፈው ዓለም
ልብህ ሳይሸነፍ ለምቾት ሳትደክም
ከትዳርህ ይልቅ ምንኩስናን መርጠህ
ከጫጉላ ቤት ወጥተህ በረኃ ተገኘህ፡፡