በማኅበረ ቅዱሳን ትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ

 

 1. የፕሮጀክቱ ርእስ፡- የስብከት ማእከል አዳራሽ ግንባታ ፕሮጀክት

የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ፡ ሕንጻ አብያተ ክርስቲያናት በሌሉባቸው አካባቢዎች የማእከል የስብከት ማዕከል አዳራሽ በመገንባት ምእመናን ተሰባስበው ቃለ እግዚአብሔር እንዲማሩ ይደረጋል፤

 • የሐዋርያዊ አገልግሎት በሚፈጸምባቸው ጠረፋማና ገጠራማ አካባቢዎች አዳዲስ አማንያንን በጥምቀት የሥላሴን ልጅነት እንዲያገኙ ትምህርተ ሃይማኖት የሚማሩበት፣ ሥርዓተ አምልኮ የሚፈጽሙበት፣ የሚጸልዩበትና እርስ በእርስ የሚመካከሩበት፣ ወጣቶችና ሕጻናት በሰንበት ትምህርት ቤት ታቅፈው ተከታታይ ትምህርት የሚማሩበት 60 (ስድሳ) የማዕከለ ስብከት ማእከላትን መገንባት ነው፡፡
 • ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልግ ወጪ
 • የአንድ ስብከት ማእከል አዳራሽ ግንባታ ወጪ፡-75,000 (ሰባ አምስት ሽህ)
 • ለ60 ስብከት ማእከል አዳራሽ ግንባታ 4,500,000 (አራት ሚሊዮን አምስት መቶ ሽህ)

አሁን ምእመናን እየተማሩ የሚገኙበት በወደፊት ገጠርና ጠረፋማ አካባቢ ምእመናን ቃለ እግዚአብሔር እንዲማሩበት የሚሠራ የስብከት ማእከል

 1. የፕሮጀክቱ ርስ፡- በተለያዩ ቋንቋዎች የሚያገለግሉና ስበከተ ወንጌልን ለማጠናከር ቀዳሚ ሚና የሚጫወቱ ደረጃ አንድ ሰባኪያነ ወንጌልን ማፍራት፣
 • የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ፡ አዳዲስ ተጠማቂያን ባሉበት የገጠርና ጠረፋማ አካባቢ የስበከተ ወንጌልን ተደራሽነት ለማሳደግ በ5 (አምስት) ጠረፋማ ቦታዎች 500 (አምስት መቶ) በተለያዩ ቋንቋዎች  የሚያገለግሉና ስበከተ ወንጌልን በማጠናከር ኢ-ጥሙቃንን በማስተማር ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን በመመለስ የሥላሴ ልጅነት እንዲያገኙ ቀዳሚ ሚና የሚጫወቱ ሰባኪያነ ወንጌልን ማፍራት፣
 • ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልግ ወጪ
 • ለአንድ ሠልጣኝ አማካኝ ወጭ ለአንድ ወር 3000 (ሦስት ሽህ ብር)
 • አጠቃላይ ለ500 (አምስት መቶ) ሠልጣኞች የሚያስፈልግ ወጭ 500*3000=1,500,000 (አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሽህ ብር)

 1. የፕሮጀክቱ ርስ፡- በተለያየ ቦታ ለሚኖሩ ምእመናን ማንኛውንም ሃይማኖታዊ ጥያቄ በቀጥታ በስልክ ምላሽ በመስጠት ምእመናንን ለማጽናት የጠፉትን ለመመለስ ይረዳል
 • የፕሮጀክቱ ዋና ዓላማ፡ ሃይማኖታዊ ጥያቂዎችን በስልክ ምላሽ በመስጠት የስብከተ ወንጌልን አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ ምእመናን ለሚጠይቁት ጥያቂ ምላሽ በመስጠት የተለያዩ የስብከት ዘዴዎችን በመጠቀም ምእመናንን ማጽናት፣ የጠፉትን መመለስና አዳዲሶችን ማጥመቅ
 • ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልግ ወጪ
 • አጠቃላይ በ4 (አራት) ዓመት የ4 (አራት) መምህራን ደመወዝ ወንበር ጠረጴዛ ማዳመጫ የቢሮ ዝግጅትና ኔቶርክ ዝርጋታን ጨምሮ የሚያስፈልግ ወጭ 1,421,400 (አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ሃያ አንድ ሽህ አራት መቶ ብር)

