በዓለ ቅዱስ ገብርኤል
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁልን? ሳምንቱ እንዴት አለፈ? በሰንበት ቤተ ክርስቲያን ሄዳችሁ መንፈሳዊ ትምህርት እየተማራችሁ እንደሆነ ተስፋችን እሙን ነው፤መልካም! ለዛሬ ልንነግራችሁ የተዘጋጀነው ቅዱስ ገብርኤል ከእሳት ስላዳናቸው ሦስቱ ሕፃናትና እና ይህን በዓል አስመልክቶ ክብረ በዓል ከሚከበርባቸው ቅዱሳን መካናት መካከል አንዱ ስለ ሆነው ስለ ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ነው!