ጽዮን ሆይ ክበቢኝ!

የገባልሽ ኪዳን የሰጠሽ መሐላ

ከንቱ ነበረ ወይ የጨረቃ ጥላ?

በአጋንንት ፍላጻ ነፍሴ ብትወጋ

ምልጃሽ ነው ተስፋዬ ከጥላሽ ልጠጋ፡፡

ጽዮን ሆይ ክበቢኝ ለውዳሴሽ ልትጋ

የኃጢአት ጎዳናዬ መንገዴ ይዘጋ!

እኔም ልመለስ!

እኔም ልመለስ ድንግል እናቴ
ከስደት ሕይወት ከባርነቴ
በልጅሽ ጉንጮች በወረደ ዕንባ
ባዘነው ልብሽ በተላበሰው የኀዘን ካባ
በእናት አንጀትሽ እንስፍስፍ ብሎ ያኔ በባባ

ልመለስ ድንግል ሆይ እኔም ከስደት
እውነትን ልያዝ ልራቅ ከሐሰት፡፡

ጥላቻ ገዝቶኝ ወንድሜን ከጠላው
እምነት ምግባሬን ሰይጣን ዘረፈው
መልሽኝ ድንግል ይብቃኝ ግዞቱ
በምግባር እጦት በቁም መሞቱ!

ከውድቀት አነሣን!

ለሰሚው በሚከብድ ቃላት በማይገልጸው

በመከራ ውሎ አዳምን አዳነው!

ዲያብሎስ ታሠረ አዳም ነጻ ወጥቶ

ልጅ ተባለ ዳግም በደሉ ተረስቶ

የማይሞተው አምላክ ስለ እኛ ሲል ሞቶ

ከውድቀት አነሣን ልጅነትን ሰጥቶ!

የዛፉ ፍሬ

አዳም ያየ መስሎት ዓይኑ እንደተዘጋ
ይኖር ነበር ገነት ብቻውን ሲተጋ

ሔዋን ባትቀጥፈው የበለሱን ፍሬ
መቼ ይሰማ ነበር የአምላክ ልጅ ወሬ

አዳም የተከለው የፍቅር አበባ አድሮ እየጐመራ
አምስት ሽህ አምስት መቶ ዘመን አብቦ ቢያፈራ
ከላይ ከሰማያት መንበረ ጸባኦት
የአምላክን አንድ ልጅ መዓዛው ጐትቶት

ወዮልኝ!

በኃጢአት ተፀንሼ በዐመፃ ተወልጄ
ከቃልህ ሕግ ወጥቼ በዝንጉዎች ምክር ሄጄ
በኃጢአተኞች መንገድ ቆሜ በዋዘኞች ወንበር ተቀምጬ
በውኃ ማዕበል ሰጥሜ የሞት ጽዋን ጨልጬ

የተራበችው ነፍሴ!

ቀንና ሌት ዙሪያዬን ከቦ ሲያስጨንቀኝ፣ ሲያሠቃየኝ የኖረው ባዕድ ከእኔ ባልሆነ መንፈስ ሊገዛኝና ከበታቹ ሊያደርገኝ ሲጥር በዘመኔ ኖሯል፡፡ ሥቃይና ውጥረት በተቀላቀለበት መከራ ውስጥ ብኖርም ሁል ጊዜ ተስፋን ማድረግ አላቆምኩም፤ ሆኖም ተፈጥሮዬ የሆነውን ሰላም ስናፍቅ የሰማይን ያህል ራቀብኝ፡፡

የከርቤ ኮረብታ

ከሕያው የመዐዘኑ ራስ ድንጋይ

ታንፆ በጽኑዕ ዐለት ላይ

ተዋጅታ በበጉ ደም ቤዛ

ሺህ ዓመታት ሺህ አቀበት ተጉዛ

መልካሟ ርግብ

ከቀለማት ሁሉ በላይ በሆነው፣ የፍጹምነት መገለጫ፣ ሰማያዊ ክብር በሚገለጽበት በጸአዳ ብሩኅነት ደምቃ፣ የንጽሕናን ሞገስ ተከናንባና አሸብርቃ በሰማይ ትበራለች፡፡ ከውልደቷ ጀምሮ የፈጠራት ይህን ሰማያዊ ጸጋ ሲያላብሳት እርሷም “አሜን” ብላ ተቀብላ ሰማያዊ መናን እየተመገበችና በሰማያት ሠራዊት እየተጠበቀች ከምድር ከፍ ከፍ ብላ መብረርን ለምዳ ከቤተ ሰቦቿ ተለየች፡፡

የማያልቀው ሀብት

ነጭ አይሉት ጥቁር፣ አመዳማም አይደል ቀለሙ ይለያል፡፡ብዙዎች ስለ መልኩ መናገር ያዳግታቸውና ዝምታን ይመርጣሉ፤አያሌዎች ደግሞ በተፈጥሮው ተማርከው ውበቱን ያደንቃሉ፤ መግለጽ ግን ያቅታቸዋል፡፡

የቀና ልብ

ድሮ ድሮ ልቡ ሲቀና ሕሊናውን መግዛት ተስኖት፣ አእምሮውን ወጥሮ ሲይዘው፣ ሐሳቡን መሰብሰብና አቅንቶ ማየት ያቅትውና ይጨነቅ ነበር፤ ቀጥተኛውን መንገድ  ጠማማ፣ ከፍተኛውን ኮረብታ ዝቅተኛ፣ አባጣ ጎርባጣውን ምቹ አድርጎ ሲመለከት ለመልካም ነገር መወሰን ይሳነዋል፤ ፍቅር ግን ይህን ሁሉ ቀየረለት፤ በትዕቢት የታወረውን ዓይኑን አብርቶ፣ ትምክህቱንና ጭንቀቱን አጥፍቶ የውስጥ ዕረፍት ሰጥቶታልና፡፡