ማጠቃለያ

 የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት እኔ እላካለሁ በማለት የሐዋርያዊ አገልግሎትን የማስፋፋት ኃላፊነት የእያንዳንዱ የቤተክርስቲያን አካል ድርሻ በመሆኑ ረድኤተ እግዚአብሔርን አጋዥ አድርገን  በስሑታን ትምህርት ለተወሰዱትና ቃለ እግዚአብሔርን ናፍቀው በሜዳ ለሚቅበዘበዙት ወገኖቻችን እንደርስላቸው ዘንድ “ኑ የወንጌል ማኅበርተኛ እንሁን!” እያለ ማኅበረ ቅዱሳን መንፈሳዊ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

በማኅበረ ቅዱሳን ትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

የባንክ ሒሳብ ቍጥር፡- 1000195489541

አቢሲኒያ ባንክ

የባንክ ሒሳብ ቍጥር፡- 15376481

አዋሽ ባንክ

የባንክ ሒሳብ ቍጥር፡- 01304024224400

ስልክ ቍጥር፡- +251-9-60-67-67-67

ኢ-ሜይል፡-evangelism.program@eotcmk.org

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

በመዝገበ አእምሮ (encyclopedia) የሚካተቱ ጥናታዊ ጽሑፎችን ለማበርከት የቀረበ ጥሪ

EOTC Encyclopaedia Internal and External Editorial Guidelines

(2) final edited version1 st Round Call for Encyclopedia

List of Entries

የማኅበረ ቅዱሳንን አገልግሎት በመደገፍ ድርሻችንን እንወጣ

የማኅበረ ቅዱሳንን የቴሌቭዥን መርሐ ግብር እና ሌሎች የአገልግሎት ዘርፎችን በገንዘብ ለመደገፍ፡-

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አራት ኪሎ ቅርንጫፍ፣

ሒሳብ ቍጥር፡- 1000003780717

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቍጥር፡-

09 62 16 16 16 /09 62 17 17 17 ይደውሉልን፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን

ማኅበረ ቅዱሳን በ፳፮ ዓመታት ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ያበረከተው አስተዋጽዖ – ክፍል አራት

ማኅበረ ቅዱሳን በ፳፮ ዓመታት ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ያበረከተው አስተዋጽዖ – ክፍል ሦስት

ማኅበረ ቅዱሳን በ፳፮ ዓመታት ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ያበረከተው አስተዋጽዖ – ክፍል ሁለት

ማኅበረ ቅዱሳን በ፳፮ ዓመታት ያበረከታቸው አገልግሎቶች – ክፍል አንድ

የማኅበረ ቅዱሳን መደበኛ የቴሌቭዥን መርሐ ግብር በአሌፍ ጣቢያ

የማኅበረ ቅዱሳን መደበኛ የቴሌቭዥን መርሐ ግብር፣ በየሳምንቱ ቅዳሜ ከሰዓት 11፡00፤ እሑድ ከረፋዱ 4፡30 ጀምሮ በአሌፍ የቴሌቭዥን ጣቢያ በትግርኛ፣ ኦሮምኛ እና አማርኛ ቋንቋዎች በመተላለፍ ላይ ይገኛል፡፡

መርሐ ግብሩም የቅዳሜው፡- ማክሰኞ ከጠዋቱ 1፡00፤ የእሑዱ፡- ሐሙስ ከጠዋቱ 1፡00 ጀምሮ በድጋሜ ይተላለፋል፡፡ መርሐ ግብሩን ትከታተሉ ዘንድ ማኅበረ ቅዱሳን መንፈሳዊ ግብዣ አቅርቦላችኋል፡፡

የቴሌቭዥን ጣቢያው የሥርጭት አድራሻም፡-

Aleph Television Nilesat (E8WB)

Frequency: 11595

Polarization: Vertical

Symbol Rate: 27500

FEC: 3/4

ማኅበረ ቅዱሳን በአፋን ኦሮሞ ያሳተማቸው መጻሕፍት በከፊል

ማኅበረ ቅዱሳን በአፋን ኦሮሞ ካሳተማቸው መጻሕፍት መካከል ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፤

የስብከተ ወንጌል አገልግሎቱንና ሰባክያኑን እንደግፍ

በገጠርና ጠረፋማ አካባቢዎች የሚያገለግሉ ሰባክያነ ወንጌል

በገጠርና ጠረፋማው የአገራችን ክፍል ተበታትነው የሚኖሩ ብዙ ወገኖቻችን እውነተኛውን የወንጌል ብርሃን ሳይመለከቱ፣ ለሥላሴ ልጅነት ሳይበቁ፣ በጎውን ነገር ሳያዩ፣ ድኅነትን እንደ ናፈቁ ሞተ ሥጋ ይቀድማቸዋል፡፡

