‹‹ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ነገር ሁሉ እናንተም አድርጉላቸው›› (ማቴ.፯፥፲፪)
በሕይወታችን ውስጥ ለአምላካችን እንዲሁም ለሌሎች ፍቅራችንን የምንገልጽበት መንገድ ለራሳችን እንደምናደርገውን ሁሉ ከልብ ከመነጨ ፍቃድ ለባልንጀሮቻችን ማድረግ ነው፡፡ መሠረታዊ ነገሮች እንዲሟሉልን ብቻ ሳይሆን ለምድራዊ ኑሮአችን የሚያስፈልጉንን ሁሉ ስናደረግ እንዲሁ ለቤተ ሰቦቻችን፣ ለወዳጆቻችን፣ ለዘመዶቻችን እና ለጎረቤቶቻችን ማድረግን መርሳት የለብንም፡፡ ይህም ማዕድ ከመጋራት ጀምሮ አብሮ እስከ መቸገር፣ መራቆትና ኅዝንንም ሆነ ደስታን እስከ መካፈል ይደርሳል፡፡