ጥቂት የእግዚአብሔርን ቃል ያወቁ ወንድሞች የምሥራቹን የእግዚአብሔርን ቃል ለማብሠር፤ ለወገኖቻቸው የወንጌል ብርሃንን ፈንጥቀው ወደ ዘላለማዊ ሕይወት ለማሸጋገር ሲሉ የበረኃው ንዳድ፣ የአራዊቱ ግርማ፣ ረኃቡና ጥሙ፣ ስቃዩና ሕመሙ ሳይበግራቸው፣ እንቅልፍ በዐይናቸው ሳይዞር የሐዋርያትን አሰር ተከትለው ከጠረፍ ጠረፍ እየተዘዋወሩ ወንጌልን ይሰብካሉ፡፡

የእናት ቤተ ክርስቲያናቸውን ርእይ በማንገብ ለወገኖቻቸው በጥምቀት የሥላሴ ልጅነትን ለማሰጠት ለቀናት በረኃውን በእግር ያቋርጣሉ፤ እነርሱ በእግር ሁለት፣ ሦስት ቀን የሚወጡ የሚወርዱበትን መንገድ ሌሎች የጥፋት መልእክተኞች (መናፍቃን) በዘመናዊ ተሽከርካሪ ገደል ኮረብታውን ጥሰው፣ በግል ሄሊኮፕተር ጭምር ያለ ችግር ቀድመው በመድረሳቸው ብቻ ወገኖቻችንን ይነጥቃሉ፤ ያልዘሩትን ያጭዳሉ፡፡ ይህም ለእኛ ሰባክያነ ወንጌል ሌላ ድካም ይኾንባቸዋል፤ ቀድመው ባለ መድረሳቸው በወገኖቻቸው ላይ የተዘራውን ክፉ አረም ለመንቀል ጊዜም ጕልበትም ይፈጃልና፡፡

እነዚያ የበረኃ ሐዋርያት ‹‹ወልድ ዋሕድ›› ብለው ሲያስተምሯቸው፣ ስለ ቅዱሳኑ ምልጃ ሲነግሯቸው፣ የእግዚአብሔርን መንግሥት መውረሻ ስለኾነችው ዳግም ልጅነትን ስለምታሰጠው አሐቲ ጥምቀት ሲያበሥሯቸው ‹‹እስከዚህ ዕድሜያችን ድረስ ስንጠብቃችሁ ነበር፤ እኛ የምናምነው አያቶቻችን የነገሩንን የቄሶች ሃይማኖት ነው፡፡ አስተምሩን፤ አጥምቁን፤›› ይሏቸዋል፡፡

ሰባክያኑ ከዚህ ያለውን አረም ነቅለው ሌሎች ወገኖቻቸው ጋር ለመድረስ ሲነሡ በክንፍ አይበሩ ነገር እንዴት ይድረሱ? ሥጋ ለባሽ ናቸውና ከመንገድ ይመለሳሉ፡፡ እነዚህ የበረኃ ሐዋርያት በአንዲት ሞተር ሳይክል እጦት ምክንያት በጊንጥና በእባብ እየተነደፉ፣ አጋዥ አጥተው ለወገኖቻቸው ቃለ ወንጌልን ሳያዳርሱ ይቀራሉ፡፡

እነዚህ ሐዋርያት ያለምንም እገዛ በረኃውን በእግር እያቋረጡ ከ፹፮ ሺሕ በላይ ወገኖችን በጥምቀት የሥላሴ ልጅነትን እንዲያገኙ ማድረግ ከተቻላቸው፣ ድካማቸውን በትንሹም ቢኾን ብንቀንስላቸው ደግሞ በመቶ ሺሕ የሚቈጠሩ ወገኖችን እንደሚያስጠምቁ የታመነ ነው፡፡

በጕዞ የደከመ የሰባክያኑን ጕልበት ለማደስ ፍቱን መድኀኒቱ ሞተር ሳይክል ነውና እኛ ከቤታችን ኾነን በጕዞ ሳንደክም አንዲት ሞተር ሳይክል በመለገስ ተራራውንና ቁልቁለቱን፣ በረኃውንና ቁሩን ከሐዋርያቱ ጋር አብረን እንውጣ፤ እንውረድ፡፡ የስብከተ ወንጌል አገልግሎቱንና ሰባክያኑን በመደገፍ የበረከቱ ተሳታፊዎች እንኹን፡፡

ሞተር

በጎ አድራጊው ምእመን የሞተር ሳይክል ስጦታ ሲያበረክቱ

ለድጋፋችሁና ሐሳቦቻችሁ በ 09 60 67 67 67 ደውሉልን

በማኅበረ ቅዱሳን የትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ዋና ክፍል የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ መርሐ ግብር